የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የአቡነ ጳውሎስ አባታዊ መልእክት ለደቀ መዛሙርት

ቤተ ጳውሎስ ቅዳሜ ነሐሴ 12 2004 ዓ.ም.
           /ቅዱስነ
 
           /ቅዱስነታቸው ለመንፈሳዊ ኮሌጆች አድገትና መስፋፋት ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው ይታወቃል። ላለፉት 20 ዓመታትም  ተማሪዎችን አስመርቀዋል። ይህ ጽሑፍ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በየዓመቱ ለሚመረቁ የሥነ መለኮት ተማሪዎች ከትምህርት ማስረጃቸው ጋር የሚሰጡት አባታዊ መመሪያ ሲሆን እኛም ለአንባብያን አቅርበነዋል። በምክሩ ረቂቅነት ከመደነቅ በላይ በእውነትነቱ ብርሃንን ታገኙበታላችሁ ብለን እናምናለን!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
አባ መልእክት ለደቀ መዛሙርት
       የዘመናችሁን ዐሥራት ሳይሆን መላዕድሜአችሁን ለወንጌል አገልግሎት የሰጣችሁ፣ ዘመናዊውን ዓለምተላምዳችሁ ዘመናውያን ሰዎችለመሆን ሳይሆን መንፈሳዊውን ዕውቀት ቀስማችሁ የዓለም ብርሃን ለመሆን በመንፈሳውያን ኮሌጆች ውስጥእየተማራችሁ የምትገኙና የትምህርታችሁን የመጀመሪያ ምዕራፍ አጠናቃችሁ በእግዚአብሔር ስም ልትመረቁ የበቃችሁ የተወደዳችሁ ልጆቼ! በፍቅሩ ቅመም አልጫውን ምድርባጣፈጠው፣ ጨለማውን ዓለም በቃሉ ባበራው በጌችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምሰላም እላችኋለሁ!
       የተወደዳችሁ ልጆቼ!እግዚአብሔር አምላካችን የአንድ ቀንንመታመን የማይረሳ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማገልገል ብቁዎች መሆንአለብን ብላችሁ ወደ መንፈሳዊ ትምህርት ቤትየመጣችሁበትን የአንዷን ቀን ፍቅራችሁን የሚያስብ አምላክ ነው፡፡ ምንምእንኳ የጓዳውና የቤቱ ሥራአስፈላጊና የማይታለፍ ቢሆንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግንከማርታ ይልቅ በማርያም ደስተሰኝቷል፡፡ ማርታ  ያላትን ለትልቁ እንግዳ ልታቀርብ ባለቤቱን ጌታ እንደ እንግዳ ቆጥራመባከን ጀመረች፡፡ ማርያም ግንበቤቷም የሚያስተናግዳትን፣ የታዛዋ ብቻ ሳይሆን የሕይወቷም ራስየሆነውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልታደምጥ ከእግሩ ሥርቍጭ አለች /ሉቃ.10፡38-42/፡፡ጌታችን ለእርሱ ከማድረጋችን በፊት ያደረገልንን፣ ስለእርሱ ከመናገራችን በፊትየነገረንን እንድናስተውለው ይፈልጋል፡፡ የማርታ  እህት ማርያም ይህንየተረዳች ትመስላለች፡፡ እናንተም ደቀ መዛሙርት ያሳለፋችኋቸው ዓመታት ከጌታችን እግርሥር ቍጭ ብላችሁ ድምፁን የሰማችሁበት ዓመታት ናቸውና ደስይበላችሁ! ምንም እንኳ  የዘወትር ትካዜአችን እንደቃሉ መኖርአለመቻል ቢሆንም በቃሉ የመኖርንይል በንስሐና በጸሎት ልንለምን ይገባናል፡፡
      የተወደዳችሁ ደቀ መዛሙርት ልጆቼ!እስከ ዛሬ የሚታሰብላችሁ ልጆች ነበራችሁ፡፡ ዛሬግን የምታስቡ ወላጆች እንድትሆኑ ለወንጌል ሙሽራይት ቤተ ክርስቲያን ትድራችኋለች፡፡ በዘመናት ሁሉ እንደ  የው ወንጌል ዝም ማለትየማትወድ ናት፡፡ ወንጌልም መክናአታውቅም፡፡ የወንጌል የማጌጫ ዘውዷ አክሊለ ሦክ፣የሥልጣን ዘንጓም መስቀል፣ መገለጫዋም መገፋት ነው፡፡ የማትገድለው ወንጌል ለመሥዋዕትነት የጨከነች ናትናአዲሱ ኑሮአችሁን ቤተክርስቲያን ትመርቃለች፡፡
     የተወደዳችሁ ልጆቼ! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ለሦስት ዓመታት ከሦስት ወራትያህል ካስተማራቸው በኋላ በኃይለ መንፈስ ቅዱስከልሎ ወደዓለም ልኳቸዋል፡፡ እናንተም ላለፉት ዓመታት የደቀመዝሙርነት ትምህርታችሁን ተከታትላችኋል፡፡ ትምህርታችሁ በሞገስ ለሕዝብ እንዲደርስ የመንፈስ ቅዱስን  ይል ልትለብሱ ያስፈልጋችኋል፡፡ ይህንም  ይል የምታገኙት በጽሞናና በጸሎት በመቆየት ነው /ሉቃ.2449/፡፡ ቤተ ክርስቲያን እናንተን መምህራን አድርጋ ሳይሆን ደቀመዛሙርት አድርጋ መርቃለች፡፡ ስለዚህ የሁልጊዜ ተማሪዎች እንደሆናችሁ፣ ትምህርትም የማያልቅ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባችኋል፡፡
      የተወደዳችሁ ልጆቼ! ምንም ብታስተምሩ፣ ምንምብትጽፉ ዓለም አበባ ይዛእንደማትቀበላችሁ ዕወቁ፡፡ ይህበእናንተ የተጀመረ ሳይሆን የዓለም መገለጫዋ መሆኑን አትዘንጉ፡፡ ልዩልዩ ነቀፋና ስደት ሲመጣባችሁ ከዓለም እንደ ተጣላችሁ አትቍጠሩት፡፡ እንዲያውም ከዓለም ጋርእንደተዋወቃችሁ ቍጠሩት፡፡ ዓለምእንደዚህ ናትና፡፡ ጎበዝ የሚባለው ሳይቀር በመገፋት ውስጥበኀዘን ይጎዳል፡፡ የሚታተስፋም እያጣ በብቸኛነት ይንገላታል፡፡ ይሁንና ሰው መተማመኛ የማይሆን የሸምበቆ ምርኵዝ መሆኑን ቃሉ ይነግረናል /ኢሳ.366/፡፡ ስለዚህ በሁሉም ነገርውስጥ የጠራችሁን ጌታ  ክርስቶስን ተመልከቱ /ዕብ. 31/፡፡ የተቀበላችሁትን ለመስጠት ብቻሳይሆን ያልተቀበላችሁትንም ለመስጠት ፈቃደኞች ሁኑ፡፡ ፍቅርን አላያችሁ ከሆነ ከእናንተ ይልቅየፍቅርን ረሀብ የሚያውቅ የለምና ፍቅርን ስጡ፡፡ የሚያዝንላችሁ አባት አላገኛችሁ እንደሆነ ለሚጠጓችሁ እናንተ ደግሞ አዛኝአባቶች ሁኑ፡፡ ተራራውን ስትጨርሱ መስክ እንደሚያጋጥማችሁ እያሰባችሁ በተራራው አትዘኑ፡፡ እናንተ ዱርመንጣሪዎች
ናችሁና
የተመቸ ቦታንፍጠሩ እንጂ ምቹ ቦታን አትጠብቁ፡፡ የደረሰባችሁ ችግርም እስከ ዕድሜአችሁ ፍጻሜ የምትናገሩትን ትምህርት ይሰጣችኋልና አትበሳጩ፡፡ ከምትፈልጉት ነገርይልቅ ያገኛችሁት ይበልጣል፤ እርሱም የሰማይ ዜጎችመሆናችሁ ነውና ደስይበላችሁ!
     የተወደዳችሁ ልጆቼ! እግዚአብሔር የሚባርከው አሳባችሁን ሳይሆን ቃልኪዳናችሁን ነውና አገልግሎታችሁን በቃልኪዳን ያዙ፡፡ መጽናናትን የሚሹ ብዙዎች ኀዘነተኞች፣ በማዕበል የሚንገላቱ ብዙዎች ደካሞች እየጠበቋችሁ ነውና ፍጠኑ፡፡ እናንተን ለማለት አቅምየሌላቸው ብዙ አሉና ሳይጠሯችሁ ዱ፤ወንጌል አገሯ እስከ ምድርዳርቻ ነውና፡፡ ዘመናዊነትና ሥልጣኔ የማይሞላው የሕይወትን ክፍተት በወንጌል የምትሞሉ እናንተ ናችሁ፡፡ የያዛችሁትን እንደቀላል አትቍጠሩት፡፡ የዓለምን  ይልና እውቀት ሁሉ የምትማርኩ የዕውነት ዘማቾች ናችሁ፡፡ እንደማይፈለግ ሰው ራሳችሁን አትቍጠሩት፡፡ የሞተላችሁ
ጌታ  ውበቱ የማያረጅ፣ ዛሬም ያደመቃችሁ እርሱ ነው፡፡
                                                                                                            የተወደዳችሁ ልጆቼ!ዋጋችሁ በሰማያት እንደሆነ እያሰባችሁ በትንንሽ የምድር ዋጋክብራችሁን እንዳትጥሉ ተጠንቀቁ፡፡ እኔም በጸሎትና በአባታዊ ፍቅርከእናንተ ጋር ነኝ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በሰማያዊና በምድራዊ በረከቱ ይባርካችሁ! ዛሬእንደ ያዕቆብ በሌጣ ወጥታችሁ፣ ለከርሞ ግንበብዙ ፍሬይመልሳችሁ! እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ! የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒችን ኢየሱስ ክርስቶስ አገራችን ኢትዮጵያን ይባርክ!
አባ ጳውሎስ ዶክተር ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት
             ለደቀ መዝሙር                 
                
                                         —————-ቀን 200—- ..
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ