ማክሰኞ፣ ኅዳር 26 2004
አውቃለሁ ዘመኔን ከንቱ ያለፈውን
በስርቆት በዝሙት በስካር በዘፈን
በአድመኝነት ቁጣ በክርክር ቅናት
በሽንገላ ፍቅር በርኩሰት መዳራት
ምራጭ እንደሆንኩኝ የሰው መጨረሻ
መንፈሴ ያደፈ ስጋዬም ቆሻሻ
አውቃለሁ መሆኔን ፍጹም በደለኛ
ነፍሰ ገዳይ አሳች ቀጣፊ ቀማኛ
ብዙ ያሰናከልኩ የዕንቅፋት ድንጋይ
አውቃለሁኝማ
ፍጻሜዬ ከንቱ ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ያለጌታ ምህረት ያለቸርነቱ
በአንዱ ክንፌ ጌታ ኃጢአቴን ልናዘዝ
በአንዱ ክንፌ ደግሞ በፀጋህ ልታገዝ
በኒህ ሁለት አክናፍ በርሬ በርሬ ወደአንተ ስመጣ
ጥርስ ፉጨትና ለቅሶ አይሆን የኔ ዕጣ
ግና የኔ ጌታ
‹‹ ሌባ ዕናት ልጇን አታምንም›› እያሉ
የቀደመ ነውሬን ዛሬም ያወራሉ
አንተ ረስተኸዋል እነርሱ ያውቃሉ
እባክህ እርዳቸው
ከንቱ አትተዋቸው
የጠቢብ አይኖቹ በራሱ እንዲሉ
አይናቸውን ከሰው ነቅለህ ጣልላቸው
አፋቸው ስለሰው ማውራቱን ይዘንጋው
የእድሜያቸውን ሙሉ አመፃ አበሳ ያውሩት ለራሳቸው፣ ለንተም ቅዱስ ጌታ
እኔም አረፍ ልበል ለእነርሱም ይቅርታ፡፡