መግቢያ » ግጥም » ነፍሴ አንተን ብቻ

የትምህርቱ ርዕስ | ነፍሴ አንተን ብቻ

ወንድሜን አሳዳጅ ቃኤላዊ እብደቴ
ጥርጥር የሚነዳው ዲዲሞስነቴ
ኬፋዊ ግርግር ችኩል የሚነዳው
ሄሮድሳዊ መርገም የህፃን ደም የሚጥመው
ሳኦላዊ ስሜት አሳዳጅነቴ
አጋርን ሚገፋ ሳራ ሰውነቴ

ያዕቆብን የሚጠላ ኤዶማዊነቴ
ማስታረቅ የማይችል ርብቃ ማህጸኔን
አለምን ናፋቂ ዴማሳዊ ህይወቴን
ከጠወለገ ገጽ ኤማውሳዊ ተጓዥ
ለሀገር ከማይረባ ከኤካቦድ አርጋዥ
አልጋ ሲሉት ቀጋ ከይሁዳዊ ሩጫ
እረፍት ከጠፋበት ከሌለው ማምለጫ
ጠብቀው ባርያህን ስራኝ ላንተ ፈቃድ
ነፍሴ አንተን ብቻ ለዘላለም ትውደድ።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም