የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ትንሽ ነኝ! አትበል

            
                            ሰኞ፣ የካቲት 26 2004
ከትልቁ ቤተ መቅደስ
በአገልግሎቷ ሳታንስ
ከብራ በቅድስና ረብቦባት መንፈሱ
ነፍሳት ለዘወትር እንደውሀ ሲፈሱ
በንስሐ ለቅሶ ከለመዱት ኃጢአት ልባቸው ተሰዶ
ልብሳቸውን በማቅ ተክተው በአመድ                                
ከምህረቱ ምንጭ ተቃጥለው በጥማት
ሲሹ ፍለጋውን በትንሿ ምኩራብ
ሁሌ መልስ አላቸው ከሰማዩ አምላክ
ምኩራብ አካልህን ስትቀድስ ለጌታ
መስዋዕት ልታቀርብ በአርምሞ በእልልታ
የክፋትን አፀድ የመርገምን መንገድ
የሞትን መሰውያ የኃጢአትን ህንፃ የጣዖትን ገበታ
ደርምሰህ ልትንድ ደምስሰህ ልትሽር
የመርገምን ተክል አጥፍተህ ልትነቅል
ትንሽ ነኝ! አትበል
                   ምንም የማልረባ
ስጋህን ቀድሰህ ሥራ ልትሠራ
ትንሽ ነኝ! አትበል
                 አንደበቴ ያልቀና
አረ አይሆንም ከቶ አልበቃሁም ገና
ልትሠራ ልትተክል ጽድቅን ልትመሰክር
ትንሽ ነኝ! አትበል
በትንሿ ምኩራብ ብዙ ጸሎት ሰምሯል
ባንተ በትንሹ ብዙ ሊሰራብህ
የተቆረጠ ሀሳብ ከፈጣሪህ ወጥቷል፡፡
 
 
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ