የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ፍሬው የደስታ ነው

                                               ቤተ ጳውሎስ፤ ሐሙስ ግንቦት 30 2004 ዓ.ም.

ሳንጀምረው ፈርተን
ሳንሞክር ርቀን
ሳንሻገር ቆመን
እሾሁን መንጥረን
ኩርንችቱን ነቅለን
ካንድም ሁለት ሶስቴ ሳንታክት መላልሰን
እርፍና ሞፈሩን ቀንበርም አጣምደን

የእርሻና የዘር ወራቱን ታግሰን
ብናርስ ብንኰተኩት
በዓላማ ጽናት
ለእህሉ ማፋፊያ
አኑረን ፋንድያ
ከዘሩ በኋላ አረሙ ሲመጣ
በማስተዋል ፀጋ ነቅለን ብናወጣ
ፍሬው ተንዥርጐ ፀንቶ ቆሞ ሥሩ
ይበዛ ነበረ ሊታጨድ መከሩ
አገልጋይ ይተክላል
ተክቶ ያሳድጋል
አድጎ እስኪያፈራ ችሎ ይጠብቃል።
የዘሩ ለት ትቶ እግዜር ይየው ማለት
መሆኑን እወቀው የጌታን አይኝ መውጋት
አንተ እንድትዘራ አንተ እንድታሳድግ
የመከሩ ጌታ ከመረጠህ በውድ
አትታክት አትድከም መከሩን ጠብቀው
አድጎ ያበበ ለት ፍሬው የደስታህ ነው።

ያጋሩ