እንኳን ለበዓለ ብሥራት አደረሳችሁ !
በእውነት በእኛ ዘንድ እንዳለው በጊዜው ልክ (በመጽነሻ ጊዜ) ፣ በተፈጥሮ ሕግ መሠረት /ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን መጽነስ/ ፣ በሌላም ከተፈጥሮ በላይ በሆነ መልኩ እግዚአብሔር ቃል ከአርያም በአንቺ ላይ አደረ ፣ ቅዱስ በሆነው ማሕፀንሽም አዲሱን አዳም ፈጠረ ። መንፈስ ቅዱስ የመጽነስን ኃይል በሰጣት መጠን እርሱ አካሉን ከእርሷ ነሣ ።
ውድ የሆነው ዕንቊ ከሁለት ባሕርይ በባህር ምሥጢራዊ ምልክት ማለትም ከመብረቅና ውኃ እንደ ተገኘ ፣ ልክ እንደዚሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ መቀላቀልና ያለ መጠፋፋት ንጽሕትና ምርጥ ከሆነች እድፍም ከሌለባት ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ። (እርሱም) ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው፣ በሁሉም ነገሮች ውስጥ ከአብ ጋር የተካከለ ፣ ከኃጢአት በቀርም በሁሉም ነገር ከእኛ ጋር የተካከለ ነው ።
አብዛኛዎቹ (የብሉይ ኪዳን) አባቶችና ነቢያት ያዩትና የዓይን ምስክሮች ይሆኑ ዘንድ ወደዱ ግን አልደረሱም ። ጥቂቶቹ እርሱን በምሳሌ በድንግዝግዝ ተመለከቱት ። እንደገና ሌሎች ደግሞ መለኮታዊውን ድምፅ በደመና ለማዳመጥ ብሎም መላእክትንም ያዩ ዘንድ ታደሉ። ነገር ግን ሊቀ መልአኩ ገብርኤል ደስ የሚያሰኘውን “ደስ ይበልሽ ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ” (ሉቃ 1፥28) የሚለውን ዜና ይዞ ራሱን በብርሃን የገለጠላት ንጽሕት ድንግል ለሆነችው ለማርያም ብቻ ነው ። በዚህም ምክንያት ቃልን ተቀበለች ፤ በተመሳሳይ ጊዜም በተፈጥሮ ሕግ መሠረት እጅግ ውድ የሆነውን ሉል ወለደችው ።
እንግዲህ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ እናንተም ኑና መንፈስ ቅዱስ ባደረበት ባለ በገናው ዳዊት የተማርነውን ዝማሬ እንዲህ እያልን አብረን እንዘምር “አቤቱ ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት ።” (መዝ 133(132)፥8) ቅድስት ድንግል በእውነቱ በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠች፣ የቅድስተ ቅዱሳኑን መላ ስጦታ የተቀበለች ታቦት ነች። “አቤቱ ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ” በቅድሚያ የተፈጠረውን በኃጢአትም ወድቆ የነበረው የሰው ዘር ታነሣ ዘንድ አቤቱ ጌታ ሆይ ከአባትህ እቅፍ ተነሥ ። እነዚህን ነገሮች አስቀድሞ ተመልክቶ ዳዊት በትንቢት ከእርሱ ስለሚወጣው በትር ወደዚያ ውብ ወደሆነው ፍሬም ስለሚበቅለው አበባ እንዲህ አለ ፤ እንዲህ አለ ፡- “ልጄ ሆይ ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና ፥ እርሱ ጌታሽ ነውና ።” (መዝ 44(45)10-11)። ልጄ ሆይ ከዘመናት በፊት ስላንቺ ስ
ለተነገረው ትንቢት፣ ትንቢት የተነገረለትን ነገር በመረዳት ዓይን ታዪ ዘንድ ስሚ ። ቀደም ብዬ ነገሮችን ስነግርሽ ስሚኝ ፣ ፍጹም የሆነውን ምሥጢር የሚያውጅልሽን መልአክ ስሚው ። እጅግ ተወዳጅ የሆንሽው ሆይ እንግዲህ ነይ ፤ ከእኛ አስቀድሞ ወደነበረው ትዝታ እንመለስ ፤ ከእሴይ ድንቅ በሆነ መንገድ የወጣውን አንድ ላይ እናክብረው፣ እናሞግሰው ፣ እናመስግነው ፣ እንባርከውም ።
ለተነገረው ትንቢት፣ ትንቢት የተነገረለትን ነገር በመረዳት ዓይን ታዪ ዘንድ ስሚ ። ቀደም ብዬ ነገሮችን ስነግርሽ ስሚኝ ፣ ፍጹም የሆነውን ምሥጢር የሚያውጅልሽን መልአክ ስሚው ። እጅግ ተወዳጅ የሆንሽው ሆይ እንግዲህ ነይ ፤ ከእኛ አስቀድሞ ወደነበረው ትዝታ እንመለስ ፤ ከእሴይ ድንቅ በሆነ መንገድ የወጣውን አንድ ላይ እናክብረው፣ እናሞግሰው ፣ እናመስግነው ፣ እንባርከውም ።
ሉቃስ በተቀደሰው ወንጌል ትረካ ላይ የሚመሰክረው ስለ ዮሴፍ ብቻ ሳይሆን የአምላክ እናት ስለሆነችው ስለ ማርያምም ነው ። ስለ ቤተሰቡና ስለ ዳዊት ቤትም እንዲህ ብሎ ይገልጣል፡- “ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ። በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች ፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው ፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው” (ሉቃ 2፥4-7) ። ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረውን እርሱን በመጠቅለያ ጠቀለለችው። በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውና በእልፍ አእላፍ መላእክት የሚመሰገነውን እርሱን በግርግም አስተኛችው ። በነጻ ፈቃዱ ኢምክንያታዊ የሆነውን ሰው እውነተኛ አመክንዮ ይሰጠው ዘንድ ለእንስሳት ብቻ በተለየው ግርግም የእግዚአብሔር ቃል ጋደም አለ ። የሚበሉ እንስሳት በሚተኙበት በረት ሰማያዊው እንጀራ ወይም የሕይወት እንጀራ በምድር ላይ እንደ እንስሳ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች የመንፈሳዊ ምግብ ዘላለማዊ ተካፋዮች ያደርጋቸው ዘንድ በግርግም ተኛ። ለእርሱ ቤት ውስጥ እንኳን ማረፊያ አልተገኘለትም። በቃሉ ሰማይና ምድርን የመሠረተው እርሱ (ማረፊያ) ቦታ አላገኘም ፤ “ሀብታም ሲሆን ፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ” (2ኛ ቆሮ 8፥9) ። ለእኛ ስላለው መልካም ነገር ስለ ባሕርያችን ድኅነት እጅግ ታላቅ የሆነ ትሕትና መረጠ ።
ከመነገር በላይ የሆነውን የድኅነትን ምሥጢር ጽድቅን በምልአት የፈጸመው እርሱ በሰማይ በአባቱ እቅፍ፣ በዋሻም በእናቱ እቅፍ አረፈ ። ሰማያዊ መዘምራን “በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና በምድርም ለሰው ልጅ ሰላም” እያሉ በመዘመር ከበቡት ። በሰማይ በአብ ቀኝ ተቀምጦ ነበር ። በግርግም በኪሩቤል ላይ እንደነበረው አረፈ ። በእውነት በዚህም የኪሩቤል መንበሩ፣ የንጉሥ ዙፋኑ ነበር ። ክርስቶስ አምላካችን ያረፈበት ቅድስተ ቅዱሳን፣ በምድርም የከበረች ብቸኛዋ፣ ከቅዱሳን በላይ ቅድስት (በሆነችው በድንግል ላይ ነበር።) ለእርሱም ምስጋና ፣ ክብርና ኃይል ይሁን። ቅዱስ ከሆነው ከአብ ሕይወት ሰጪ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አሁንና ዘላለም ፣ ለትውልደ ትውልድ ። አሜን !
ታሕሣሥ 23 ቀን 2011 ዓ.ም.