ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 2004
ለአደባባይ ኃጢአት
ሌላም ለበደለ በሚገድል ስህተት
ትውልድ ለሚሻገር ለማያቆም ግድፈት
እልፍ ላሰናከለ
በጥቂት ፅድቅ ለታጀለ
የነፍሶች ሕሊናን ወግቶ ላቆሰለ
በክፋት ፍላፃ አልሞ በገሀድ
ሁሉን አሳድሞ ወደራሱ መንገድ
አስጨፍሮ አስኮብልሎ
በጉቦ ቃል ፍትሕ ረግጦ
ጦር አንግሦ ሰላም ጠልቶ
እንዲህ ኖሮ ኖሮ ተመልሻለሁ ሲል
ባይቸኩል ምናለ ከንቱ ለማገልገል
ምነው እንደ ኃጢአት ምነው እንደነውሩ
ንስሐው ይቅርታው ቢተርፍ ለሀገሩ
ኃጢአቱ በገሐድ ከተሰራ ባዋጅ
ትውልድ እንድንፈውስ ዘመኑን እንድንዋጅ
ንስሐውም ይሁን በየአደባባዩ
በቀል ቂሙ ጠፍቶ
ይቅርታው ጎምርቶ
አንድ ሆነን ስንዘምር መቅደሱ ተሞልቶ
ያላመነው እንዲያምን
ያመነው እንዲጸና በሕይወት ተሰብኮ