የትምህርቱ ርዕስ | የሆነብንን አስብ

“አቤቱ ፥ የሆነብንን አስብ ተመልከት ስድባችንንም እይ ።” ሰቆ. 5፡1።

እውነት ከያዘው ፣ ስሜት የወዘወዘው በበዛበት ፣ ጥቅስ የሕይወት ፈርጥ ሳይሆን የግድግዳ ጌጥ በሆነበት ፣ አቋም በአቋቋም በተተካበት ፣ የገባውና የገባው የመሰለው በማይለይበት ፣ እጅ ለድሀ ለመቸር እየሰሰተ ፣ አፍ ጮማ በሚቆርጥበት ፣ ጆሮ የሰማውን መቋቋም አቅቶት ሌላ ጉድ በሚናፍቅበት ፣ የወደቁ በወደቁት በሚስቁበት ፣ አገር ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በከሸፈበት ፣ ያቀፈ እየነቀፈ ባስቸገረበት ፣ ምላስ ልብን ለመደለል በሚሞክርበት ፣ ቃለ ሰብእ እና ቃለ እግዚአብሔር በተቀላቀሉበት ፣ በቅብዐት የተሾሙ በብረት በትር በሚገዙበት ፤ ቂም በዓለት ላይ ፣ ፍቅር በአሸዋ ላይ በሚጻፍበት ፣ ጉዳይን ከመፍታት ባለ ጉዳይ በሚገደልበት ፤ ባለ መድኃኒት ገዳይ ፣ ዳኛ ወንጀለኛ በሆኑበት ፣ መብል በሽታ ሁኖ ፣ በሽታም ፈውስ ባጣበት በእኛ ዘመን አቤቱ በመልካም አስበን ።

በአደባባይ ጅራፍ የምንገረፈውን ፣ በማይደበቅ ጦርነትና ረሀብ የክፉ ምሳሌ የሆነውን አቤቱ ስድባችንን ተመልከት ። ከሰውነታችን ገንዘባችን በሚፈለግበት ፣ ከእኛነታችን ይልቅ የአንድ እንስሳ ዋጋ በበለጠበት ፣ ጽጌረዳ አበባ ዙፋን ላይ ወጥታ ሰው እንደ ጥራጊ በሚደፋበት ምድር ላይ አቤቱ የሆነብንን አስብ ። እያሸበርን አሸባሪ የምንፈራውን ፣ እየገደልን እገሌ አገር ገዳይ ነው የምንለውን ግብዞች አቤቱ በፍቅርህ አስበን ። የሚያድነውን ንስሐ እባክህ አሳየን ። ሰውን ሰው ባደረገው ምሕረትህ ለዘላለሙ አሜን!

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም