ረቡዕ፣ ኅዳር 13 2004
ከመቃብር፤ከተማሰው ጉድጓድ ማዶ
ከሚታየው፤ ከዚህ ዓለም ትንሽ ጎጆ
ከጨለማ ወዲያ ከሞትም ባሻገር
ተስፋዬ እዛ ነው ከሰማያት አገር፡፡
ተስፈኛ አይደለሁም ከፍጡር እንጀራ
ከትዳር ከሀብቱ ከስልጣኑ ተራ
አላስብም ከቶ ነገድና ዘሬን
ለጌታ ያልሆነ ችሎታ እውቀቴን
ተስፋ ከምድር የለም ከሰዎች መካከል
ሚጨበጥ ሚዳሰስ የሚታይም አይደል፡፡
ተስፋዬም ረዳቴም ከላይ ነው ከሰማይ
ሣምነው ማየው እንጂ አይደለም የሚታይ
ሩጫዬን ሮጣለሁ በወደደኝ በእርሱ
በአይኖቼ አያለሁ ሙታን ሲነሱ
ወዲያ ነው ተስፋዬ በአይን አይታይም
አመስጋኝ ነኝና ማመኔ አይዝልም
ማየቴ አያምንም ማመኔ ግን ያያል
ልቤ ከተስፋዬ በሰማያት አርፏል፡፡