የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ረቡኒ መጽሐፍ – ረቡኒ…አለችው

 
የዲ/ን አሸናፊ መኰንን ገጽ                      ማክሰኞ  ግንቦት ፲፪ ፣ ፳፻፮ ዓ/ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፳
                                         ረቡኒ
መግደላዊት ማርያም ራሱን ጌታችንን፡– «ጌታ ሆይ፡አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ» (ዮሐ. 2015) አለችው፡፡ ለመሆኑ ትችለዋለች? ወስዳስ የት ታደርገዋለች? ፍቅር ከመቻል ያልፋል፤ በዚህ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ራሱን መሰወር አልቻለም፡፡ «ማርያም» አላት፡፡ እርሷም በአካል ቢገለጥ፣ ቢጠይቃት አላወቀችውም፡፡ በስሟ ሲጠራት ግን አወቀችው፡፡ የእርሱ አጠራር ከሌሎች አጠራር የተለየ ነው፡፡ ቅላጼው፣ የድምጹ ቃና፣ የቃላቱ ፍሰት ዘላለማዊ ፍቅር የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ቃና ሲጠራት ነፍሷ ተላወሰች፣ ልቧ ተቃጠለች፡፡እነዚያ የሚፈጥሩ ቃላት ሀዘኗን እንደ ጉም ሲበትኑት በቅጽበት ተሰማት፡፡ከሦስት ቀን በፊት የምታውቀው ድምፅ ነው፡፡ ይህ ድምፅማ ያኖረኝ፣ ዕድሜ የቀጠለልኝ፣የመኖር ፍላጎቴን የጨመረልኝ፣ለራሴ ዋጋ እንድሰጠውያደረገኝ ነው፡፡ በፍጹም ፍቅር እንዲህ ብሎ የሚጠራኝ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም የለም ብላ፡– «ረቡኒ» አለችው፡፡ በዕብራይስጡ መምህር ሆይ ማለት ነው፡፡
ለደቀ መዛሙርቱናለመላእክቱ «ጌታዬ» ብላ ገልጻዋለች፡፡ ራሱን ግን መምህሬ አለችው፡፡በርግጥም እርሱ ጌታም መምህርም ነው፡፡ በዓለም ላይ ከሚገኙ ጌቶች እርሱን ልዩ የሚያደርገው በፍቅር፣ በርህራኄ የሚገዛ ጌታ መሆኑ ነው፡፡ መምህርነቱም ከመምህራንየተለየ ነው፡፡ «የሚለውጥ ፍቅር» በሚለው መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተገልጾአል፡
           –ታላቁ መምህር ክርስቶስን ልዩ የሚያደርገው፡
1.         ለልብ ቀርቦ የሚናገር መሆኑ፡በዓለም ላይ የሚገኙት አስተማሪዎች ለአእምሮአችን ይናገሩ ይሆናል፡፡ ክርስቶስ ግን ለልባችን ቀርቦ ይናገራል፡፡እርሱ ለልባችን ያለ ድምጽ ይናገራል፡፡ «ኢየሱስ በልባችን ውስጥ ካልተናገረመጽናናት ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ እርሱ አንድ ቃል ብቻ ቢናገር ግን ታላቅ መጽናናት ይሰማናል፡፡»

2.         የሚረዳ መሆኑ፡በዓለም ላይ የሚገኙት አስተማሪዎች ያስተማሩትንትምህርት እንዲኖሩትተማሪዎቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ታላቁ መምህር ክርስቶስ ግን ያስተማረውንእንዲኖሩት አማኞቹን ይረዳል፡፡
3.         በሕይወት የሚያስተምር መሆኑ፡ማንኛውም አስተማሪ በሰሌዳና በብዕር እንጂ በሕይወት እያሳለፈ ማስተማር አይችልም፡፡ ክርስቶስ ግን በሕይወት እያሳለፈ የሚያስተምር ብቸኛ መምህር ነው፡፡ ዘረኛው ናፖሊዮን እንኳ እንዲህ ብሎ ተናግሯል ይባላል፡– «ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል መገኘት ሳያስፈልገው አማኞቹን ለማዘዝና ለመግዛት ችሏል፡፡» /የሚለውጥ ፍቅር፣ ገጽ 231997 ../፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስንጌታዬ ስንለው ገዝቶኛል ሕይወቴን ለውጦታል ማለታችን ነው፡፡ ራሱን መግዛት ያቃተው ዓለም ወደ እኛ የሚመጣውም ይህን የሕይወት ምስክርነት ሲያይ ነው፡፡ በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ከታወቁት ምስክርነቶችአንዱ፡– «ኢየሱስ ጌታ ነው» የሚለው ነው፡፡ ጳውሎስ ይህን ቃል በሁለት ስፍራዎች ላይ ገልጾታል፡– «ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክርእግዚአብሔርም ከሙታን እንዳነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና» (ሮሜ 10 9-10) ይላል፡፡ ዳግመኛም፡– «ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፡ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ. በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፡ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ» (1ቆሮ. 123) ብሏል፡፡
  በዘመኑ የነበረው ገናና የዓለም ገዥ ኔሮን ቄሣር ምስሉን አሠርቶ ያሰግድ ነበር፡፡ በየግዛቱም፡– «ቄሣር ጌታ ነው» እየተባለ በመንፈስ ይሰገድለት ነበር፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖችም እንዲህ ያለ ክህደትና ንጉሣዊ ትእዛዝ ባለበት ዘመን ላይ ቄሣር ጌታ አለመሆኑን እያወጁ፡– «ኢየሱስ ጌታ ነው» በማለት ይመሰክሩ ነበር፡፡ ምስክርነቱ ግን የሕይወትንመሥዋዕትነት የሚጠይቅ፣ለእሳትና ለሰይፍ የሚዳርግ ነበር፡፡ «ኢየሱስ ጌታ ነው» የሚለው ቃል ዛሬ፣ ዛሬ ለአንዳንድ እምነት ተከታዮች ፉከራ፤ ለሰባኪዎቻቸው ደግሞ ስብከት ሲጠፋባቸው ጉባኤ ማድመቂያ መሆኑ ይገርማል፡፡በዘመኑ ዋጋ የሚያስከፍልምስክርነት ነበር፡፡ ዛሬም የቃል ሳይሆን የሕይወት ምስክርነት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ጌታ ሆኖ ከኃጢአት፣ ከሱስ አላቆኛል የሚል ምስክርነትያዘለ መሆን አለበት፡፡ምክንያቱም ያልተገዛንለትን አምላክ ጌታ ነው ብለን ቃል ብቻ በመመስከራችን አናከብረውምና፡፡ ቃላችን የሕይወታችንመግለጫ ሲሆን ክብር አለው፤ ቃላችን የሕይወት መሸፈኛ ከሆነ ግን ውርደት ነው፡፡
መግደላዊት ማርያም ለደቀ መዛሙርቱና ለመላእክቱ«ጌታዬ» በማለት መሰከረችለት፡፡ በርግጥም ከሰባት ጨካኝ ገዥዎች ያላቀቃት፣በፍቅር ሕይወቷን የለወጠላትጌታዋ ነበር፡፡ ለእርሷ ግን ጌታዋ ብቻ ሳይሆን መምህሯም ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን «ጌታዬ» ማለት ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ መምህሬ ማለት ግን ከባድ ነው፡፡ ፍጹም ራስን መስጠት ይጠይቃል፡፡ ኢየሱስ ከርስቶስንጌታ ማድረግ ለማኅበራዊትርፍም መልካም ነው፡፡ እርሱ ጌታ ሲሆንልን ከኃጢአት፣ ከሱስ እንላቀቃለን፡፡ ጤናና በሰዎች ዘንድ ከበሬታን እናገኛለን፡፡ ይህ ለራሳችን ጠቃሚ የሆነና እንደተከበርን እንድናልፍ የሚረዳን ነው፡፡ እርሱን መምህር ማድረግ ግን ለብዙዎች ጭንቅ ነው፡፡ ምክንያቱምበሚያሳየን የሕይወት ጎዳና መከተልን ይጠይቃልናነው፡፡ መግደላዊት ማርያም በርግጥም ከፍላጎቷ፣ ከወዳጆ  ይልቅ የጌታዋ ፈቃድ በሕይወቷ ይፈጸማልናመምህሬ አለችው፡፡ ክፉ ነገርን መተው ለጌትነቱ መገዛት ነው፡፡ ፈቃዳችንንለፈቃዱ መተውና በሚመራን መንገድ መከተል ግን ለመምህርነቱ መገዛት ነው፡፡ 
የመምህርን ወግ ብንመለከት የመግደላዊት ማርያም ቃል ይገባናል፡፡ መምህር፡
1-        የእውቀት አባታችን ነው ፡፡
2-        አለማወቃችንን የሚያግዝ ነው፡፡
3-        በሚመራን መንገድ የምንከተለውነው፡፡
4-        ጊዜአችንንና ዕድሜያችንን የምንሰጠውነው፡፡
5-        ቅጣቱን በምስጋና የምንቀበለውነው፡፡
6-        ወደ ቀጣዩ ደረጃ የሚያሸጋግረን ነው፡፡
7-        በፍቅር ፍርሃት የምንፈራውነው፡፡
8-        የማናፍረው ራሳችንን የምንገልጥለት ነው፡፡
9-        የማንሟገተው በሚመራን መንገድ የምንከተለው ነው፡፡
10-      ደስታው ደስታችን የሆነ፣ ማወቃችንን የምናረጋግጥበት ነው፡፡
መግደላዊት ማርያም «ረቡኒ» ስትለው አውቀዋለሁየምለው እውቀቴ፣ ዕድሜ ያስገነዘበኝ ነገር ሁሉ ያለወጠኝ፤ አንተ ግን ራሱን ከሚያስፈጽም ቃልህ ጋር ወደ እኔ የመጣህ፣ የለወጥከኝ መምህሬ ነህ ማለቷ ነው፡፡ የሕይወትን ሆሄ የቆጠርኩብህ፣ ኑሮና አገርን፣ ከሰው ጋር መግባባትንያስለመድከኝ ብርሃኔ ነህ ማለቷ ነው፡፡ መሳሳቴን የማይቀበለውን ግትር ማንነቴን በትዕግሥትና በፍቅር ቃላት የመለስክልኝ፣ ወድቃ ትማር ብለህ ያልተውከኝአባቴ አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡ በቀና ጎዳና የምትመራኝ የፍጻሜዬ አምላክ አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡ ሕይወትህንለእኔ የሰጠህ፣ ለክብርህ ሳትደራደር ከእኔ ጋር የሆንህ፣< span lang=”EN-US” style=”font-size: 14.0pt; line-height: 150{4b4da169c759b5946ddb3f317039cb2ea64d4fb7f78fe75ad0fe4f16b4d4e0da};”> እንደገና ፈጥረኸኝ ከእግርህ ሥር ያስቀመጥከኝ፣ ስለ ራሴ ስለ ዕድሌ ስለ ጉዳቴ ከማልቀስ ስላንተ ፍቅር ወደማልቀስ ክብር የመለስከኝ አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡ አለማወቄንያገዝህ፣ እኔ የማስፈልገው ለማያውቁትና ለሚስቱት ነው ብለህ ራስህን ስለ እኔ በፍቅር ያሰርክ፣ የገዛ ቃልህ አስሮህ ለእኔ የተዋረድህመምህሬ ነህ ማለቷ ነው፡፡ አለማወቄን ያገዝክልኝብዙ ዘመን የታገሥከኝ፣እስካድግና እስክለወጥተስፋ ያደረከኝ፣ የጠፋሁትንእኔን በቃልህ ትምህርት፣በእጅህ ተአምራት፣ በመስቀል ሞተህ የፈለከኝ መምህሬ አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡
የእጅህን ሳይሆን ራስህን የሰጠኸኝ፣ ሕይወትህንመዓዛ ያለው መሥዋዕት አድርገህ ያቀረብክልኝ አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡ ኑሮህና ሕይወትህን ለእኔ የገለጥህ፤ በእኔና ባንተ መካከል ያለው ማስተዋልናቅድስና እንደ ሰማይና ምድር ቢራራቅም ንቀህ ያላለፍከኝ፣ የሰው ማንነት የማይገርምህ፤ በፈረሰው በኩል ልቁምላችሁ የምትል መምህሬ አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡ በኑሮህ የማረከኝ፣ካለህበት ያኖርከኝ፣ከረቂቁ ማዕድህ ያሳተፍከኝመምህሬ ሆይ ማለቷ ነው፡፡ አለማወቄን እንደ ትላንትናዋ ቀን ያሳለፍክልኝ፣ የእኔን ፍጹም ኃጢአተኝነት ያንተን ፍጹም አዳኝነት የገለጥክልኝ መምህሬ አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡
በራሴ ማስተዋል ስደገፍ፤ ልከተልህ ሳይሆን ተከተለኝ ስልህ የኖርኩ ተላላ ፍጡርህ ነኝ፡፡ አሁን ግን ያንተ እውቀት ዋስትናዬ ነውና ማንነቴን ይዤ ቀርቤልሃሁማለቷ ነው፡፡ አውቃለሁ ማለቴ የአለማወቄ ውጤት መሆኑን፣ በዘላለማዊ ጥበብህ ፊት የእኔ ውስንነት ታይቶኛልና የጠቢባን ጠቢብ ሕይወቴን ያላንተ ለመምራት ከእንግዲህ አልደፍርም ማለቷ ነው፡፡ ድርቅና ድንቁርና መሆኑን ተገንዝቤ፣ አንተ ከከለከልከው ነገር ውስጥ ደግ ነገር እንደሌለ አምኜ «ለምንሳልልህ ልቀበልህ፣ «ወዴትሳልልህ ልከተልህ ወስኛለሁ ማለቷ ነው፡፡
ለእኛስ ኢየሱስ ክርስቶስ መምህራችን ነው? እርሱን መምህር ካደረግነው፡
እናከብረዋለን
                       — ይቀጥላል—
ረቡኒ
በዲ/ን አሸናፊ መኰንን
የመጀመሪያ እትም ሚያዝያ 2002 ዓ/ም
አድራሻ – 0911 39 35 21/0911 67 82 51
ፖ.ሳ.ቁ. 62552
አ.አ. ኢትዮጵያ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ