የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ማንም

እግዚአብሔር በጊዜ ውስጥ የማይሽረው ቍስል የለም ። ከዛሬ ነገ የተሻለ ነው ። ከባዱ ይቀላል ፣ መራራው ይጣፍጣል ፣ ዓመፀኛው ይበርዳል ። ለሞት የሚፈልጉህ ንዴታቸው ይበርዳል ። ያሳደዱህ “ግን ምን ሁነን ነው ?” ብለው ንስሐ ይገባሉ ። ያደሙብህ ተጣልተው ይበታተናሉ ። ጠላቶችህ እየኮሰሱ ያንተ ቤት ግን እየበረታ ይሄዳል ። እውነት እልሃለሁ ከዛሬ ነገ ይሻላል ። ብቻ ቅን ሁን ። እግዚአብሔርንም ተስፋ አድርግ ። ሕይወት የእግዚአብሔር ሂሳብ ናትና ማንም አይዘጋትም ።

ከኤፌሶን ምዕራፍ አራት ትርጓሜ የተወሰደ /ያልታተመ/

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ታኅሣሥ 25 ቀን 2014 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ