የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ንስሐውም ይሁን…

                                          ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 2004
ለአደባባይ ኃጢአት
ሌላም በደለ በሚገድል ስህተት
ትውልድ ለሚሻገር ለያቆም ግድፈት
እልፍ ላሰናከለ
በጥቂት ፅድቅ ለታጀለ
የነፍሶች ሕሊናን ወግቶ ላቆሰለ

በክፋት ፍላፃ አልሞ በገሀድ
ሁሉን አሳድሞ ወደራሱ መንገድ
አስጨፍሮ አስኮብልሎ
በጉቦ ቃል ፍትሕ ረግጦ
ጦር አንግ ሰላም ጠልቶ
እንዲህ ኖሮ ኖሮ ተመልሻለሁ ሲል
ባይቸኩል ምናለ ከንቱ ለማገልገል
ምነው እንደ ኃጢአት ምነው እንደነውሩ
ንስው ይቅርታው ቢተርፍ ለሀገሩ
ኃጢአቱ በገሐድ ከተሰራ ባዋጅ
ትውልድ እንድንፈውስ ዘመኑን እንድንዋጅ
ንስሐውም ይሁን በየአደባባዩ
በቀል ቂሙ ጠፍቶ
ይቅርታው ጎምርቶ
አንድ ሆነን ስንዘምር መቅደሱ ተሞልቶ
ያላመነው እንዲያምን
 ያመነው እንዲጸና በይወት ተሰብኮ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ