መግቢያ » ግጥም » ውሰደኝ ወዳንተ

የትምህርቱ ርዕስ | ውሰደኝ ወዳንተ

                        ቅዳሜ፣ ጥር 5 2004
በፍርሐትቆፈን ተይዞ
አልጋው በድካም ተከቦ
በሠርጉ እያለቀሰ
አለ ሲሉት እየፈረሰ
በመርገም ዘር ተፀንሶ
ሕይወት በሞት ተገሶ
ሲኖር ትውልድ የደም ክልባቦት አርግዞ
እየዳ በጣዕር
አለመኖርን ሲኖር … 


ስምዖን ግን ተግቶ
ለተስፋው ቃል ተንበርክኮ
የጌታን መወለድ በትንቢት ታግሶ
እርጅና ሳይገታው በመንፈስ ታድሶ
ለእስራኤል መጽናናት ለወገኑ ማረፍ
ዓይኖቹ ሳይፈዙ የዘመኑ ርዝመት – ራእዩን ሳያረግፍ
ሞትን ያህል ነገር እግዚአብሔር አስሮለት
ወጣ ወደ መቅደስ ሕፃኑን ለማየት
እንደ አንበሳ ደቦል እየተቻኰለ
እርጅናውን ረስቶ እየተቃጠለ
አቀፈው ናፍቶቱን የዘመናት ሕልሙን
ሳመው በከንፈሩ ብርሃን ጉንጮቹን
አረጋዊው አዲስ ሆነና ጐልማሳ
ትንቢት ተናገረ ለሕፃኑ ንጉሥ- ለይሁዳ አንበሳ
በእውነት ለሰው ሁሉ አንተነህ መዳኑ
ሁሉን የምትገልጥ የዓለም ብርሃኑ
ለእስራኤል ሕዝብህ ክብርና ሞገሱ
ለኔ ለባርያህም የእርጅናዬ ልብሱ
የስንብት ቃሌ የዓይኖቼ ማረፊያ
ውሰደኝ ወዳንተ ሕልም የለኝም – በቃ አንተን ካየሁ ወዲያ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም