በዓለም የነበረ፣ በዓለም ያልታወቀ
ወገን ሳለ በወገን ፣ የተቸነከረ
ማስገደድ በሌለው ግሩም ትሕትና
ፈቅዶ ለሚቀበል የዝንትዓለም ፋና
ብርሃን ዘእምብርሃን
ጥበብ ለየዋሃን
በስሙ ለሚያምኑ
ልጅ ማድረግ ሥልጣኑ
አማናዊ ብርሃን ፣ ፋኖስ የማይጠፋ
ክርስቶስ ኢየሱስ ፣ የዘላለም ተስፋ
copyright @ 2024 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
የዚህ ገጽ ዓላማ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ማስተላለፍ፣ ትውልድን በእግዚአብሔር ቃል ማነጽና የተሻለ ዘመንን መናፈቅ ነው።