የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የክብር ፍጻሜው

ቤተ ጳውሎስ፤ ማክሰኞ ሐምሌ 17 2004 ዓ.ም.
አስኪ አትቸኩል ኤልያብ አልሆነም
የእግዚአብሔር ሞገስ ዘለግታ አይደለም
ዳዊት ነው በሞገስ ሊቆም የሚቻለው
ጌታ ሊያድርበት ወዶ የፈቀደው
የእንጨት ስራ አይደለም መቅደሱ ልብ ነው።

እሞታለሁ አትበል በቁም ሞተህ ሳለ
መሞትህ ላይፈይድ ዝምን ማን ገደለ
ግና አትቃመም ታዘዝ ለፈቃዱ
የሚበልጠው ነገር መገዛት ነው ለአንዱ
ከእርሱ የሆነ እንደሁ ፍጹም ነው በእውነቱ
ሞቱ እንኳ የጌታ ጸድቋል በአባቱ
ወዲህ ሲል እግዚአብሔር ወዲያ የምትዞረው
በሰው ሀሳብ ሁሌ ምታገለግለው
ለጥቂቷ ዕድሜ ለቀረው ዘመንህ
ከእርሱ የሆነውን ሀብቱን ሀብቴ ብለህ
ያለህን ሁሉንም ተከተለው ጥለህ
ይህ ነው መክበሪያህ ከፍ ብሎ መታያህ
የአንተ ፈቃድ ወድቆ የእርሱ ሲነግስብህ
ልብህን ሀሳብን ተውለት ይያዘው
ከእርሱ የሆነው ነው የክብር ፍጻሜው።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ