መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » እንኳን ለ2014 ዓ.ም ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

የትምህርቱ ርዕስ | እንኳን ለ2014 ዓ.ም ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

ሰው ለመሆንህ ሰላም እላለሁ !

ሰው ፣ ሰው መሆንን ሲጠየፍ አንተ ግን ሰው ሆንህ ። ሰው አምላክነትን በሕግ አፍራሽነት ሲሻ ፣ አንተ ግን በፍቅር ሰው ሆንህ ። ሰው የሌለውን አምልኮት ሲያስስ ፣ አንተ ግን የሌለህን ሰው መሆን ገንዘብህ አደረግህ ። ሰው የሌለውን ከፍታ ሲናፍቅ ፣ አንተ ግን የማይገባህን ዝቅታ ሰው በመሆን ወረስህ ። ሰው ጌትነትን ሲፈልግ ፣ አንተ ግን በባሪያ መልክ ተገለጥህ ። ሰው ፣ ሰውን ሲሸሸው ፣ አንተ ግን ሰውን በፍቅር ተከተልከው ። ሰው ፣ ሰውን ለመርዳት ሰው መሆኔ በቂ አይደለም ሲል ፣ አንተ ግን ሰው ለማዳን ሰው መሆን ያስፈልጋል ብለህ መጣህ ። ሰው ከሆነችው ከባሕርያችን መመኪያ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ፣ ከንጽሕትና አዛኝ ከምትሆን እናትህ ሰው ሆንህ ። ሰው ከእናቱ ማኅፀን ሲወጣ ቀዳማዊ ልደቱ ነው ፤ አንተ ግን ከድንግል ማርያም ስትወለድ ዳግማዊ ልደትህ ነው ። አዳም ከመሬት ፣ ሔዋን ከገቦ አዳም ፣ አቤልና ቃየል ከዘር ከሩካቤ ተወለዱ ። ያንተ ሰው መሆን ያንተ ልደት ግን ከድንግል ነው ። ልዩ ለሆነው ልደትህ ሰላም እላለሁ ! ለዳግም ልደት ታበቃን ዘንድ ዳግም ለተወለድከው ፣ ሰውነትን ታከብረው ዘንድ ሰው ለሆንከው ፣ ደናግላንን ከፍ ታደርጋቸው ዘንድ በድንግልና ለተወለድከው ፣ ለምስኪኖች ታዛ ትሆን ዘንድ በበረት ለወደቅኸው ክርስቶስ ሰላም እላለሁ !

ክርስቶስ ሰው ሆነ ፤ ሰዎች ሆይ ደስ ይበለን !

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ታኅሣሥ 29 ቀን 2014 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም