መግቢያ » ግጥም » ቀን ሳለ ተመለስ

የትምህርቱ ርዕስ | ቀን ሳለ ተመለስ

ቅዳሜ፣ የካቲት 3 2004
መቅረዙ ፈክቶ
የሕይወት በር ተከፍቶ
ህመምህ ርቆ
መቆምህ ፀድቆ
ዳፍንት ሳይመጣ
ቀኑ ሳይሆን ማታ
ድንገት ሳይጨላልም
ዕድሜህ ሳይገደም
ብርሃንህ ሳይያዝ
ጉልበት ሳይደነዝዝ
ቀን ሳለ ተመለስ
ተንደህ ሳትፈርስ
ታግለህ በምትጥለው
ሮጠህ በምትቀድመው
በጉብዝና ወራት
በዘር መዝሪያህ ሰዓት
በደም ክርስቶስ
የታነጽኽው መቅደስ
ቀን ሳለህ የመዳን
ይኽው በእውነት አሁን
ዛሬ ይሁን ልደትህ
ከፈጠረህ ጌታ መታረቂያ ቀንህ
የዛገው ቀለበት ያደፉት ልብሶችህ
የራስህ ባርኔጣ መጫሚያ የእግሮችህ
የተሰባበረው መመርኮዣ ዘንጉ
ይለወጡ ዛሬ ፍፁም ይታደሱ
ተብሎ ስላንተ መዘመርያ ቀኑ
ቀጠሮ የለውም ጊዜው ነው አሁኑ፡፡
                       
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም