የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

መንፈስ ቅዱስ ሆይ !

የእስትንፋሴ መሠረት ፣ የመኖሬ ምሥጢር ፣ የመንገዴ ቀያሽ ፣ የሃይማኖቴ አስረጂ ፣ የጥያቄዬ መልስ ፣ የራሴ ራስ ፣ የኑሮዬ ኑሮ ፣ የነፍሴ ነፍስ ፣ ያልተፈጠርህ ሕይወት ፣ የምስቅልቅሉ አስተካካይ ፣ የፀጥታው ወደብ ፣ የሰማይ መነጽር ፣ የመንፈሳዊ ዓለም ብርሃን ፣ መካኑን ባለፍሬ የምታደርግ ፣ የጸጋ ባለቤት ፣ የሀብታት ምንጭ ፣ የቤተ ክርስቲያን መሥራች ፣ የአገልጋዮች አንደበት ፣ የካህናት ሞገስ ፣ ሳልኖር የምታውቀኝ ፣ ኖሬ የምታበረታኝ ፣ ሞቴን በትንሣኤ የምትለውጥ ፣ በዘላለም ከተማ የምትቀበለኝ ፣ የምትሠራኝ ፣ የምትሠራብኝ ፣ የምታግዘኝ ወዳጄ ፣ ያለነቀፋ የምታስተምረኝ መምህር ፣ የምደገፍብህ ምርኩዝ ፣ የበረሃው ጥላ ፣ ሳላይህ ያየኸኝ ፣ የሕፃንነቴ አሳዳጊ ፣ በሚወዱኝ ውስጥ ሆነህ የወደድከኝ ፣ ዘመን ሲያባርር መጠጊያ ፣ ያከበረ ሲያዋርድ አንተ ንጹሕ ካባ ፣ ቀኑ ሲከፋ መጠጊያ ፣ የእናት ደጅ ሲዘጋ መጽናኛ ፣ መነሻ ሲጠፋ የአልፋው ፊደል ፣ መድረሻው ጭልም ሲል የዖሜጋው ማኅተም ፣ ጠባዬ ሲበላሽ አዳሽ ፣ ስቆሽሽ አጣቢዬ ፣ ሰይጣን ሲከሰኝ የስርየት ቃሌ ፣ ስሜ ሲጠፋ ስሜ ፣ ከጭቃ ስወድቅ ንጽሕናዬ ፣ ፍጥረት ሲያምፅብኝ ተዋጊዬ ፣ ከራሴ ስጣላ ሰላሜ አንተ ነህ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ! ላንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም ፣ ከልቤ እስከ አርያም ክብር ምስጋና ይሁን ! አሜን !
የሚሻህ ሁሉ አሜን ይበል ።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ሰኔ 22/ 2015 ዓ.ም

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ