ሰኞ፣ ታኅሣሥ 2 2004
አብርሃም ተስፋውን በብዙ ሊቀበል
ብዙ አስርት ዓመታት ፍፁሙን ታግሷል
ሕዝቡን እንዲመራ ቅዱሱ ሲጠራ
ሰማንያ አመታትን ሙሴ ፃድቅ ነብይ በእጁ ተሰራ
የልዑልን መንገድ ጠራጊውን ሊወልድ
ካህኑ ዘካርያስ ብዙ ዘመናት ፀንቷል በአገልግሎት
አብንና እኛን ሊያገለግል ጌታ ሰላሳ ዘመናት ኖሯል በዝምታ
የመሰራት ዘመን ከአገልግሎት በልጦ
የአገልግሎት ዘመን ከመሰራት አንሶ
በፍጹም ማስተዋል ሩጫቸውን ሮጠው
ለእግዚአብሔር መንግሥት መንጋ ምርኮ አብዝተው
የህይወት መምህራን እንዲህ ካስተማሩ
ምንድን ነው ችኮላው ታይቶ መሰወሩ
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
ሳይሰሩም መሮጥ አረም ያስታቅፋል
እናንተ አገልጋዮች ቀድማችሁ ተሰሩ
ሮኆቦት እንዲሆን እንዲሰፋ መከሩ