የማስተዋል ጥጉ የጥበብ ከፍታ
የዕውቀት ልቀቱ ፅንፉ የይቅርታ
አንተን ማወቅ አንተን መኖር
ባንተ ታውቆ በረት ማደር
በትሕትና ለዓይን አንሶ
በሕይወት መግዘፍ ፍቅርን ለብሶ
በእሳት መሐል እንዳለ ወርቅ
በመቃጠል እንደሚደምቅ
ክርስትና
ትሕትና
የክርስቶስ ልብን መውረስ
በምድር ሆኖ ሰማይ መድረስ
copyright @ 2024 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
የዚህ ገጽ ዓላማ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን ማስተላለፍ፣ ትውልድን በእግዚአብሔር ቃል ማነጽና የተሻለ ዘመንን መናፈቅ ነው።