የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ስላለህ አለሁ!

እኔ አለሁ ጌታዬ፣ አንተስ እንደምን አለህ? ድሆች በረከትን፣ ግፉዓን ፍርድን ፣ ብቸኞች የመኖር ጉልበትን ይለምኑሃል። ቀኑ ያደከማቸው “ልበ ሰፊ ፣ ነገር አላፊ አርገኝ” ይሉሃል። ጥሩ ኑሮ ሳይሆን ጥሩ ሞት በሚናፈቅበት ዘመን መኖር ገራሚ ነው። ካንተ ካልሆነ ይህ ከወዴት ይገኛል? ሁሉ የሚገኝብህ መዝገብ ሆይ በመኖር ስለባረከኝ ተመስገን! ስጠራጠርህ እየታመንህልኝ ፣ በጠላቶች ጉልበት ልክ ስለካህ አንተ አልተቀየምከኝም። ፈራጅ የለም ስልህ አንተ ግን በማይናወጥ ዙፋን አለህ! ምን እልህ ይሆን? የፈጠርከውን ላልፈጠረ ጨካኝ አሳልፈህ አትስጠው። ዘመኑን ብቻ ሳይሆን እኛንም ለውጠን። ልብ ለልብ መገናኘት ተረት እንዳይሆንብን አስበን። ዓመቱን በሰላም አስፈጽመን! ምስጋናችን ይኸው ይድረስህ!

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ