ማክሰኞ፣ የካቲት 13 2004 ዓ.ም.
የባሪያውን ልብስ
አድርጎ እንደክት
ገረዲቱንም ሊያከብር
ዘርግቶ የክብር ወንበር
በፈጨት ድምጽ ሊሰበስብ ጠርቶ
እርሱን እንድንመስል እያስዋበ ስሎ
ከዘላለም የጽድቅ መንግስቱ
በአንድ መንጋ በበረቱ
ሊኖር ተከቦ በወዳጆቹ
ወረደ የክብራችን ሰገነቱ
የትንቢት ቃል ሊዘጋ
ሆኖ የተስፊችን ኦሜጋ
በጠላት ፉት ሊፇላ ዘይቱ
ሊያሰፊን በርስቱ
ወረደ አክባሪው
እኛን ሰሪው
ወንጌልን ለድሆች
ብሎ የምስራች
እስራትን ፇቶ
ሞትን ውጦ ረትቶ
ማየትና መስማት
ድንቅ ተአምራት
ጽድቅ እያረበበ
ጽድቅ እየመገበ
ሊያኖረን ነው ጌታ ከሰማይ መውረዱ
እንዲያ አለዋጋ እኛን በመውደዱ
እንኪያ ተወዳጆች
የእርሱ ባለሟሎች
ድካማችንን ሊያግዝ
ደግፎንም ሊይዝ
እርሱ ለከፍታ ከሆነ የመጣው
የእኛ ወደ ውርደት መንደርደር ምንድር ነው?
በሚተጋ ጽናት በታገሰ ጸሎት
በተወደደ ቃል በፆምና ምፅዋት
መውረዱን እናድንቅ ከሰማይ መንበሩ
በእርሱ እንድንከተት ከፅድቅ ሀገሩ፡፡