ወዳጄ ሆይ !
የዚህን ዓለም ንትርክና እልቂት የሚገድበው አንድ ነገር አለ ፣ እርሱም ይቅር ለእግዚአብሔር ነው ። እግዚአብሔርን የረሳ መከራ አይረሳውም ። የአብርሃም ሥራ ለዘር ፣ የይስሐቅ ሥራ ለመከር ፣ የያዕቆብ ሥራ ለጎተራ እንደበቃ ተናባቢ ትውልድም ሙሉ በረከት ያገኛል ። የእግዚአብሔርንና የንጉሥን ውለታ መርሳት ከዕድል ጋር መጣላት ነው ። ዕንባን ከዓይን የሚያደርቅ ፣ ኀዘንንን ከልብ የሚያርቅ የእግዚአብሔርን የፍቅሩን ዜማ ማሰላሰል ነው ። ያለፈው ደግነትህ ላይ ዛሬ ሳትጨምርበት እርሱን ብቻ እያሰብህ መኖር የራስህን ታሪክ ተራኪ ያደርግሃል ። ኑሮውን በሰው ሞት ላይ ያደረገ አንድ ቀን እንደሚሞት የዘነጋ ነው ። እስከ መቃብር ድረስ በጎ ግብር ሥራ ። ደግ ለመሆን የምታባክነው ጉልበት ክፉ ለመሆን ከምትደክመው ድካም ያነሰ ነው ።