የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ለእኔ ነው ! ?

አዎ ጌታዬ ለእኔ ነው ዘመን የጨመርከው? ለእኔ ነው እያጡ ማግኘትን፣ እየሞቱ ሕያው መሆንን ያደልከው ? እኮ አንተ የቀትሩ ጥላ፣ አንተ የበረሃው ምንጭ ለእኔ ነው የመኖር ፈቃድ የሰጠኸው? በዚህ በጥም ቀን ለእኔ ነው የደረስከው? ከተሰበከው፣ ከተዘመረው በላይ የሆንከው፣ የበላይ የሌለብህ የበላይ ሆይ ለእኔ ነው ፍቅርህን የላከው? ሰውን መዓት ያስደነግጠዋል፣ ራሱ የሚያንስበት አሽከር ግን ውለታ ያስደነግጠዋል። እኮ ያልጠበቅሁትን ቀን፣ አይደርስም ያልኩትን ዓመት አየሁት ! አንተ የዕድሜ ማማ፣ አንተ ዝርግፍ ጌጥ፣ አንተ በራስህ የምትኖር፣ አንተ የጠላት ብዛት የማይመልስህ እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን! በከፍታም በዝቅታም ለታመኑልኝ ወዳጆች ክብረት ስጥልኝ! በአማኑኤል ስምህ፣ በፈሰሰው ደምህ ፣ በማርያም እናትህ ! አሜን።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ታኅሣሥ 1 ቀን 2017 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ