የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ማን ይግዛን?

ቤተ ጳውሎስ፤ ቅዳሜ ነሐሴ 5 2004 ዓ.ም.
መሪመፈለግ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ጠባይ ነው፡፡ ሕዝብአንድ ድምጽ ኖሮት እንዲተዳደርና ጠላቱን እንዲከላከል መሪያስፈልገዋል፡፡ መሪ የነጻነት ምልክት ነው፡፡ ሕዝቡን ቢበጅም ባይበጅም ንጉሥያላት አገር ነጻነት እንዳላት ይታወቃል፡፡ መሪነት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ  ነው /ምሳ.8፡15/፡፡ መሪ ለመሆን ግንየሚያስፈልገው ቀድሞ ማየትነው፡፡ ቀድሞ ያላየ መሪመሆን አይችልም፡፡ የሥልጣን ሥርዓት የእግዚአብሔር ሥርዓት ነው/ሮሜ.13፡1-7/፡፡ ገዥና ተገዢመሆን ግን የሥራ ድርሻእንጂ የስብእና ልዩነት አይደለም፡፡ በዘመናት መሪዎች ሕዝቡ ለእነርሱ እንደ ተፈጠረ ያስቡ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድግን መሪው የሕዝቡ እንጂ ሕዝቡ የመሪው እንዲሆን አይደለም/2ሳሙ.233-41ነገ.1271ጴጥ.52-3/፡፡
ሕዝብ በሌለበት ወንበር አይኖርም፣ ሕዝብባለበትም መሪ አይቀርም፡፡ ሁላችንም እኩልነን የሚሉ ወገኖች እንኳን ስያሜውን አይቀበሉት እንጂ መሪ አላቸው፡፡ ሥራው ካለ ስያሜው ትንሽ ድርሻ ነው የሚወስደው፡፡ ሥልጣን የገዢዎች ደሴትአይደለም፡፡ ስለዚህ የመንግሥትና የሕዝብ የሚባል ነገርአይኖርም፡፡ የመንግሥት የሕዝብ ነው፣የሕዝብም የመንግሥት ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም አንዱየአንዱ ነውና፡፡

ይህ ሲሆን ነው ሥራ የሚሠራው፡፡  ብረት ማለት አንድየጋራ ነገርን በእኩል መጠቀምና አንዱየአንዱ እስኪሆን ድረስ ራስንመካድ ወይም መሞት  መሆኑን ቃሉ ይነግረናል፡፡
መሪን መውደድ ጸጋነው፡፡ ለመውደድ ግን መውደድ እንጂ ምንም ቅድመሁኔ ዎችየሉትም፡፡ ለመሪዎች መጸለይ ግድነው፡፡ ምክንያቱም በፀጥታ  መኖር የምንችለው ለእነርሱ በትጋት ስንጸልይ ነው/1ጢሞ.21/፡፡ ጳውሎስ ለንጉሥ በብርቱ መጸለይን ሲናገር በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ኔሮን ቄሣር መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ኔሮንበጭካኔው ወደር ያልነበረው የክርስትና አሳዳጅና ከሦስት ዓመትበኋላ ጳውሎስን የሚሰይፈው ቢሆንም ሊጸለይለት ይገባነበር፡፡ ስንጸልይ እግዚአብሔር በፍቅር ይነካቸዋል፡፡ ለመሪዎች መጸለይ ካልቻልን ሰይጣን ሲያውካቸው ሕዝቡን ያውካሉ፡፡

መሪዎች እጅግ ፍቅርየሚያስፈልጋቸውና ፍቅርን የተራቡ ናቸው፡፡ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ሕዝቦች መሪዎቻቸውን ይጠላሉ፡፡ ማንምየመጥላት መብቱ ዲሞክራሲ የሚባል የምድር ሕግቢሆንም ክርስትና ግን የማፍቀርን መብትየሚጠቀም ሰማያዊ ሕግ ነው፡፡ ማፍቀር ሲቻልመጥላት እንዴት ይመረጣል? ሰዎች ነጻነት አላችሁ በተባሉበት አገር ሁሉ ነጻነታቸውን ጥላቻቸውን ለመግለጥ መጠቀማቸው በመሪዎችና በሕዝብ መካከል ረጅምገደል ፈጥሯል።
በዓለማችን ላይ ብዙ ገዥዎች ተለዋውጠዋል፡፡ ከአውሬ በጥቂት የሚለዩ አምባገነኖችም ተከስተዋል፡፡ ደጋግነገሥታትም ራቅ ራቅ ብለው ተነሥተዋል፡፡ የእነዚህ ደጋግነገሥታት ምንጫቸው ጥሩ ስብእናቸው ሳይሆን ስብእናን የሚለውጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ነበር፡፡ ሥልጣን የሕዝብ አደራ መሆኑን መቀበል ከብልግና አያግድም፡፡ ሥልጣን የእግዚአብሔር አደራመሆኑን መቀበል ግን ጠንቃቃ ያደርጋል፡፡ የክፉገዢዎች ተጽእኖም አሁን ያሉበት ወንበር ሳይሆን ያደጉበት ቤተሰብና  ብረተሰብ የነፈጋቸው ፍቅር ነው፡፡ ማንምቢሆን ያልተቀበለውን አይሰጥም፡፡
 እግዚአብሔር በተናቁ ሰዎች ዓለምን የሚያናውጥ ሥራ ይሠራል፡፡ በማይገመቱ ሰዎች ፈዋሽ  ሪክ መሥራት ባሕርይው ነው፡፡ ሰይጣን ግን በትልልቅና በዝነኛ ሰዎች ይጠቀማል፡፡ በቀላሉ ሥራው ይከናወንለታልና፡፡ ስለዚህ ለአገርና ለቤተክርስቲያን መሪዎች በብርቱ የምንጸልየው ሰይጣን ዒላማ ስለሚያደርጋቸውና በቀላሉም ብዙ ጥፋት ሊከሰት ስለሚችል ነው፡፡
        በዓለማችን ላይ በእግዚአብሔር ሳይሆን በክንዳቸው የሚተማመኑ ነገሥታት ተፈራርቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያሉትየምድር ነገሥታት በሙሉ በአፋቸው የእግዚአብሔር ስም የማይገባ ሃይማኖት የለሽመሪዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለገዛሕጋቸው እንኳን ዘዝ እያቃቸው ራሳቸውን እየተቃወሙ የሚኖሩ፣ ውሸትን በኃይል እውነት ለማድረግ የሚጥሩ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ነገሥታት እምነትን ባይፈልጉም ሃይማኖትን ግንየሥልጣናቸው ሞግዚት ለማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡ እግዚአብሔር የሌለው ሰው ለክፋቱ ምን ከልካይ ይኖረዋል?
ሥልጣን ዐጽመ ርስትመሆኑ ቀርቶሥልጣን ከቤተሰብ ወደ ሕዝብመጥቷል፡፡ ከሕዝብም ወደ ቅኖችሳይሆን ማድረግን በንግግር ተክተው ወደሚኖሩ የአንደበት  ይሎች አጋድሏል፡፡ በምኞት ሕብስተ መናእንሰጣችኋለን ያሉትም የተለመደውን ኑሮእንኳ ሲያደፈርሱት በታሪክ አይተናል፡፡ ከተጨነቀችው ዓለም ጋር የተጨነቀችው ኢትዮጵያ ፊውዳሊዝምን፣ ሶሻሊዝምን፣ ካፒታሊዝምን መፍትሔ ቢሆን ብላ አስተናግዳለች፡፡ ዛሬምከእነዚህ የተለየ የፖለቲካ ራእይአሳዩኝ ትላለች፡፡ የኢትዮጵያ መልሱ ግን እግዚአብሔር ብቻነው፡፡
የእስራኤል ልጆች ብርቱጠላታቸው ከነበሩት ከምድያም እጅጌዴዎን ከታደጋቸው በኋላ እንዲህ አሉት፡ከምድያም እጅ አድነኸናልና አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም ደግሞ ግዙን አሉት፡፡ ጌዴዎንም፡እኔ አልገዛችሁም ÷ልጄም አይገዛችሁም፤ እግዚአብሔር ይገዛችኋል አላቸው /መሳ.8÷22-23/፡፡ እኛስኢትዮጵያውያን ማን ይግዛን?  እግዚአብሔር በጽድቅ ይግዛን!*
                               
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ