የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ረቡኒ መጽሐፍ መግቢያ

የዲ/ን አሸናፊ መኰንን ገጽ
ረቡዕ ሚያዝያ  ፲፭፣ ፳፻፮ ዓ/ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፳
                                       መግቢያ                                      
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር የገለጡ ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎችን እናገኛለን፡፡ እነዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደወደዳቸው ተረድተው እነርሱም ወደውታል፡፡ ፍቅራቸውንም በኑሮና በሕይወቸው መስክረዋል፡፡ ብዙዎቻችን እግዚአብሔርን፡የመውደድ ዕዳ ያለበት፣ መጥላት ስለማይችል የወደደን፣ የእኛን ፍቅር ግን ለመስማት የማይፈልግ አድርገን እናስበዋለን፡፡ ነገር ግን አፍቃሪ ፍቅር ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔርም ፍቅራችንን መስማትና ማየት ይሻል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔርን በማስመሰል ፍቅር ልንወደው አንችልም፡፡ እርሱ የተሰወረውን የውስጥ አሳብ ያውቃልና፡፡ በእውነተኛ ፍቅር ግን እንድንወደው ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር እንዴት እንደወደዳቸው የተረዱ እነዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች እርሱን መውደድ ብቻ ሳይሆን መውደድ የሚያስከፍለውንም ዋጋ በመክፈል በኑሮና በሞቸው አስከብረውል፡፡ ከእነዚህ ዕድለኞች አንዷ መግደላዊት ማርያም ናት፡፡  ታየተዋበ፣ የመጣችበት መንገድም የቀና ባይሆንም ችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ስምና በመለወጥ ከሰው ቍጥር ደምሯል፡፡ ላቅ ስቃይ ወደላቅ ዕረፍት መልሷል፣ ለአንድ ቀን እንማዕበል ካልተለየው ኑሮ አውጥቶ በታላቅ ፀጥታ አሳርፏል፡፡ዲያ ለሰላሟና ለሕይወቷ ፍቅሯን የምትገልጥበት ሁነኛ ሰዓት ደረሰ፡፡ ጊዜ ፍቅሯ የሚመዘንበትም ጊዜ ነበረ፡፡ ችን ሲሰቃይ ከመስቀሉ አጠገብ አልተለየችም፡፡ ሞቶም አልረሳችውም፡፡ ቅዱስ ሥጋውን ሽቱ ልትቀባ ወደ መቃብሩ ገሰገሰች፡፡ እርሱ ግን ሕያው ነውና የሙንን ሽቱ አልተቀባም፡፡

መግደላዊት ማርያም ያንን ደግ መምህር ለዘላለም ያጣችው መስሏት ልቧ በሀዘን ተሰብሯል፡፡ ቢያንስ ቅዱስ ሥጋውን ሽቱ ቀብታ ለመሰናበት ብትመጣም ሥጋውንም በማጣቷ ሀዘኗ ወደር የሌለው ሆነ፡፡ የተሰረቀ ስለመሰላት መሰረቁን ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች፡፡ የተሳሳተ ምስክርነት ቢሆንም ሲገለጥላት ግን እውነተኛ ምስክርነት ይዛ ወጥለች፡፡ መላእክት ቢገለጹላትም መረጋጋት አልቻለችም፡፡ ነፍሷ የሻተችውን እስክገኝ ዕረፍት አልነበራትም፡፡ ቅዱስ ሥጋውን ባገኘው እወስደዋለሁ የሚል ቍርጥ አሳብ ያዘች፡፡ ይህ ከባድ ነው፡፡ የትደርገዋለች? ፍቅሯ ግን ይህን ለማድረግ ጨክኗል፡፡ በዚህ ጊዜ ችን ተገለፀላት፡፡ እርሱም በስሟ ሲጠራት «ረቡኒ» አለችው፡፡ መምህር ሆይ ማለቷ ነው፡፡ ዛሬም የምትማረው፣ ገና ያልገባት ነገር ስላለ መምህር ሆይ ብላ ያስተምራት ዘንድ ፈለገችው፡፡
በዘመናት ሁሉ ሕዝቦች መምህር ይፈልጋሉ፡፡ የመምህር ፍላጎታቸው ግን የጨው ውሃ እንደጠጣ መልሶ ያስጠማቸዋል እንጂ እንደ ልባቸው የሚሆን መምህር አላገኙም፡፡ መምህራን ነን ብለው የተነሡም በየዘመናቱ ተረኛ ተመጋቢዎች እንጂ መጋቢዎች ስላልሆኑ እልፍ ይላሉ፡፡ እነርሱ ፌርማታውን ያውቁልና ያለይሉኝታ ሲወርዱ እስከ መጨረሻው የተሳፈራቸው ሕዝብ ግን መድረሻው ግራ ገብቶት ይቅበዘበዛል፡፡ አሁንም እውነተኛውን መምህር ክርስቶስን ከመፈለግ ሌላ መምህር ከሰማችሁ አፋልጉኝ እያለ ገና ለመንከራተት ይኖራል፡፡ መምህር ፍለጋ ከአንዱ እምነት ወደ አንዱ እምነት ሲንከራተቱ በየዱሩ የቀሩ፣ የጨካኝ መምህራን ነን ባዮች የግፍ ማርኪያ የሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ለልባችን የቀረበውን እውነተኛውን መምህር «ረቡኒ» ያለማለችን ቅጣት ነው፡፡ መምህሩን «መምህር ሆይ» ብለን ስንቀርበው እውነተኛ እረኞችን ይሰጠናል፡፡ እረኞች ሁሉ በግ ያሰማራሉ፡፡ እውነተኛው መምህር ክርስቶስ ግን በግ ያደርገናል፡፡
ነቢዩ፡«ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ. የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል» (ኢሳ. 54.13) በማለት ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔርን መምህር አድርገን ባልተመላለስንበት ዘመን ሁሉ ብንማርም ሰላም አልነበረንም፡፡ ከእርሱ ለመማር ስንቀርብ ግን ሰላሙን አብዝቶልናል፡፡ዲያ የእኛስ መምህራችን ማን ነው? ከፍ ያሉትና ትልቅ ተስፋ የጣልንባቸው ሲሰወሩብን እጃችንን ይዞ የሚመራን መምህራችን ማን ነው? አዎ ከሰው የሚገኝበትላቅ መምህር አለ፡፡ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
ይህች አነስተኛ መጽሐፍ ለፍቅሩና ለመምህርነቱ የማትመጥን፣ የመግደላዊት ማርያም ፍቅሯ፣ ፍቅራችንን ዘበው ለማረፍ ተብሎ የተጻፈ ነው፡፡ የሚያጽናናና የሚመክር መምህር ለተራበው ለዛሬው ትውልዳችን ይህች መጽሐፍ መቅረዝ እንደምትሆን እናምናለን፡፡ ለወደደን ጢአችንም በደሙ ላጠበን ለጌችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ አምልኮት ይሁን፤ አሜን፡፡
ረቡኒ
በዲ/ን አሸናፊ መኰንን
የመጀመሪያ እትም ሚያዝያ 2002 ዓ/ም
አድራሻ – 0911 39 35 21/0911 67 82 51
ፖ.ሳ.ቁ. 62552
አ.አ. ኢትዮጵያ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ