የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ጳጉሜን አብረን እንጸልይ

ቤተ ጳውሎስ፤ ረቡዕ ነሐሴ 30 2004 ዓ.ም.

ጳጉሜን ወር በሀገራችን ስለአሮጌው ዓመት ምስጋና የሚቀርብበት አና ስለአዲሱ ዓመት ደግሞ ምልጃ የሚቀርብበት  የጾምና ጸሎት ወር ነች፡፡ እኛም ይህን በማሰብ ለአንባቢዎቻችን የአብረን አንጸልይ ግብዣ ለማቅረብ ወድደናል፡፡
ስለዚህ
እግዚአብሔር ባለፈው ዓመት ስላደረገልን መልካም ነገሮች የምስጋና ጸሎት፤ 
v በሀገራችን ስላለው ሰላም፣
v ስለግል ሕይወታችን፣
v አምላካችን እግዚአብሔር ስላሳየን የፍቅር ልብ፣
v ስለአበዛልን ይቅርታ፣
v በሰማይና በምድር ከፍ ብሎ ያለው ጌታ ከፍ ባለው ሀሳቡ ጠርቶ ልጆቹ ስላደረገን፣
v  ስለባረከን፣
v ስለቀደሰን፣
v በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዘላለማዊ እና ከቶውንም የማይቋረጥ ፍቅሩን በመስቀል ላይ ስለገለጠልን፣
v እኛም ይህን እውነት ስለአስተዋልን፣
v አገራችን በቤተ ክህነትም በቤተ መንግሥትም መሪዎችዋን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አጥታ ሳለ እግዚአብሔር አምላካችን በህዝቡ ልብ መረጋጋትን ስላስቀመጠልን፣
v ጠላትም የተንኮል እጁን የሚዘረጋበት መንገድ ስላጣ፣
v በአጠቃላይ ስለዋለልን ውለታ እናመስግነው፡፡
ስለ ክፋት በደላችን የሚቀርብ የንስሐ ጸሎት፤
v ስለበደላችን፣
v የይቅርታ ልቡን ስለመግፋታችን፣
v በተደረጉልን በጎ ነገሮች ማመስገን ስለአልቻልን፣
v በፍቅር ተጠርተን በበደል ስለመመለሳችን፣
v ዛሬም በኃጢአት ቁስሉን ስለምንወጋ፣
v ዛሬም በበደል ውስጥ ስላለን፣
v  ለሰዎች ማሰናከያ ስለሆንንባቸው ነገሮች፣
v የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለህዝቡ ለመመስከር ባለመጨከናችን፣
v እሱ ሕያዉ ጌታ ከዘር እና ከቋንቋ ዋጅቶን ሳለ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንኳ ልንደብቀው ስለአልቻልነው ዘረኝነታችን፣
v ከእግዚአብሔር ሀሳብ ይልቅ ራሳችንን ለፖለቲከኞች ሀሳብ ስላአስገዛን፣
v ለእነርሱ የጥቅም ፍቅር አጋር ስለሆንናቸው፣
v ሁሉን እንድንወድ ታዘን ምክንያታዊ በሚመስል ጥላቻ ውስጥ ስለመደበቃችን፣
v ለወንጌሉ ቃል እንደሚገባ ስለአልታዘዝን ራሳችንን በፊቱ ዝቅ አድርገን ንስሐ እንግባ
እንዲሆኑ ለምንፈልጋቸው ነገሮች የሚቀርብ የምልጃ ጸሎት   
v እግዚአብሔር አምላካችን በሀገራችንንም በቤተ ክርስቲያንም የሰዎችን ምርጫ እና ጥበብ ከንቱ አድርጎ እርሱን የሚወድና የሚታዘዝለት መሪ እንዲሰጠን፣
v ቤተ ክርሰቲያናችንን እንዲመለከትልን፣
v ዲያቢሎስ በሽንገላ አባቶችን እንዳያስትብን፣
v ሁሉም በጥሞና ሁሉም በንስሐ ሆነው እግዚአብሔር ብቻ የሚሰሙበትን እና ለእርሱ የሚታዘዙበትን ማስተዋል እንዲያድላቸው፣
v ምዕመኑም ለእግዚአብሔር ሀሳብ እሺ በጄ ብሎ በሙሉ ልብ የሚታዘዝበት ቀን እንዲመጣ፣
v ሰባራው እንዲጠገን፣
v ጎባጣው እንዲቀና፣
v ድሀ አደጉ እና መበለቲቱ ከፍርድ እንዳይጎድልባቸው፣
v ቀጣዩ ዓመት ለሀገሪቱ በጎ ነገሮች እንዲከሰቱ፣
v የኑሮ ውድነቱ እንዲቀንስ፣
v ምርት እንዲበዛ፣
v ሰላምዋ አንዲጠናከር፣
v ሰዎች የተመኙልን ሳይሆን የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ያሰበልን እንዲፈጸም፣
v የሀገሪቱ ስም ሁሌም በበጎ እንዲጠራ የእኛም ክርስትና በእግዚአብሔር እውነት የተደገፈ እንዲሆን፣
v ሀሳቡን ከመጋፋት እንዲጠብቀን፣
v በሕይወታችን የላላውን መልካምነት እንዲያጠብቅልን፣
v እየከሰመ ያለውን ቸርነት የበረከታችን ምንጭ እንዲያደርግልን እንማልደው፡፡
በነዚህ ርዕሶች ሳምንቱን አብረን እንጸልይ፡፡ ሌላም እንዲጸለይባቸው የምትፈልጉዋቸው ርዕሶች ካሉዋችሁ በአስተያየት መስጫው ጻፉልን እኛም ሆንን አንባቢዎቻችን እንጸልይባቸዋለን፡፡ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጎ የሆነ የጾምና ጸሎት ወቅት ያድርግልን፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ