መግቢያ » ግጥም » ልባችሁን አምጡ

የትምህርቱ ርዕስ | ልባችሁን አምጡ

            ቤተ ጳውሎስ፤ ማክሰኞ ሰኔ 12 2004 ዓ.ም.
ከዘመን በፊት ዘመን ተሻግሮ
ከርቀት ሆኖ የሩቅ ዘመንን አመስጥሮ
ኢሳይያስ ነቢይ ብሉይ ወሐዲስ
አሰምቶ ጮኽ ቃለ ትንቢት ሲደርስ
የሰማነውን ከቶ ማንስ ያምናል
የጌታችን ክንዱ ለማንስ ተገልጧል
ያዳንከን አንተ ነህ ብሎ መዘከሩ
ዕፁብ ነው ድንቅ ነው ግሩም ነው ነገሩ፡፡ 

ኢሳያስ ጻድቁ
ውበት የፈጠረው ደምግባቱ ጠፍቶ

ኃይልና ብርታቱ ደክሞ ዝሎ ቃቶ
ከሰውነት ተራ ተንቆ ተገፍቶ
መደረቢያ ካባ ለዕርቃኑ ጠፍቶ
የማይሞተው ጌታ ሞተ ተቀበረ
የበጐቹ እረኛ እጅ እግሩ ታሠረ
እኰ ይህን እንዴት ጆሯችን አመነ?
እያለ በምስጢር እየተነተነ
ማህበረ ነቢያትን በፍቅር ጠየቀ?
በሸላቾቹ ፊት የተጐተተ በግ
እርጉም ተብሎ የሰማያት ጻድቅ
በክፉ ህሊና በህግ ተገፍቶ
በሊቀ ካህናት  ሸንጐ ፍትህ ጠፍቶ
ሞት ተፈረደበት ይግባኝ ተከልክሎ
የፍትህ አለቃ ፍትህ ተበድሎ
እኰ ማንስ አምኖ እንዴት ይናገራል
ክንዱ ብድራቱ ለማንስ ተገልጧል
የሰማነው ዜና ከዓይን ከማየት በጆሮ ከመስማት
ይገዝፋል ይረቃል ካስተዋሉት በእምነት
አዎ ነቢያት የምታምኑት ሁሉ
ምስጋናውን አብዙ ለዚህ ድንቅ ፍቅሩ
ታላቁን መስዋዕት ልባችሁን አምጡ
የመስቀሉን ዜማ በተደሞ አድምጡ
አትርሱ ዘክሩ ታላቁን ውለታ
የደስታ እንባ ለሞትክልን ጌታ
ጭብጨባው ዕልልታው ላንተ ይሁን በሉ 
ከዘመናት ደስታ ጽድቁን ተቀበሉ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም