የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

አሳይተህ ወግድ

መንገዱን የምታጠራ
ሰርጓጉጡን የምታፀዳ
ተራራውን የምትደላድል
ሸለቆውም ይሞላ የምትል
አሳልፍ እንጂ መንገዱን አትዝጋ
ሰዎች ይመልከቱት ያን አልፋ ኦሜጋ።
ኮልኩለህ በዙርያህ ተከበህ በአንቱታ
የድምፅህን ነገር የስብከትህን ለዛ
 የምትደሰኩረው የምትለፈልፈው
በተሰጠህ ፀጋ ታብየህ ከፍ ያልከው 

አንተ ላትገባ በሩን የምትዘጋው
እልፍ በል ወደዚያ አጥራና መንገዱን
አሳይተህ ወግድ ይለፍ አማንያን
በወንጌል አላማ
በመስቀል ከተማ
የጫማውን ጠፈር እኔ እንኳ አልፈታ
የእኔም የእናንተም እርሱ ነው አለቃ
እርሱን ተመልከቱት ትሑቱን መምህር
እኔ ታናሽ ነገር የቃሉ ምስክር
እርሱ ይገባዋል ከኔ ይልቅ ሊከብር
ብለህ አመልክት እንጂ የተላክህበትን
ሂዱ ወደጌታ በል የከበቡህን
የተዘራው እርሻ ፍሬ እንዲያፈራ
ጠብቀው ልብህን እግዚአብሔርን ፍራ
በትንሹ ፀጋ ደርሰህ ሳትመካ
ለባለ መክሊቱ አትርፈህ አስረክብ ለሠራዊት ጌታ

ያጋሩ