መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » በዝምታ መልስ አለ ከጌታ

የትምህርቱ ርዕስ | በዝምታ መልስ አለ ከጌታ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ፦ “ይህ ሁሉ ሲደርስብዎትና ይህን ሁሉ ሲባሉ ለምን ዝም ይላሉ? ለምን መልስ አይሰጡም” ቢባሉ፦ “ዝም አላልኩም ለእግዚአብሔር እየተናገርሁ ነው” ብለዋል። ዝም ያሉ ሁሉ ዝም አላሉም ለእግዚአብሔር እየተናገሩ ነው።
በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን አንድ ሹም ተይዘው ሲታሠሩ ሚስታቸው ከአሽከራቸው ጋር ኑሮ ጀመረች። ዐፄ ቴዎድሮስም ይህን ሰው አስደፈርኩት ብለው አዘኑ። ጠርተውም፦ “የሆነውን ሁሉ ሰማሁ ሚስትህንና አሽከርህን እንድቀጣቸው ፍቀድልኝ ደግሞስ ሰምተህ ለምን አልነገርከኝም?” ቢሏቸው “ለትልቅ ሰው ነግሬአለሁ” አሉ።  
ዐፄ ቴዎድሮስም ተበሳጭተው “አሁንም ትዕቢትህ አለቀቀህም? ከእኔ በላይ ትልቅ ሰው አለ ወይ?” ቢሏቸው “ለትልቅ ሰው ለመድኃኔዓለም ነግሬአለሁ” አሏቸው። 
ንጉሡም፦ “ትልቅ ሰው አልከው” ብለው ተገረሙ። 
በሦስተኛው ቀን አሽከርየውና ሚስትዬው ሲዝናኑ መብረቅ ወድቆ ገደላቸው። 
ንጉሡም ሰምተው እኒያን ተገፊ ጠርተው፦ “በል ወንድሜ ለትልቅ ሰው እያሳበቅህ እኔንም ሳታስገድለኝ ውጣልኝ” ብለው ከእስር ፈቷቸው።
 ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሰሜን ትልቅ ሰው መድኃኔዓለም ያውቃል ይባላል።
ለሰው ዝም ያሉ ለእግዚአብሔር እየተናገሩ ነው። ለሰው ቢናገሩት ይታዘባል፣ ይፈርዳል። እግዚአብሔር ግን በቅን ይፈርዳል።
ጌታችን የእውነት ሁሉ ማሰሪያ፣ ራሱም እውነት የሆነው አማኑኤል በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ ዝም አለ። በግ ከአካሉ ሲሰረቅ ለምን እንደማይል ጌታም ልብሱን ክብሩን ሲገፉት ይግባኝ አልጠየቀም። ስለሚባለውም መልስ አልሰጠም። በክርክር የበላይ ሆኖ ማሸነፍም አልፈለገም። ገዢው እስኪደነቅ ዝም አለ። በመስቀል ላይ ግን በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በሰው ፊት ዝም አለ፣ በአባቱ ፊት ጮኸ። ውጤቱ ትንሣኤ ነው።
እኛ በተቃራኒው ነን። በሰው ፊት እንጮሃለን፣ በእግዚአብሔር ፊት ዝም እንላለን። ስለራሳችን እንድናስረዳ አልተላክንም። መከላከያ እንድናቀርብም አልተጠራንም። ዝም ስንል እግዚአብሔር መልስ ይሰጣል።
 በዝምታ መልስ አለ ከጌታ!!!
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም