መካድ ስትችል ለተቀበልኸኝ ፣
ደካማ እምነቴን ላልተጸየፍክብኝ ፣
ከክርስቲያን ማኅበር ለደባለቅኸኝ ፣
አዎ ምስጋና ፣ ላንተ ለእግዚአብሔር ይሁንልኝ !
ምስጋና ላንተ
ሰጥተህ ስጠኝ ላልከኝ ፣
በታዘቡኝ ፊት ላስተካከልከኝ ፣
ቅዱስነትህ ኃጢአተኝነቴን ላልናቀው ፣
መኖሬን ባለ ምክንያት ላደረግኸው ፣
ምስጋና ፣ ላንተ ለእግዚአብሔር ይሁንልኝ !
ምስጋና ላንተ
ሕይወትን ያህል በነጻ ለሰጠኸኝ ፣
ፍቅርህ ይህን ያህል ለማይባል ፣
ስተች ለመከርከኝ ፣
ስንቅ አፈር ነህ ላልከኝ ፣
ያንን ቀን ላሳለፍክልኝ ፣
ሰፊ ምኞቴን አትርፈህ ለሰጠኸኝ ፣
ሚዛን ከሌላት ዓለም ላዳንከኝ ፣
ምስጋና ፣ ላንተ ለእግዚአብሔር ይሁንልኝ !
ምስጋና ላንተ
በፈተናዬ መልሱን ላቀበልከኝ ፣
በከሳሾች ፊት አንደበት ለሆንከኝ ፣
ሰውን መውደድ ላለማመድከኝ ፣
አስገራሚ ቅባትህን ላፈሰስክልኝ ፣
ጉዳዬን ጉዳይህ ላደረግህልኝ ፣
እኔን ማስተማር ለማይሰለችህ ፣
ሕይወትን በምዕራፍ ላሳየኸኝ ፣
የሆነልኝን ሁሉ ለከወንክልኝ ፣
ምስጋና ፣ ላንተ ለእግዚአብሔር ይሁንልኝ !
ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም.