የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

አስበን

በጸናው የምስጋና ርስትህ ፣

በማይደፈረው ግዛትህ ፣

በማይናወጸው ዙፋንህ ፣

በማይለያየው አንድነትህ ፣

በማይጠቀለለው ሦስትነትህ ፣

በማይሰጋው መንግሥትህ ፣

በማይታበለው ቃልህ ፣

በማያማክሩት ጥበብህ ፣

በማይመረመር ማስተዋልህ ፣

በማያበድሩት እውቀትህ ፣

በማይፈርስ ምክርህ ፣

በማይክደው አባትነትህ ፣

በማይቀየመው አፍቃሪነትህ ፣

በማይሰለቸው ቸርነትህ ፣

በማይገፋው ጥላህ ፣

በማያባርረው ማደሪያህ ፣

በማይዘናጋው ጥበቃህ ፣

በማይጠገበው ጣዕምህ ፣

በማይሻረው ፍርድህ ፣

በማይጨክነው ርኅራኄህ ፣

በማይጥለው ትዕግሥትህ ፣

በማይካደው ጻድቅነትህ ፣

በማያልፈው ስጦታህ ፣

በማይነጥፈው እጅህ ፣

በማይዝለው ትከሻህ ፣

በማያባራው ምስጋናህ ፣

በማይተካው ጌትነትህ ፣

በማይሰረቀው አምልኮህ ፣

በማይሞተው ሕያውነትህ ፣

በማይገሠሥ ሥልጣንህ ፣

በማያልፍ ዓይንህ ፣

በማያፈስስ ጆሮህ ፣

በማይሰበር ምክርህ ፣

በማይነገር ሐሤትህ ፣

በማይሸነፍ መድኃኒትህ ፣

በማይደመሰስ መሐላህ ፣

በማይቀር ኪዳንህ ፣

በማይከዳ ወዳጅነትህ ፣

በማይረሳ ወንድምነትህ ፣

በማያጋልጥ እናትነትህ ፣

በማይታዘብ አበ ነፍስነትህ

አቤቱ አሁን አስበን !!!
የነግህ ምስጋና /15
መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም.
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

ያጋሩ