የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

…ስብከት አራት /ካለፈው የቀጠለ/

11.     ልክ የሌለውና ከቃላት በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ጥበብ ግዙፍርና ያማረ የየራሳቸው አካል ያላቸውን ፍጥረታት በቃዱ ፈጠረ። እንደ ቃዱ የሚያደርገው ይህ አምላክ በማይነገር ስጦታው ፣ ከአእምሮ በላይ በሆነው በጎነቱ ራን ወስኖ ከሥጋችን ጋር ዋሕዷልማይታየው ይታይ ዘንድ ፣ የማይዳሰሰው ይዳሰስ ዘንድ ነፍሳቸው የታደሰ ሰዎችም መልካምነቱን ይቀምና ዘለዓለማዊውን ብርሃን በእውነት ያጣጥሙ ዘንድ እንደየችሎታቸው መጠን ቅዱስና ታማኝ ለሆኑ ለሚገባቸው ነፍሳት ራሱን ይገልጽላቸዋል ። እሱ ሲፈቅድ እሳት ይሆንና ነፍስ ውስጥ ያሉትን የኃጢአት ሳቦች ያቃጥላል አምላካችን፡- “በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነው” (ዕብ 12፥29፤ ዘዳ 4፥24) ። ሲፈቅድ ከቃላት በላይ የሆነ ረፍት ይሆናል በዚህም ነፍስ በእርሱ እፎይ ትላለች ። ሲፈቅድ ሐሤትና ሰላም ይሆናል ይበዛልምይትረፈረፋልም
12.  በእውነት ፍጡራኑን ለማስደሰት ከፍጥረቱ እንደ አንዱ መሆን ከፈለገ ይሆናል ለምሳሌ የብርሃን ከተማ እንደ ሆነው እንደ የሩሳሌም ወይም እንደ ሰማያዊቷ ዮን መሆን ይችላል መጽሐፍ እንዲህ ይላል፡- “ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም” (ዕብ 12፥22) ። ለእርሱ ሁሉም ነገር ቀላል ነው  ለታማኝ ነፍሶች ደስታ ራሱን ወደ ፈለገው ዓይነት ቅርጽ መቀየር ይችላል ። ሰው የእርሱ ጓደኛ ለመሆንና እርሱን ለማስደሰት ብቻ ይጣር እንጂ “ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው” የተባሉትን ሰማያዊ የሆኑ መልካም ነገሮችንከቃላት በላይ የሆኑ ደስታዎችንና መስፈሪያ የሌላቸውን መለኮታዊ ሀብቶችን በእውነት ይካፈላል ። የጌታ መንፈስም ለተገቡ ነፍሶች ራሱ ረፍታቸውደስታቸውና ዘላለማዊ ይወታቸው ይሆናል ። ጌታ በሥጋና በጽዋውም ራሱን ይገልጻል በወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና ፡- “ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል” (ዮሐ 6፥58) ። ነፍስን ከመታሰብ በላይ የሆነውን ረፍትና በመንፈሳዊ ደስታ ይሞላት ዘንድ እሱ እንዲህ አለ፡-  “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” (ዮሐ 6፥35)። እሱ ራሱን  በሰማያዊው ምንጭ እንዲህ ሲል ይገልፃል፡- “እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል” (ዮሐ 4፥14) “ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና ። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል” (1ኛ ቆሮ 10፥4፤  12፥13) ።
13.  ለሁሉም ቅዱሳን አባቶች እርሱ በፈለገውና ለእነርሱ ምርጥ በሆነው መልኩ ተገለጸላቸው ለአብርሃምለይስሐቅለያዕቆብለኖኅ ፣ ለዳንኤልለዳዊትለሰሎሞንለኢሳይያስና ለሁሉም ነያት በተለያየ መንገድ ተገለጸላቸው ። እኔ እንደማምነው ሙሴ በዚያ ተራራ ላይ በየሰዓቱ ወደ ጠረጴዛው ተጋብዟል በዚያም ልን አክብሯል ሐሤትንም አድርጓል ሁሉንም ቅዱሳን ረፍትና ድኅነትን ሊሰጣቸው ወደ መለኮታዊም እውቀትም ሊመራቸው እንደ ፈቀደው ሆኖ ተገልጾላቸዋል ። እሱ የመረጠው ነገር ሁሉ ለእርሱ ቀላል ነው ። እርሱ እንደ ፈቀደ ራሱን ወስኖ ይገልጻል የሚያፈቅሩትም በዓይናቸው እንዲያዩትለሚገባቸውም ራሱን ከአእምሮ በላይ በሆነው የክብር ብርሃንታላቅ በሆነው ፍቅሩና ይሉ ይገለጽላቸዋል ። በታላቅ ፍላጎት እግዚአብሔርን ለመቀበል የታደለች ነፍስ በእምነትና በፍቅር እግዚአብሔርን የምትጠብቅ ሰማያዊውንም የመንፈስ ፍቅርና ሰማያዊውን የዘላለም ያውነት የተቀበለች ነፍስ ከሁሉም ከዓለማዊ ምኞቶች ትላቀቃለች ከሁሉም የክፋት ባርነቶችም ነትወጣለች
14.  ብረትእርሳስወርቅ ወይም ብር እሳት ውስጥ ሲጨሩ እንደሚቃጠሉ ከነበራቸውም ተፈጥሮአዊ ጥንካሬ እንደሚለሰልሱ በእሳት ውስጥ በቆዩ መጠንም ይበልጥ እየቀለጡ እንደሚሄዱ የነበራቸውም ጠንካራ ባሕርይ በጋለው እሳትይል እንደሚቀየር ዓለምን የካደችና ፍላጎቷን ጌታ ላይ ብቻ  ያደረገች ነፍስ በብዙ ፍለጋ ፣ ሕመምና ሁከት ውስጥ እሱን በእምነትና ተስፋ ያለ ማረጥ ትጠብቃለች ሰማያዊውንም እሳትና የመንፈስን ፍቅር የተቀበለች ነፍስ ከሁሉም ዓለማዊ ምኞቶች ትላቀቃለች ።ከክፉ ምኞትም ነፃ ትወጣለች። ነፍስ የማያልቅ የማይጠፋ ፍቅር ካለው ከሰማያዊው ሙሽራ አን ለምዳው የነበረውን የኃጢአት ደስታና ሁሉ ነገሮች እንደ ጉዳት ትቆጥራቸዋለች
15.  በእውነት እንዲህ ዓነት ነፍስ ያላቸው በጣም ተወዳጅ የሆኑ ወንድሞች (ነፍስን) ይህን መለኮታዊ ፍቅር ከከለከሏት ፍቅር ከእነርሱ ይሸሻል ይህም ፍቅር የነፍስ ሕይወትና ረፍት ከቃላትበላይ የሆነ ከሰማያዊው ንጉሥ ጋር የሚኖር ምሥጢራዊብረት ነው ። የምድራዊው ፍቅር ብረት (ትዳር) ከአባትእናትወንድምና እህት ይለያል ። በዚህ ዓይነት ግንኙነትም ሁሉም ነገር እንደ ውጫዊ ነገር ይታሰባል ካገቡም በኋላም ቢሆን እነዚህ ያገቡ ሰዎች ቤተሰባቸውን ይወዳሉ ር ግን ከትዳር አጋራቸው ጋር እንዳለው መውደድ ሳይሆን ከዚያ ውጪ በሆነ በተለየ መውደድ ነው  ሚወዷቸው ። ወንድ ለሁሉም ነገር ያለው እይታ ከሚስቱ ጋር ባለው ግንኙነት ይወሰናል በዚህም ምክንያት መጽሐፍ እንዲህ ይላል፡- “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ፥ በሚስቱም ይጣበቃል ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” (ዘፍ.2:24) ይህ ሥጋዊ ፍቅር ከሌሎች የፍቅር ዓይነቶች እንድንለይ የሚያደርገን ከሆነ በእውነት ሰማያዊና ተወዳጅ ወደ ሆነው ወደ መንፈስ ቅዱስ የፍቅር ብረት የገቡት እንዴት አብዝተው ከዓለማዊ ፍቅር አይለዩም ? እነርሱም ሁሉንም ነገር ችላ ይሉታል እነርሱንም አንዳች የሚስባቸው ነገር የለም ምክንያቱም እነርሱ በሰማያዊው ናፍቆት ድል ስለ ተነና ከሰማያዊ ናፍቆት ጋር ሙሉ በሙሉ  ብረት ስላደረጉ ነው
16.  እንግዲህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እንዲህ ዓይነት መልካም ነገሮች ከፊታችን ካሉልን እንዲህ ያለም ታላቅ ቃል ኪዳን ከጌታ ከተገባልን እሱን እንዳናገኝ የሚያደርጉንን እንቅፋቶች ነቅለን እንጣል የዓለምንም ፍቅር እንካድ ያንን መልካም ነገር በመፈለግና በመናፈቅ ራሳችንን ለጌታ እንስጥ። በዚህም ቅዱስ ጳውሎስ፡- “ፍቅርን ተከታተሉ” (1ኛቆሮ 14፥1) ብሎ እንድንከተለው የተናገረለትን ከመናገር በላይ የሆነውን የመንፈስ ፍቅር እንድናገኝ ከግትርነታችንም በገናናው ቀኝ እጅ ተለውጠን ወደ መንፈሳዊ ግለትና ረፍት ለመድረስ መለኮታዊ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እንሸነፍ። እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ መመለሳችንንና ከእርሱ በተቃራኒ ካሉ ነገሮች ነመውጣታችንን በተፋ ስለሚብቅ ለሰው ልጆች ቸር ነው ። ምንም እንኳን እኛ ታላቅ በሆነው ጭፍንነታችንበአላዋቂነታችንና ይወትን ትተን ለክፉው መንገድ ባለን ዝንባሌ በመንገዳችን ላይም ብዙ እንቅፋቶችን በማስቀመጣችንንስለመግባት ባንወድም እርሱ አሁንም ትተኛ ነው እርሱ ስለ እኛ ይራራል ንስገብተንወደ እርሱ እንድንመለስ በተስፋ ይጠብቀናል በውስጥ ባለው ሰውነታችን /በውስጣዊ ማንነታችን መንፈሳዊ አብርሆትን አግኝተን በፍርድ ቀን እንዳናፍር ይሻል
17.  ጸጋን መለማመድ ከባድ ስለሆነና ከዚህም በላይ ሳይታወቅ ውስጥ ውስጡን የሚራ የጠላት ምክር ስላለ ይህ ነገር አስቸጋሪ ከመሰላችሁ ይህን አስተውሉ እግዚአብሔር እየራራእያዘነና ድካማችንን እየተሸከመ መቀየራችንን እየጠበቀ ነው። ኃጢአት ስንራም ንስእንደምንገባ በመጠበቅ እጁን ይዘረጋልና፤ ነዩም እንዳለው፡- “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን? (ኤር 8፥4)። ስንወቅም እኛን መልሶ ለማንት አያፍርብንም ። እኛ መልካም ፍላጎት እንዳለን በማስተዋል ብቻ እንሁን ፤ ከእርሱ እገዛ ለማግኘት እንለወጥና እንሻ። እሱ ሁል ጊዜ ሊያድነን ፈቃደኛዝግጁ ነው ። እርሱ የእኛን ወደ እርሱ መመለስ ከልብ በሆነ ስሜት ይጠብቃል ባለን አቅም ሁሉ ከመልካም ላማም ከሚመነጭ ምነትና ቅናት የጥረታችን ሁሉ መሳካት እርሱ በእኛ የሚራው ራ ነው። ስለዚህ የተወደዳችሁ እንደ እግዚአብሔር ልጆች ክፉ አሳግድ የለሽነትንና ስንፍናን አስወግደን ደፋር ለመሆንና እሱን ለመከተል እንጣር ። ከሥጋ መቼ እንደምንለይ አናውቅምና ኃጢአት እንዴት እየጎዳን እንደሆነ ሳንገነዘብ በየቀኑ አናስወግደው ።  ለክርስያኖች የተሰጠው ተስፋ እጅግ ታላቅና ከመናገር በላይ የሆነ ነው። የሰማይና የምድር ክብርና ውበትየትኛውም ዓይነት ጌጥና አማራጮች ፤ የሚታየውም ነገር ክብርአስደሳችነትመልካምነትና ብልጽግና ከአንድ ነፍስ ተፋና ክብር ጋር አይነጻጸርም
18.  ይህ ከሆነ እንዴት ነው የጌታን ተፋና ማሳመኛ የማንቀበለው ? ራሳችንን ለእርሱ ሰጥተን ወንጌልም “የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ”(ሉቃ 14፥26) እንደሚለው ራሳችንን ክደን ሌላውን ትተን እርሱን ብቻ የማናፈቅረው እንዴት ነው ? ነገር ግን ከእነዚህ ነገሮችና  ከተሰጠን ከታላቁ ክብር  ከአዳም ጀምሮ ለአባቶችና ለነቢያት ከጌታ የተሰጣቸውን ቃልኪዳን ትተን ታላቁ ጌታ ምን ያል ታላላቅ ተፋዎችምን ያመተማመኛዎችና ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዴት የሚደንቅ ርኅራኄ እንዳሳየን እስኪ እናድንቅ በመጨረሻም በራሱ መምጣት ለእኛ ያለውን ከቃላት በላይ የሆነ ደግነቱን በመቀል ላይ በመሰቀል እኛን ወደ ይወት ጎዳና በመመለስ አሳየን ። ስለዚህ እኛም ወደ ራሳችን ፍላጎቶችወደ ዓለም ፍቅርወደ ራሳችን ዝንባሌና ልምድ ዳግም አንሄድም ። እኛ ምነት የለሾች አያም ጥቂት እምነት ያለን እንደሆን ይወታችን ይመሰክራል። ሆኖም ግን እርሱ አሁንም ለእኛ መልካም እንደሆነ ቀጥሏል። በሚታየው መልኩ እንደ ክፋታችን ለኃጢአት ለዘላለም አሳልፎ ሳይሰጠን በዚህ ዓለምም ማታለል እንዳንጠፋ እየተንከባከና እየጠበቀ ታላቅ በሆነው መልካምነቱም የምንመለስበትን ሰዓት በትዕግሥት ይጠብቃል
19.  እኛ ከንቱ ከሆኑት ሳቦቻችን ጋር ተጣብቀን ፍላጎታችንንም እየተከተልን “ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?”(ሮሜ. 2:4) የሚለው የሐዋርያው ቃል እንዳይፈጸምብን እሰጋለሁ። ነገር ግን እንደ እርሱ ተስፋመልካምነትና ትዕግሥት መጠን ካልተመለስን በፋንታውም ኃጢአትን ከጨመርን በቸልተኝነታችንና በግድ የለሽነታችን ለራሳችን ተጨማሪ ፍርድንና ቁጣን እናከማቻለን እንዲህ የሚለው ቃልም ይፈጸምብናል፡- “ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ /ሮሜ.2:5/ እግዚአብሔር ከሰው ጋር ባለው ግንኙነት እጅግ ታላቅና ከቃላት በላይ የሆነ  መልካምነትን አሳይቷል ፤ ከመጠን በላይ የሆነ ተስፋም ሰጥቷል እኛም ራሳችንን ለመቀየር ወደ እርሱም ሙሉ በሙሉ ለመመለስ ከጣርን ብቻ ድነትን እናገኛለን
 
20. የእግዚአብሔርን ትዕግሥትና ታላቅ የሆነውን መልካምነቱን ማወቅ ከፈለጋችሁ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንማር። አባቶች ከእነርሱ የሆኑትንቃል ኪዳንም የተሰጣቸውንከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ የመጣውንኪዳንና የመቅደስ ርዓት ለእነርሱ የሆነውን እስራኤልን ተመልከቱ (ሮሜ 9፥5) እስራኤል ብዙ ኃጢአት ርተዋል እግዚአብሔርም ብዙ ጊዜ ገሸሽ ብለዋል ሆኖም ግን እርሱ ከቶ አልተዋውም ነገር ግን ለራሳቸው ጥቅም ብዙ ጊዜ ቀጥቷቸዋል ። ልባቸውን ሊያለሰልስ ወዶ መቅሰፍትን ልኮባቸዋል ፤ አጽናንቶአቸዋል ። አበረታቸዋል ያትንም ልኮላቸዋል። እነርሱ ብዙ ኃጢአት ርተዋል ብዙ በደልም በድለውታል ። እርሱ ግን ትተኛ ነበርና ሲመለሱም በደስታ ተቀበላቸው። ደግመው ከመንገዱ ሲወጡ አይተዋቸውም በነያቱ ለንስይጠራቸነበር። እነርሱም በተደጋጋሚ ከመንገዱ እየወጡና እየተመለሱ ሲኖሩ መልካም ሆኖ ይቀበላቸውና በእርጋታ ያኖራቸው ነበር ። በመጨረሻ ከሁሉ በላይ በሆነው መተላለፍ ወደቁ ። ይህም መተላለፍ የአባቶችና የነያት ትውፊት ነአውጪአቸውና አዳኛቸውንጉቸውና ነያቸው ብሎ ባስተማራቸው በጌታቸው ላይ እጃቸውን  ማንታቸው ነው ሥጋ ሲመጣ አልተቀበሉትም በተቃራኒው ክብረ ነክ በሆነ መንገድ ተቀብለውት በመጨረሻ መስቀል ላይ ሰቀሉት በዚህ ታላቅ ጥቃት ይህ የላቀ በደል ኃጢአታቸው ከልክ በላይ ሆነና ሞላ በዚህም ለምኞታቸተላልፈው ተሰጡ መንፈስ ቅዱስም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከተቀደደበት ጊዜ አንቶ ተለያቸው ። በዚህም ቤተ መቅደሳቸው ጌታ፡- “ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም ”  (ማቴ 24፥2) ባለው የነቀፋ ቃል መሠረት ለጠላቶች ተላልፎ ተሰጠ ። ፈረሰ ባዶም ሆነ ። በዚህ ሁኔታ በጠላቶቻቸው እጅ ተላልፈው ተሰጡ ቅኝ በገዛቸው ንጉም በዓለም ዙሪያ ተበተኑ ወደ ሀገራቸውም ድጋሜ እንዳይመለሱ ተከለከሉ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ