የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ/5

ቤተ ክርስቲያን በሊቃውንት ምሥጢር


1-  ቤተ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር በኃጢአት የሞቱ ልጆቹን እጃቸውን ይዞ የሚያነሣባት የኢያኢሮስ ቤት ናት ። ማቴ. 9፡25 ።
2-  ቤተ ክርስቲያን ማለት ክርስቶስ ረሀብተኞችን የሚመግብባት የጥብርያዶስ ባሕር ናት ። ዮሐ. 6፡1-10 ።
3-  ቤተ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር የኃጢአተኛ ልጆቹን ኑዛዜ የሚሰማባት የዘኬዎስ እልፍኝ ናት ። ሉቃ. 19፡1-10 ።
4-  ቤተ ክርስቲያን ማለት የሕይወት ዛፍ መስቀል የተተከለባት ቀራንዮ ናት ።

ወርቃማ የቤተ ክርስቲያን ስያሜ
1-  “የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ድርጅት ሳትሆን በመንፈስ ቅዱስ የምትመራ ከክርስቶስ ጋርና በክርስቶስ አዲስ ሕይወት ናት ።  
                                                        /ቅዱስ ሰርጌዎስ/
2-  “ቤተ ክርስቲያን የፍትሕ ፀሐይ ለጨለማው ዓለም የሚበራባት መስኮት ናት ።”
/ቅዱስ ሊቃናዎስ/
3-  “ቤተ ክርስቲያን በምትገኝበት ስፍራ የእግዚአብሔር መንፈስ ይገኛል ። የእግዚአብሔር መንፈስ በሚገኝበትም ቤተ ክርስቲያንና መላው ጸጋዋ ይገኛሉ ።”
/ቅዱስ ሄሬኔዎስ/
4-  “ምንም እንኳ የአብያተ ክርስቲያናት ቊጥር የበለጠ ፍሬያማ እየሆነ ያለ ማቋረጥ ቢያድግም ቤተ ክርስቲያን ግን አንዲት ናት ።”
/ቅዱስ ቁጵርያኖስ የካርቴጁ ጳጳስ/
5-  “ክርስቶስ ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያን አድሮ ይኖራል ። መንፈስ ቅዱስም ሁልጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ሕይወትና ተግባር ይመራል ።ቤተ ክርስቲያን የሁሉ ናት ። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም የዚህች የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ክፍል ናት ።”
/ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ/
6-  ቤተ ክርስቲያን ማለት ራሱ የሰው ዘር ሁሉ ሕይወቱን ለማሟላት፣ ዓላማውን ለማስተካከል ፣ ከኃጢአት ተለይቶ በሰላም በጽድቅ ታድሶ፣ አሮጌ ሰውነትን ጥሎ ፣ አዲስ ሰውነትን ለብሶ ለመኖር በእግዚአብሔር መንፈስ እየተረዳ በአንድነት የሚሠራበትና የሚመራበት ማኅበራዊ አንድነት ማለት ነው ።
/ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ/
7-  ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ ያለች ሰማይ ናት ።
/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
8-  ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ተስፋና ምልክት ናት ።ምክንያቱም እንደ ዘር ፍሬ ፣ ውስጥ እንዳለ እርሾ የመንግሥተ ሰማያት ሂደት የሚጀምረው ከቤተ ክርስቲያን ነውና ።
/ቅዱስ አግናጥዮስ/
9-  ክርስቲያኖች በጥምቀት አማካይነት አንድ የሆኑባት የትንሣኤያችን የደኅንነታችን ምንጭ የክርስቶስ አካል ናት ።
/ቅዱስ አትናቴዎስ/
10-    ቤተ ክርስቲያን ከሰማይ ወደ ምድር የተለቀቀች ናት ። አዲስም ዓለም ናት ። ክርስቶስም ፀሐይዋ ነው ።
/ቅዱስ አምብሮስ/
ይቀጥላል
አንብቡ ፣ አንብቡ ፣ አንብቡ ፣ ኧረ እባካችሁ አንብቡ
ዲአመ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ