የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

እግሬን ፈውስልኝ

                                                      አርብ፣ ጥቅምት 24 2004
ጎዳናው ሰፍቶብኝ መንገዱ በዝቶብኝ፣
የእግሮቼ አድራሻ መድረሻው ጠፍቶብኝ፣
ባገኘሁት ስዘልቅ በወደድሁት ስሮጥ፣
እግሮቼ መርተውኝ እዚም እዛም ስረግጥ፣
በአዘቅት በገደሉ በረግረጉ ስሰምጥ፣
ፍለጋህን ትቼ የእኔን መንገድ ስመርጥ፣
አንተ ግን ኢየሱስ፣
አይተህ አዝነህልኝ ደርሰህ ቆመህልኝ፣
በረግርግ ያለውን እግሬን አድንልኝ፣
ወጥመድ ይዞብኛል እባክህ ፍታልኝ፣
ጋሬጣ ወግቶብኛል እስኪ ፈውስልኝ፣
መንገድ ስቶብኛል የአንተን አሳይልኝ፣
ወደ ዓለም ኮብልሏል ወደ አንተ አቅናልኝ፡፡
ጉንድሽ ሆኖብኛል ሙሉ አድርግልኝ፣
አነክሶብኛል ዳሰህ አዘልልልኝ፣
በአንተ ዱካ ላይ ዳግም አራምድልኝ፣
ጉዞዬን እንድዘልቅ እግሬን ፈውስልኝ፡፡
ክርስቶስ ጌታ ሆይ ዛሬም ለዘላለም፣
የሄድክበት ሄጄ የቆምክበት እንድቆም፣
ስታርፍም አርፌ በሀገርህ እንድከትም፣
መንገድ መሪ ሆነህ ከፊት ለፊት ቅደም፡፡                                                                                                       
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ