መግቢያ » ግጥም » የቆምኩኝ ሲመስለኝ

የትምህርቱ ርዕስ | የቆምኩኝ ሲመስለኝ

                              ቤተ ጳውሎስ፤ ዓርብ ግንቦት 3 2004 ዓ.ም.
ማዘያው ከጠፋ የህፃን አንቀልባ
መልካሙ ተጣሞ ካጨድን ገለባ
አፅናኙ ተክዞ መፅናናትን ካጣ
የቆመ የሚመስለው ጎብጦብን ከመጣ
ረሀብ አጠውልጎት  ህፃን ካለቀሰ
ጻድቅ መላ ጠፍቶት ሰይጣን ከቀየሰ
ብርታት አጎንብሶ ድካም ፀንቶ እግሩ
ይሁዳና ዴማስ ጽድቅ ከመከሩ
ሳዖልና ኬፋ ደግ ካልተስማሙ

አቤቱ ለባሪያህ መንገዱን አብራለት

ማየትና መስማት ካንተ ይሁንለት።
ፈትልን የሚፈትል ተራቁቶ ካደረ
ውለታ የበዛለት በሳቅ ካልዘመረ
በብዙ የተሾመ ጥቂት ካልታመነ
ልብን አሳራፊው ልቡ ከጨከነ
ሰባኪ እየካደ ዓለሙ ካመነ
አማኙ ሲታበይ ቀራጭ አጐንብሶ
የጽድቁን አዝመራ ከወሰደ አፍሶ
አቤቱ ለባሪያህ አይነልቡን አብራ
የቆምኩኝ ሲመስለኝ እንዳልወድቅ አደራ።
ሥራዬ የሞት ነው ጽድቄ የመርገም ጨርቅ
አቤቱ አድነኝ በድካሜ ሳትፈርድ
ብርታትህ ያቁመኝ አንተን እንድመስል
ማስተዋሌን አድስ ያለማመኔን ቃል፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም