የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ኪዳን አለኝ እኔ

              ሰኞ ታኅሣሥ 9 2004
ንፋሱን ቀስቅሰው
ሞገዱን አናውጠው
ቀስትህን ገትረው
ሰይፍህን ሰይፈው
አሹለው ጥርስህን
ከስክሰው ፊትህን
ግንባርህን ቋጥረው
ቁጣህን ተቆጣው

ጩኸትህን ጩኸው
ጭፍራህን ቀስቅሰው
ወድረው ጦርህን
ዘርጋው ወጥመድህን
ጉድጓዱንም አስፋው
ጅራፍህን ግመደው
የቤቴን ምሰሶ አብዝተህ ነቅንቀው
ከፊቴ ያለውን ሁሉንም ውሰደው
እንዲህ ተግዳሮትህ ገንፍሎ ሲወጣ
ብዙ ይጠቅመኛል በነፍሴ ልሠራ
ይደንቀኛል ክንዱ የጌታ ፈቃዱ
ሰልፉን ለእጆቼ ሲያሳይ በጥበቡ
ካንተ ሺህ ተግዳሮት ብዙ ዘመን ቀድሞ
ኪዳን አለኝ እኔ
ንፋስህ ላይነቅለው ጎርፍህም ላይነካው የእኔን ቤት ፈጽሞ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ