የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ሰማያዊ ወግ / 9

የምእመኑ ድምፅ!

ጌታ ሆይ ! በቀንና በሌሊት ወዳንተ እጮኻለሁ ፣ ዝም ብትለኝ ከቆሙት በታች፣ ከሞቱት በላይ እሆናለሁ። በነፍስ ግሥጋሴ ወዳንተ እመጣለሁ ። በልቤ አለህ ፣  አንተን አስሳለሁ :: አጠገቤ አለህ፣ ግን እፈልግሃለሁ። |  ከእኔ አልራቅህም፣ ነገር ግን ሀልወትህ ይሠወረኛል። በሥራህ እየተናገርህ ነው፣  እኔ ግን በቃል ዝም አለኝ እልሃለሁ። አንተን በቀንና በሌሊት ፍርርቅ ውስጥ ካላየሁህ በምን ውስጥ አይሃለሁ?  እስትንፋሴን ደግፈህ በመያዝህ ካላመሰገንሁህ በምን አመሰግንሃለሁ? በውስጤ እያለህ በደጅ ስፈልግህ እኖራለሁ።

አንተን ጌታዬን በታሪክ ጅረት ውስጥ አላስስህም። በመዛግብት ውስጥ አልበረብርህም :: በሕይወቴ አደባባይ በፍቅር፣ በኑሮዬ ዐውድ በበረከት ስትገለጥ አስተውላለሁ። አያለሁ፣ ግን አላይም። እመለከታለሁ ግን አላስተውልም:: በማጣት ውስጥ ማግኘት ሲሰማኝ እርሱ እምነት ነው። በማግኘት ውስጥ ማጣት ሲሰማኝ፣ በረከቴን በአፌ ይዤ ራበኝ እያልሁ ሳጉረመርም እርሱ አለማመን ነው። አማኑኤል ሆይ እንደ ንሥር ክንፍ እጆችህን በመስቀል ላይ የዘረጋኸሁ አለማመኔን እርዳው! በሰላም ሰብስበኝ  አሜን።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ተፃፈ ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ