የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ረቡኒ መጽሐፍ – በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን

የዲ/ን አሸናፊ መኰንን ገጽ
እሑድ  ሚያዝያ  ፳፮ ፣ ፳፻፮ ዓ/ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
                                          
በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን
የሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን ለብዙዎቻችን ከዕረፍት ማግሥት በመሆኑ የረሳናቸው ጉዳዮች የሚወሱበት፣ ፀጥ ያሉ ስልኮች የሚጮሁበት፣ ያልተቋጩ ሩጫዎች ድቅን የሚሉበት፣ የሰዓት ተቆጣጣሪዎችና ቍጠኛ አለቆች ትውስ የሚሉበት፣ የረሳናቸው ነገሮች መቀስቀስ የሚጀምሩበት ቀን በመሆኑ የሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን «ጨለማው ቀን» እንለዋለን፡፡ በሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን ጌታችንን ካልፈለግን ስሜችን የጨገገ ነው፡፡ አንድ ሰው በየዕለቱ ሲያገኘኝ፡– «እንኳን አደረሰህ» ይለኝ ነበር፡፡ እንዲህ ሲለኝ ከሰሞኑ ያለፈ በዓል እፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን ዓመት ሙሉ «እንኳን አደረሰህ» የሚል በመሆኑ እያንዳንዱ ቀን ልዩ ቀን መሆኑን በዚህ ወጣት እግዚአብሔር አስተማረኝ፡፡ ለካ ትልቁ በዓል መኖር ነው።
አንድ አባትም ሲጸልዩ፡– «ሰላማዊ ቀን እዘዝልን» ይሉ ነበር፡፡ ሰላምንም ቀንንም የሚያዝዝ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ሁለቱ የሚገጥሙት በስንት ጊዜ አንዴ ነው፡፡ በጸሎት መንፈስ ግን ሰላማዊ ቀን ይታዘዝልናል፡፡ ነቢዩ፡«ሁሉም ባሪያዎችህ ናቸውና ቀኑ በትእዛዝህ ይኖራል» (መዝ. 11891) ይላል፡፡ ቀን እንኳ ሳይቀር የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡ ዕድሜ ስለተጨመረልን በጣም ልናመሰግንበት የሚገባን ቀን ቢኖር፣ የሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ ከዕረፍት አስነሥቶ ያሰማራን የኑሮ ጉድለት ነው፡፡ ይህ የኑሮ ጉድለት በሥላሴ ጥበብ የጐደለ ሲሆን እኛን የሚያተጋን በመሆኑ ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ጉድለት ባይኖር ከቤታችን የምንወጣበት ምክንያትናይል ባልኖረን ነበር፡፡ ጉድለት ባይኖር የሙላት ደስታ ባልኖረን ነበር፡፡ ሲሞላልን ደስ የሚለንላቅ ሐሴት ከጉድለት በኋላ የተገኘ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ዘመኑ እየፈጠነ፣ ወሩ በዓመት ለመተካት እየቸኮለ በመሆኑ ብዙ ጊዜ እናዝንበለን፡፡ «ቀኑ ይበርራል» እንላለን፡፡ ቀኑ አልገፋ ያላቸው ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ለእኛ ቀኑ ሳናስበው የሚሄድ ከሆነ ጣፍጦልናል ማለት ነው፡፡ ያልጣፈጠ ቀን የዓመት ያህል ይረዝማልና፡፡ ሌሊቱ አልፎ ብርሃን ሲመጣ እግዚአብሔር ዛሬን እንድንኖር የዕድሜ ኮንትራቱን አድሶልናል ማለቱ ነው፡፡ ስለታደሰልን ዕድሜ እጅግ ልናመሰግን ይገባናል፡፡ በሕይወት ከሌለን የማንኖረው ለጉድለታችንም ለሙላታችንም ነው፡፡ የሚከብደው የኑሮ ጉዳይ ሳይሆን የሚከብደው ዕድሜ ነው፡፡ ፍላጎታችንን አንድ ባለጠጋ ሊሞላው የሚችል ይሆናል፡፡ ዕድሜን ግን በእርዳታ የምናገኘው ሳይሆን የአምላካችን ጸጋ ነው፡፡ ሳምንቱን ስንጀምር ይህንን ጸሎት መጸለይ ያስፈልገናል፡

«ጌ ሆይ ብዙዎች መኖር እየፈለጉ ይህችን ቀን ሳያዩ አልፈዋል፡፡ ማለፋቸውንም በማለዳ ሰምቻለሁ፡፡ እኔ ግን አኑረኝ ብዬ በመጸለዬ ሳይሆን ኑር ብለህ በመፍቀድህ ለዚህ ደርሻለሁና አመሰግንሃለሁ፡፡ ሳምንቱንም ካንተ ጋር እንዳሳልፈው፣ ያቀድኩት ሳይሆን ያቀድክልኝ እንዲሆን እማፀንሃለሁ፡፡ የማይኖሩበትን ቀን እንደተቀበሉ ሰዎች ሳይሆን ካንተ ጋር ዕድሜአቸውን እንደሚያጣፍጡ ሰዎች አድርገኝ፡፡ የምኖር ያልመሰሉኝ የፈተና ቀኖችን አሳልፌአለሁ፡፡ ኖረኝ ደግሞ ደስ እንዲለኝ እርዳኝ፡፡ ያለኝን ነገር የማከብረው ከእጄ ሳጣው አይሁንብኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ፡- በዚህ ቀን አንተ ቅደም፤ እኔ በጽድቅ በቅዱስ ፍርሃት ልከተልህ፡፡ ሰላምህን በዚህ ቀንና ሳምንት እዘዝልኝ፡፡ አሜን፡»፡
ወንጌላዊው ዮሐንስ፡– «ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች» በማለት ጽፎልናል (ዮሐ. 201)፡፡ ለአይሁዳውያን የሳምንቱ የመጨረሻ ቀን ቅዳሜ ሲሆን የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ደግሞ እሑድ ነው፡፡ ችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ የተነሣባት ዕለተ እሑድ «የጌ  ቀን» ተብላ ክርስቲያኖች ለአምልኮ የሚሰበሰቡባት ቀን ሆናለች (ራእ. 1፡10)፡፡ ዕለተ እሑድ የአምልኮ ቀን የሆነችው ችን ሞትን
ድል ነሥቶ ስለተነሣባት ነው፡፡ ይህች ቀን እግዚአብሔር ፍጥረትን መፍጠር የጀመረባት የዚህ ዓለም ዘመን አንድ ተብሎ መቆጠር የተጀመረባት ቀን ናት፡፡ በዚህች ቀን መፈጠር የጀመረው ዓለም በአዳምጢአት ማርጀትና መውደቅ ደረሰበት፡፡ የፍጥረት ደስም በዚህች ቀን ሆነ፡፡ ዓርብ የተፈጠረው አዳም ዓርብ ዕለት በተሰቀለው ጌታ እንደ ዳነ፤ እሑድ የተጀመረው የፍጥረት ጉዞ፣ በአዲስ ሕይወት እንደገና እሑድ ቀጠለ፡፡
መግደላዊት ማርያም
መግደላዊት ማርያም መጌዶል በሚባለው የትውልድ አገሯ መግደላዊት ማርያም ተብላለች፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማርያሞች ስላሉ መግደላዊት ማርያም በመባል ተለይታ ተጠቅሳለች፡፡ በውስጧላቅ የፍቅር ትን የሚቀጣጠልባት መግደላዊት ማርያም እስከዚህ ቀን ድረስ እንዴትግሣ ተቀመጠች? ስንል ችን የተቀበረው ዓርብ ማታ ነው፡፡ ቅዳሜ እንዳትመጣ የአይሁድ ሰንበት ነው፡፡ በሰንበት ከተወሰነ ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ ስለማይቻል በሕግ ገደብ ተይዛ በጭንቀት ሳትውል አልቀረችም፡፡ ሰንበት ካለፈ በኋላ ግን እሑድ ሌሊት ነጋ አልነጋ እያለች ስትጠባበቅ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብሩ ስፍራ ገሰገሰች፡፡ አይሁዳውያን የሞተ ወዳጃቸውን በሦስተኛው ቀን መቃብሩ ላይ ሽቱ በማርከፍከፍ ለመጨረሻ  ጊዜ ይሰናበቱል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በሕያውነቱ ሽቱን ተቀበለ እንጂ የሙ መሰናበቻ የሆነውን ሽቱ አልተቀበለም፡፡ እርሱ ሕያው ነውና፡፡ መግደላዊት ማርያም የመጨረሻ ሀዘኗን ለመግለጥና ሽቱ ለመቀባት ገና ሳይነጋ ወደ መቃብር ስፍራ ገሰገሰች፡፡
ገና ጨለማ ሳለ
«ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች» (ዮሐ. 20፡1)፡፡ ገና ጨለማ ሳለና ማለዳ ወደ ክርስቶስ መገስገስ ለብዙዎች ጣር ነው፡፡ «ጨለማው እንዳለ ይሁን እኔ ግን ጌታዬን እፈልጋለሁ፣ ጌታዬ ያስፈልገኛል፡፡ ከጨለማው በላይ ያለ እርሱ መኖር ይከብደኛል» የሚሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ጨለማ ከተወገደ በኋላ እንጂ ጨለማው እያለ ሊያመልኩት የተሰናዱ፣ ከጉዳያቸው ይልቅ የተሰቀለው ራሱ ጉዳይ የሆነላቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች በማለዳ ወደ ጌታ መምጣት አይፈልጉም፡፡ ዕድሜአቸውን ከከሰሩ በኋላ የዕድሜአቸውን እንጥፍጣፊ በእግዚአብሔር ቤት ለማሳለፍ የሚያስቡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ብዙ ሞክረው ሲደክማቸው እንጂ ገና በጠዋቱ ለእርዳታ ወደ እርሱ የሚመጡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ክርስቶስ ለብዙዎች አማራጫቸው እንጂ ምርጫቸው አይደለም፡፡ ስለዚህ በክብሩ አያዩትም፡፡
መግደላዊት ማርያም ወደ ክርስቶስ ስትገሰግስ ሴትነቷን የሚፈተኑ ብዙ ነገሮች ነበሩባት፡፡ ጨለማው፣ የመቃብሩ ስፍራ፣ ትልቁ ቋጥኝ ስጋቶቿ ነበሩ፡፡ ሴት ልጅ ጨለማን  ትፈራለች፡፡ እንኳን በጨለማ በብርሃን እንአጥቂ አለባት፡፡ የመቃብር ስፍራም እንኳን በጨለማ በቀንም የማይደፈር ነው፡፡ የከደነው ቋጥኝም በእርሷ ጉልበት የሚገፋ አይደለም፡፡ የማትችለው ነገር ከፊት ለፊቷ ቢታያትም ፍቅር ግን ፍርሃትን አውጥቶ ጥሎላት ወደፊት ገሰገሰች፡፡ ዮሐንስ፡«ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች» (ዮሐ. 20፡1) በማለት ጽፎልናል፡፡ በመንገድ ሳለች ድንጋዩ ትልቅ ስጋቷ እንደነበር ማርቆስ ይገልጣል (ማር. 16፡3)፡፡ በርግጥ ድንጋዩ የተፈነቀለው ጌታ እንዲነሣ አይደለም፡፡ መቃብሩ ባዶ መሆኑን ለማሳየት መልአኩ ፈንቅሎታል፡፡ ጌታ ግን መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ተነሥቷል፡፡
አይሁዳውያን ጌታ እንደሚነሣ እርግጠኞች ነበሩ፡፡ ጠላቶቹ ያመኑትን ትንሣኤ ግን ደቀ መዛሙርቱ አለማመናቸው ይገርማል፡፡ የምናመልከውን አምላክያልነት ጠላቶች የሚያውቁትን ያህል እኛ ብናውቅ ምንኛ በበረ ነበር፡፡ ጠላት አምላካችንን አይደለም፣ እኛን እንኳ አይንቀንም፡፡ የሚያሳድደን ስለፈራን እንጂ ስለናቀን አይደለም፡፡ እነዚህ ጠላቶች ትንሣኤውን ስለፈሩ ተከታታይ የሆኑ ሦስት ጥንቃቄዎችን አደረጉ፡፡ በትልቅ ቋጥኝ መቃብሩን ዘግተው በሮማ መንግሥት ማተም አተሙ፡፡ ይህንን ቢያልፍ ብለው የሚይዙ ልዩ ወታደሮችን ዘብ አድርገው አቆሙ፡፡ ይህን ሁለት አጥር ቢያልፍ ትንሣኤውን የሚያስተባብሉ ወሬኞችን በገንዘብ ደልለው አሰናዱ፡፡ ምን ያህል መሞኘት ይሆን? ሞትን ካሸነፈ ቋጥኝ ይከብደዋል ብሎ ማሰብ ደካማነት ነው፡፡ ኢየሱስ ኤልሻዳይ ግን መቃብሩን ሲጠብቁ ከተማውን አዳረሰ፡፡ እርሱ በየሰዉ ሁሉ ቤት ሞላ፡፡ እነርሱ ግን ባዶ መቃብር ይጠብቁ ነበር፡፡ በገንዘብ የተገዙ የሐሰት ምስክሮችን ቢያሰናዱም በፍቅሩ የተገዙ ደቀ መዛሙርት ለመሥዋዕትነት ጨክነው ለምስክርነት ወጡ፡፡…..
…….ይቀጥላል…..
ረቡኒ
በዲ/ን አሸናፊ መኰንን
የመጀመሪያ እትም ሚያዝያ 2002 ዓ/ም
አድራሻ – 0911 39 35 21/0911 67 82 51
ፖ.ሳ.ቁ. 62552
አ.አ. ኢትዮጵያ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ