የትምህርቱ ርዕስ | ወዳጄ ሆይ

ወዳጄ ሆይ
ይህች ዓለም ለስላሳ እባቦችና የሚያገሱ አንበሶች ያሉባት ዓለም ናት የእባብ ልስላሴ ያዘናጋል ቀጥሎ ግን ሞትን ይጋብዛል የአንበሳ ድምፅ ግን ያስደነግጣል ለመጠንቀቅም ግን ይረዳል ከእባብ ልስላሴ የአንበሳ ግሳት ይሻላል ጻድቅ የሚመስሉ ክፉዎችና ኀጥእ የሚመስሉ እውነተኞች በዓለም ላይ አሉ ጭምቶች ውስጣቸው ባቢሎን ነው አንገት ደፊዎች የማያውቁት ነገር የለም ዝምተኞች የተናገሩ ቀን ቃላቸው መራራ ነው ከአልችልም ባይነትና ከፍርሃት የምትላቀቀው ያለማቋረጥ በመለማመድ ብቻ ነው ዓለሙ ያንተ ነውና ሰይጣን ይፍራህ እንጂ አንተ ሰይጣንን አትፍራው ተጠሪነትህ ለኅሊናህ ከሆነ የምትፈራው ሕግ የለም በጎ መሥራት ራስን የማክበር ውጤት ነው እውነት መናገርም ሰሚን ማክበር ነው
ወዳጄ ሆይ
ድራማ ከእውነቱ ኑሮ ይልቅ ቢያምርም ያልቃል ሐሰትና ሽንገላም ሁልጊዜ አያበላም ሳታስብ የምትናገረው ነገር እውነት ብቻ ነው ውሸት ድሪቶ በመሆኗ መልኳ ብዙ ነው መንፈሳዊነት አንገትን ሳይሆን ልብን በመስበር የሚገለጥ ነው በተሰበሩ አንገቶች ውስጥ የቆሙ ብዙ ልቦች እንዳሉ እግዚአብሔር ያውቃል ጉልበትን ሳይሆን ምኞትን ማሸብረክ እርሱ እውነተኛ አምልኮ ነው የላዩ የውስጡ መግለጫ ሲሆን እግዚአብሔር ይከብራል የላዩ የውስጡ መሸፈኛ ሲሆን እግዚአብሔር ያዝናል
ወዳጄ ሆይ
ከዋክብት በቀንም አሉ ብርሃኑ ግን አላወጣቸውም አጠገብህ ያሉትን እውነተኛ ሰዎች የምታውቃቸው የመከራ ምሽት ሲመጣ ነው አበቦችን በሌሊት አታያቸውም መልካቸውና ንግግራቸው ያማረም በመከራ ቀን አይገኙም ብቻውን ከሚበርር ባለ ክንፍ ብዙዎችን ተሸክሞ የሚያዘግም ሠረገላ ይሻላል ራስህን ለማኖር ብቻ ባለራእይ አትሁን ራስን ለማኖር ዓላማ ሰዎችን ለመርዳት ራእይ ያስፈልጋል ራስን ማኖር ስኬት ሰዎችን ማኖር ክብረት ነው ከራእይ እንጂ ከስኬት ደስታ አይገኝም
ወዳጄ ሆይ
ማግኘትህ ድሆች ወዳጆችህን አያስረሳህ ማወቅህም ያልተማሩትን ንቆ ከሊቃውንት መንደር አያውልህ ትልቁ ጥበብ እኔ የማስፈልገው የት ነው ብሎ ስፍራን መለየት ነው በቦታህ ዋና ያለ ቦታህ ትርፍ ነህ ያልሰከነ ውኃና እውቀት አይጠጣም
ወዳጄ ሆይ
ወደ እኔ ካልመጣ ብለህ የምትጠብቀውን ወዳጅህን እርሱ ካለበት ዘንድ ሂድ ወዳጅነትንና ትዳርን የሚያፈርስ መግደርደር ያለበት ፍቅር ፉክክር ያለበት ትጋት ነው
ወዳጄ ሆይ
ብርሃንን ስታይ እዚያ ቦታ ላይ ከጨለማ ጋር ከባድ ጦርነት እንደተደረገ አስተውል እውነትን በነጻ ስታገኝም ውድ ዋጋ የከፈሉ ስላሉ ነው ጨለማ
ስታይ
ያንተን ጥቂት ጥረት የሚጠብቅ ጉዳይ እንዳለ አስተውል በቁራጭ ሻማም ጨለማን መዋጋት ይቻላል
ወዳጄ ሆይ
ማግኘትህን የሚወድ ሌባ ብቻ ነው ይባላል ይሰርቅሃልና ማግኘት ብዙ ጠላት ያስነሣል አላዋቂዎችም ስታውቅ እብድ ነው ብለው የሕሊና ስደተኛ ያደርጉሃል ድንቁርና ግዛት ነውና እውቀት እንዳይደፍረው ይታገላል
ወዳጄ ሆይ
እውቀትህ የሚያስታብይህ ከሆነ ሁለት ነገር ጎድሎታል ማለት ነው እርሱም ማነስና ፍቅር ያልሞላ ገንቦ ይንቦጫቦጫል የሞላ ግን ድምፅ አያሰማም በኪስ ውስጥ የሚጮኸው ሳንቲም ነው ዋጋው ከፍ ያለ የገንዘብ ኖት ግን ፀጥ ይላል
ምክር 15
ዲአመ ሚያዝያ 11 ቀን 2011 ..
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም