መግቢያ » ልዩ ልዩ አንድ » ሰማያዊ ወግ » ሰማያዊ ወግ / 9

የትምህርቱ ርዕስ | ሰማያዊ ወግ / 9

የምእመኑ ድምፅ!

ጌታ ሆይ ! በቀንና በሌሊት ወዳንተ እጮኻለሁ ፣ ዝም ብትለኝ ከቆሙት በታች ፣ ከሞቱት በላይ እሆናለሁ። በነፍስ ግሥጋሴ ወዳንተ እመጣለሁ ። በልቤ አለህ ፣ አንተን አስሳለሁ ። አጠገቤ አለህ፣ ግን እፈልግሃለሁ ። ከእኔ አልራቅህም ፣ ነገር ግን ሀልወትህ ይሠወረኛል ። በሥራህ እየተናገርህ ነው ፣ እኔ ግን በቃል ዝም አለኝ እልሃለሁ ። አንተን በቀንና በሌሊት ፍርርቅ ውስጥ ካላየሁህ በምን ውስጥ አይሃለሁ? እስትንፋሴን ደግፈህ በመያዝህ ካላመሰገንሁህ በምን አመሰግንሃለሁ? በውስጤ እያለህ በደጅ ስፈልግህ እኖራለሁ።

አንተን ጌታዬን በታሪክ ጅረት ውስጥ አላስስህም ። በመዛግብት ውስጥ አልበረብርህም :: በሕይወቴ አደባባይ በፍቅር ፣ በኑሮዬ ዐውድ በበረከት ስትገለጥ አስተውላለሁ ። አያለሁ ፣ ግን አላይም ። እመለከታለሁ ግን አላስተውልም ። በማጣት ውስጥ ማግኘት ሲሰማኝ እርሱ እምነት ነው ። በማግኘት ውስጥ ማጣት ሲሰማኝ ፣ በረከቴን በአፌ ይዤ ራበኝ እያልሁ ሳጉረመርም እርሱ አለማመን ነው ። አማኑኤል ሆይ እንደ ንሥር ክንፍ እጆችህን በመስቀል ላይ የዘረጋኸው አለማመኔን እርዳው ! ወደ እቅፍህ ሰብስበኝ ! ዝናን በተሞላው ስምህ አሜን !

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ተፃፈ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም