የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የኑሮ መድኅን ክፍል 6

የዲ/ን አሸናፊ መኰንን ገጽ ,,,,,, ሰኞ ኅዳር ፲፭ / ፳፻፯ ዓ/ም

ምዕራፍ አራት  – የሚበልጠውን ይዘናል
  ዲዮጋን የተባለ የግሪክ ፈላስፋ ኑሮው ጎርፍ በሸረሸረው ፈፋ ውስጥ ነበር፡፡ ንብረቱም አንዲት መንቀል /የውመጠጫ ቅል/ ስትሆን አንዲት ውሻም ጓደኛው ነበረች፡፡ላቁ እስክንድር ዓለምን አስገብሮ ሲመለስ ዲዮጋን የተባለውን ፈላስፋ ማየት አለብህ ስላሉት ሊያየው መጣ፡፡ ዲዮጋን ግን ከቤቱ አጠገብ በጀርባው ተኝቶ ፀሐይ ይሞቅ ነበር፡፡ላቁ እስክንድርም አጠገቡ መጥቶ ቢቆም ማን ነው? ብሎ እንኳ ዲዮጋን ዓይኑን አልገለጠም፡፡ እስክንድርም «ዲዮጋን ሆይ ተነሥ እኔላቁ እስክንድር ነኝ፡፡ ዓለምን አስገብሬ ተመልሻለሁ፣የምትሻውን ለምነኝ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሃለሁ» አለው፡፡ ዲዮጋን ግን ዓይኑን እንደ ከደነ «ይልቁንስ አንተ ልትሰጥ የማትችለውን ፀሐይ አትከልክለኝ» አለው ይባላል፡፡ ንጉሥ እንኳ የማይሰጠውን ብዙ ስጦታ ስለተቀበልን እግዚአብሔር ይመስገን፤
ሰውዬው «እግር የሌለው እስካይ ድረስ ጫማ የለኝም ብዬ አዝን ነበር» ብሏል፡፡ መለስ ብሎ ራሱን ሲመለከት የሚበልጥ ነገር አገኘ፡፡ ጫማን ገንዘብ ይገዛዋል፣ እግሩን ግን ገንዘብ አይገዛውም፡፡ ጫማም ያማረው እግር ስላለው ነው፡፡ ለማማረርም የበቃነው በሕይወት ስላለን ነው፡፡ ለማማረር እንኳ ዕድሜ ስላገኘን ልናመሰግን ይገባናል፡፡ በሣጥናቸው ብዙ ልብስ አጭቀው ከአልጋዬ ተነሥቼ አንድ ቀን እንኳ በለበስኩት እያሉ የሞቱ ሰዎችን አውቃለሁ፡፡ የሚበላው እያለው የሚሞት፣ የሚበላው አጥቶ የሚኖር ብዙ ሰው አለ፡፡ ባለጠጎች በገንዘባቸው ለአንድ ቀን ዕድሜአቸውን ማስረዘም አይችሉም፡፡ እናት ለምትወደው ልጇ ቀንሳ የማትሰጠው ዕድሜ ስላለንና ሰው የማይሰጠውን ስለተቀበልን እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል፡፡
         በዓለም ላይ የሚገኘው ሀብትና ንብረት በሙሉ የእናንተ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሁለት ዓይናችሁን መስጠት አለባችሁ ብትባሉ እሺ ትላላችሁ? አምናለሁ በፍጹም እሺ አትሉም፡፡ ግን እኮ የተጠየቃችሁት ሁለት ዓይናችሁን ብቻ ነው፡፡ ጆሮአችሁ፣ አንደበታችሁ፣ ልባችሁ፣ እጆቻችሁ፣ እግሮቻችሁአሉ፡፡ አሁንም መልሳችሁ«እየዳሰስኩ የእኔ የምለውን ንብረት አልፈልግም» የሚል ነው፡፡ዲያ በዓለም ላይ ያለው ሀብትና ንብረት በሙሉ ለሁለት ዓይናችሁ እንኳ ዋጋ መሆን ካልቻለ እናንተ ሚሊየነር ሳይሆን ቢሊየነር ከዚያም በላይ ናችሁ፡፡ዲያ ደሃ ነኝ
እያላችሁ እንዴት ትተክዛላችሁ? እግዚአብሔር በዚህ በሰውነችሁ ላይ በዋጋ የማይተመን ውድ ንብረት አፍስሷል፡፡
        
         ሁላችንም እኩል ማልቀሳችን፣ ከእኛ ያነሱትን ሰዎች ማየትና መርዳት አለመቻላችን እግዚአብሔርን ያሳዝነዋል፡፡ አዎ ያለንን በትክክል ካላወቅን የጎደለንን በትክክል ማወቅ አይቻለንም፡፡ ትልቁ ችግራችን መርሳት ነው፡፡ መነጽር አድርገን መነጽር እንፈልጋለን፣ ቁልፍ በእጃችን ይዘን ቁልፉን አምጡ እያልን እንጣላለን፡፡ በዕለታዊ ኑሮአችን ያለን ልበ ቢስነት በሕይወት ውስጥ የተጎናፀፍነውንም በጎ በረከት አስረስቶናል፡፡ ብዙ የተቀበልን፣ ከብዙ መከራ ወጥተን ለዚህ የደረስን ሰዎች ነን፡፡ ግን ስለምንረሳ እንበሳጫለን፡፡


         ክፉ ጌትነት የሚበልጠውን ሰጥቶ በትንሹ ይነፍጋል፡፡ ክፉ ተቀባይ የሚበልጠውን ተቀብሎ በትንሹ ያማርራል፡፡ እግዚአብሔር መልካም ተቀባይ አጥቷል፡፡ በሕይወት ላይ ጽንፈኛነት አይጠቅምም፡፡ ሚዛናዊነት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ያለኝ ይህ ነው፣ የጎደለኝ ነው ማለት ያስፈልጋል፡፡ በትክክል ካየን ከጎደለን ያለን ይበልጣል፡፡
         የምንተነፍሰውን አየር መዋዕለ ንዋያቸውን ያፈሰሱበት ባለጠጎች ቢሆኑ ኖሮ በጉሮሯችን ላይ ቆጣሪ ተክለው ብንከፍል እንኳ እዘጋዋለሁ የሚለው ማስፈራሪያቸው በገደለን ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከሕይወት ጋር የተያያዙትን ነገሮች በራሱ እጅ አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ለሕይወት የሚጠነቀቅ እርሱ ብቻ ነውና፡፡ ደግሞም ውድ ነገሮችን ሁሉ በነጻ ሰጥቶናል፡፡ ፀሐይን፣ አየርን፣ ትዳርን፣
ልጅን በነጻ ሰጥቶናል፡፡ የሚበልጠውን ይዘናል፡፡ ጥቃቅን ጉድለቶች ቢኖሩም ከያዝነው አይበልጡም፡፡ የአገራችን ሰው የጤና ቀለቡ ትንሽ ነው፣ የሰላም ቀለቡ ትንሽ ነው ይላል፡፡ ጤናንና ሰላምን ግን ማንም አያመሰግንበትም፡፡ ግለሰቦችና አገራት የጦርነት ወጪያቸው ምን ያህል እንደሆነ ያውቁል፡፡ ስለ ሰላም ግን አያመሰግኑም፡፡
         ችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ስለዚህ እላችኋለሁ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?» (ማቴ.625) ብሏል፡፡
         እግዚአብሔር ካልሆነ በቀር አትጨነቁ የሚል ማንም የለም፡፡ ነገሥ እንኳ ሳይበዛ እንድንጨነቅ በጣቢያቸው ያዙልናል፡፡ «ሁሉም ሰው ራሱንና አካባቢውን በንቃት ይጠብቅ» ይላሉ፡፡ አትጨነቁ የሚለው በሰላም አገር የሚኖረው ንጉሠ ሰላም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልክ ደውለው «ያን ጉዳይህን ለእኔ ተውልኝ፣ አትጨነቅ» ቢሉን ባይፈጽሙት እንኳ የእኛ ጉዳይ አጀንዳቸው በመሆኑ በደስታ አንዘልም? እንደውም ብለን እንተኛለን፡፡ አትጨነቁ ያለን ግን የሰማይ የምድር ንጉሥ የሆነውና በቃሉ ሐሰት፣ በተስፋው እብለት የሌለበት እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህን አምላክ የንጉሥ ያህል እንኳ እንመነው፡፡ አንድ ሰው«እግዚአብሔርን የመሬትያህል እንኳ እንመነው» ብሏል፡፡ መሬትን ስንረግጣት ትደረመሳለች የሚል ስጋት የለብንም፡፡ ስለዚህ ከመራመድ አልፈን እንሮጥባለን፡፡ እግዚአብሔርምኖ የማይከዳ፣ ወዶ የማይጠላ ሆኖ ሳለ እኛ ግን የመሬትን ያህል እንኳ አምነንበት ይሆን? እግዚአብሔርን የምናገኘው በእውቀችን ልክ ሳይሆን በእምነችን ልክ ነው፡፡
         ብዙዎች ይጨነቃሉ፡፡ ዓለም በቃኝ ያሉ መነኮሳት ሳይቀር ከወለዱት እኩል በፍርሃት ይናጣሉ፡፡ የቪዛ ወሬ የብዙ አገልጋዮችን አፍ ሞልቶል፡፡ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ እጆቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ሳይሆን ወደ አሜሪካ ዘርግተዋል፡፡ መነኮሳቱ እንየሚመኩበትን ገዳም ትተው አሜሪካ ገዳማቸው ሆኗል፡፡ አሜሪካ ግን ከአንድ ሰው ጋር ተጣልየምትባረርበት አገር በመሆኗ ዋስትና ልትሰጥ አትችልም፡፡ በአሜሪካ ምድር ከአራት ሰው አንድ ሰው በመንፈስ ጭንቀት በሽታ የተያዘና መድኒት ተጠቃሚ ነው፡፡ ስለዚህ የምንሸሽባቸው ራሳቸው የሚበላ እንጂ የሚያረካ ነገር የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
        
         ብላቴን ታ ኅሩይ ለልጅ ምክር ለአባት ሰቢያ በተባለው መጽሐፋቸው «ልጄ ሆይ አሳብ ብዛ ወደ ፊትም ምን ነገር ይመጣ ይሆን ብለህ
አትጨነቅ፤ ምንም አሳብና ጭንቀት ብታበዛ የሚሆን ነገር ሳይሆን አይቀርም፡፡ልጄ ሆይ፤ ጌታ ለመሆን ትፈልግ እንደ ሆነ ጌትነት ማለት ያለ አሳብና ያለ ጭንቀት መኖር ነው፡፡ አሳብህም ሁሉ ከሞትህ በኋላ በወዲያኛው ዓለም ስለሚሆነው ስለነፍስህ ነገር ይሁን እንጂ፤ በዚህ ዓለም በሥጋህ ስለሚሆነው ነገር እጅግ አትጨነቅ» ብለዋል፡፡
         በሰው ልጅ ኑሮ ውስጥ መሠረ ፍላጎት ተብለው የሚጠሩ ምግብ፣ ልብስና መጠለያ ናቸው፡፡ እነዚህን የሚያሟላ ንጉሥ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስንጸልይ «የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን» እንላለን፡፡ እንጀራ የሚበቅለው ከምድር ሲሆን የምንለምነው ግን ከሰማይ ነው፡፡ እግዚአብሔር የበረከት ምንጭ ነውና፡፡ የምንሠራበት መሥሪያ ቤት ደሞዝን እንጂ እንጀራን አይሰጠንም፡፡ እንጀራ የተሰናዳ በረከት ሲሆን የምናገኘውም ከጓዳችን ነው፡፡ እግዚአብሔር ጓዳችን ነውና እንጀራን ስጠን እንለዋለን፡፡ እነዚህ መሠረ ፍላጎቶች የብዙ ሰው ጭንቀት ናቸው፡፡ አንድ አባት «መንፈሳዊ ሰው ማለት ምን እበላለሁ፣ ምን እጠጣለሁ፣ ምን እለብሳለሁ ብሎ የማይጨነቅ ነው» ብለዋል፡፡
        
         ስለ ነፍሳችን በምንበላው ስለ ሰውነታችን በምንለብሰው እንዳንጨነቅ ያዘዘን ለምንድነው? ስንል ምክንያቱን ጠቅሷል «ነፍስ ከመብል፣ ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?» ብሏል፡፡ «የቱ ነው የሚከብደው ለነፍስ እንጀራ መስጠት ወይስ ነፍስን ካለመኖር ወደ መኖር ማምጣት? የቱ ነው የሚከብደው ለሥጋ ልብስ መስጠት ወይስ ሥጋን ከአፈር ማነጽ?» ማለቱ ነው፡፡ የሚበልጠው ነፍስን ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ መፍጠር፣ ሥጋንም ከአፈር ማነጽ ነው፡፡ የሚበልጠውን መያዝ ለትንሹ ዋስትና ነው፡፡ የሚበልጠውን ይዘን ለትንሹ መጨነቅ አይገባም፡፡ ወርቅ የሰጠ ነሐስ ይከለክላል ተብሎ እንደማይገመት እንዲሁም ነፍስንና ሥጋን ፈጥሮ መብልና ልብስ ይነሣል ተብሎ አይጠረጠርም፡፡ ሆድን ፈጥሮ እንጀራ፣ ራቁት ፈጥሮ ልብስን፣ ኑሮን ሰጥቶ መኖሪያውን አይከለክልም፡፡ በእውነት የምንጨነቀውም ትንሽ ስላለን ነው፡፡ ምንም የሌለውማ አይጨነቅም፡፡ የምናለቅሰውም ትንሽ ዕንባ ማበሻ መሐረብ ስላለን ነው፡፡ የልቅሶን ድንበር የጨረሰማ ሳቅ ነው የሚጀምረው፡፡ በጎዳና ላይ ተኝተው የሚያንኮራፉትን ስናይ እኛ በጥሩ ፍራሽ ላይ ለምን እንቅልፍ እምቢ እንዳለን ይገባናል፡፡ የምንጨነቀው ያለን ነገር ስላለን ነው፡፡ ምንም የሌለው አይጨነቅም፡፡
የሚርበው የበላ ነው፤ የበላ አምጣ አምጣ ይለዋል፡፡
         የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጠል ስንገልጥ በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ሃያ ስድስት ቍጥሮች እንደተጓዝን የምናገኘው ቃል አለ፡፡ ይህ ቃል የሰውን ክብር ከሚገልጡ ቃሎች የመጀመሪያውም የዳርቻውም ነው፡፡ ሰውን በሚመለከት የመጀመሪያው መለኮ ቃለ ጉባዔ ሊሆን ይችላል፡፡ «እግዚአብሔርም አለ፡ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤» (ዘፍ.1፣26)፡፡ ሰውን በሚመለከት የመጀመሪያው የሥላሴ ምክር ነው፡፡ ሰው በስህተት ወይም በአጋጣሚ የተፈጠረ ሳይሆን መለኮ አጀንዳ የተያዘበት ፍጡር ነው፡፡ እያንዳንዳችን የራሳችንና የወላጆቻችን ዕቅድ ሳንሆን የእግዚአብሔር ዕቅድ ነን፡፡ «ሕገ ወጥ ወላጆች ሊኖሩ ቢችሉ እንኳ ሕገ ወጥ ልጆች ግን የሉም፡፡» እስቲ- «እኔ አጋጣሚ አይደለሁም  እኔ የእግዚአብሔር ዕቅድ ውጤት ነኝ   መነሻ
እግዚአብሔር ነው» ብለን ለራሳችን እንናገር፡፡
         የሰው ልጅ የተፈጠረው ለእግዚአብሔር የመፈጠርን ጥያቄ አቅርቦ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ፈቃዱ የእግዚአብሔር በሆነበት ምሥጢር ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር እኛን ሳይሆን እኛ እግዚአብሔርን እንመስላለን፡፡ እኛን የሚመስል አምላክ እኛ የምንፈጥረው ጣኦት ነው፡፡ እውነተኛ አምላክ ግን እንድንመስለው የፈጠረን ነው፡፡
         የሥነ ፍጥረትን ትምህርት ስንመረምር ሁሉም ነገር ለሰው ተፈጥሯል፡፡ በሰማይና በምድር ውስጥ የሚገኙት ነገሮች ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለሰው ጥቅም ተፈጥረዋል፡፡ ቍሳቍስ ለእኛ፣ እኛ ለእግዚአብሔር ተፈጥረናል፡፡ ቍሳቀስ ለእኛ እንጂ እኛ ለቍሳቍስ አልተፈጠርንም፡፡ ዛሬ ግን ሎሌው ጌታ ሆኖ ሰውን ይገዛዋል፡፡ ወርቁ በሥላሴ አርአያ በተፈጠረው አካል ላይ በማረፉ ሊኮራ ሲገባው ሰው በወርቅ ይኮራል፡፡ በሱቅ ውስጥ የተቀመጡት ዕቃዎች ዋጋቸውን ያውቃሉ፡፡ እኔ ይህን ያህል አወጣለው ይላሉ፡፡ ሰው ግን ዋጋውን አያውቅም፡፡ የሰው ዋጋው እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ ዋጋ ደግሞ በየትኛውም ዘመን አይዋዥቅም፡፡
         እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ ከፈጠረ በኋላ በመጨረሻው ቀን ሰውን ፈጠረው፡፡ ሰው ከመፈጠሩ አስቀድሞ ለሰው የሚያስፈልጉ ነገሮች ተፈጥረዋል፡፡ ዛሬ የሰው ልጅ የሚጨነቀው ከእርሱ በፊት ለተፈጠሩት ነገሮች ነው፡፡ እያንዳንዱ ፍጡር ከነበጀቱ ወደዚህ ዓለም መጥቷል፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ወደዚህ ዓለም ሲያመጣው ስፖንሰር (ወኪል) የሆነው ራሱ ነው፡፡ዲያ ስፖንሰር ያለው አይጨነቅምና ሰው መጨነቅ የለበትም፡፡ በየአገራቱ ያለው የስፖንሰር ሕግ ወደዚያ አገር ያመጡትን ሰው የማኖር አቅማቸውን ይለካል፡፡ አቅም ከሌላቸው ስፖንሰር መሆን አይችሉም፡፡ ያለ መንግሥት ድጋፍ ምን ያህል ጊዜ እንግዳውን ማኖር እንደሚችል ይጠናል፡፡ እግዚአብሔር ከዚህ በተሻለ መለኪያ ያለ ማንም ብቻውን በቂና ከበቂ በላይ ሆኖ ሊያኖረን ፈጥሮናል፡፡
         መልካም ወላጅ ልጁ ከመወለዱ በፊት ለልጁ የሚያስፈልጉ ነገሮችን እንደሚያዘጋጅ፣ አሳድጎ ርስት ሰጥቶ፣ የጨዋ ልጅ ድሮ ጎጆ እንደሚያወጣው እግዚአብሔርም ለሰው ልጅ መኖሪያውን ዓለም፣ የፍላጎቱን ግብ፣ አጽናኝ ጓደኛ ሰጥቶ ፈጥሮታል፡፡ ከዚህ ባሻገር እግዚአብሔር ማንንም ሰው ያለ ወዳጅ አልተወውም፡፡ ክፉ ቢሆን እንየሚወዱትን ሰዎች አዘጋጅቶለታል፡፡ ይህም የእግዚአብሔር በጎ ስጦታ ነው፡፡
         የሚበልጠውን ይዘናል? ከበረከት ሁሉ የሚበልጠው በረከት የዕድሜ በረከት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምንኖረው መኖር መብታችን ስለሆነ ይመስለናል፡፡ መኖር ግን የእግዚአብሔር ስጦነው፡፡ ወላጆቻችን ረጅም ዘመን ስለኖሩ እኛም እንደ እነርሱ ረጅም ዘመን ኖረን የምናልፍ ይመስለናል፡፡ መኖር የእግዚአብሔር ስጦመሆኑ የሚገባን ግን መኖርን የሚቋቋሙ ነገሮች ሲገጥሙን ነው፡፡ ስንመም፣ በምርኮ ውስጥ ስንሆን እያንዳንዱን ቀን ዋጋ እንሰጠዋለን፡፡ እኛ ግን ለመኖር እርግጠኞች ሆነን ለመኖሪያው እንጨነቃለን፡፡ እስቲ መጀመሪያ ስለ መኖራችን እናመስግን፡፡ ከእኛ የተሻሉ ቆንጆዎች፣ ከእኛ የተሻሉ አዋቂዎች፣ ከእኛ የተሻሉያላን አልፈዋል፡፡ እኛ የቀረነው በብልጠችን ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረት ስለበዛልን ነው፡፡
         የሚበልጠው አለን ማንም በደግነት ለማንም የማይሰጠው የዘላለም ሕይወት አለን፡፡ የልጅነት ጸጋ አለን፡፡ መንፈሳዊ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ የምትሆን መንፈሳዊብረት አለን፡፡ የመረጃ እጥረት ያለብን እንጂ ብዙ ያጣን ሰዎች አይደለንም፡፡ ስለ ኑሮ መባነን ከበዛብን ግን የጤናችን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ዶክተር ኢሳይያስን ልኮ ከምዕራፍ 4914-16 ፍቱን መድኒት አዞልናል፡
         «ጽዮን ግን  እግዚአብሔር ትቶኛል ረስቶኛል አለች፡፡ በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን  እርስዋ ትረሳ ይሆናል  እኔ ግን አልረሳሽም፡፡ እነሆ  እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ  ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ፡፡»
የጽሞና ጊዜ
ያለህን በትክክል ካላወቅህ የጎደለህን በትክክል ማወቅ አትችልም፡፡ ስለጎደለህ ለቅስ አሁን አለኝ የምትለውም ያንተ አለመሆኑን አስብ፡፡ ስለጎደለህ ከማዘንህ በፊት ስላለህ ነገር አመስግን፡፡ «ውለታው ብዙ የእግዚአብሔር፣ አመስጋኝማ ቢኖር» እንደተባለ ይህች ሰዓት እንኳ የእርሱ ውለታ መሆኗን ተገንዘብ፡፡ ከሁሉ በላይ የሚበልጠውን ተቀብለሃል፡፡ ስለዚህ፡
·       ገንዘብ የማይገዛው ተፈጥሮ እንደተቀበልህ፣
·       ውድ ነገሮች በነፃ እንደ ተሰጡህ፣
·       እግዚአብሔርን የመሬት ያህል እንኳ ልታምነው እንዳልቻልህ አስብ፡፡
ጸሎት

ያለመያዣ የወደድኸኝ፣ ለምጻም ሳለሁ ያፈቀርከኝ፣ ሙት ሳለሁ ያልረሳኸኝ ሠሪዬም ሰሚዬም እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ ዓለም ለዲዮጋን እንዳለፈች ለእስክንድርም አልፋለችና አሳላፊው አመሰግንሃለሁ፡፡ ያኖረኝ እጅህ እንጂ መልፋት መፍጨርጨሬ አይደለም፡፡ ሁሉ ባንተ ዘንድ ከተወሰነ መጨነቄ ከንቱ ነውና አርቅልኝ፡፡ ስለጎደለኝ ነገር አንተን ከሰይጣን ጋር ከማማህ፣ ስላለኝ ነገር ከመላእክት ጋር እንዳመሰግንህ እርዳኝ፡፡ እንዳትረሳኝ በእጆችህ መዳፍ ስለቀረጽከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ መቼም በማላፍርበት ስምህ በኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለሙ አሜን። 

ያጋሩ