መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » ቃለ በረከት

የትምህርቱ ርዕስ | ቃለ በረከት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

እግዚአብሔር  በሰፊ እጆቹ ያጥግባችሁ!

በመድኃኒት እጆቹ ይዳሳችሁ !

በኃያል ጣቶቹ ጠላትን ይጣልላችሁ!

በጸናው መዳፉ በፍቅር ይጻፋችሁ!

በማይነጥፍ እጆቹ ያርካችሁ!

በማይገፉ እጆቹ ይሳባችሁ!
ባሕር በከፈሉ እጆቹ ታሪካችሁን ይለውጠው!

ፀሐይን ባቆሙ እጆቹ ማታውን ማለዳ ያድርግላችሁ!

በመለኛ እጆቹ ከክፉ ወገን ያላቅቃችሁ!

ሰጥተው በማይረኩ እጆቹ ያትረፍርፋችሁ!

አዳምን በሠሩ እጆቹ እንደገና ይሥራችሁ!

ተዋጊ በሆኑ ጣቶቹ የበረታባችሁን ይጣልላችሁ!

ማልደው በሚሠሩ እጆቹ ዘመናችሁን ያትርፍላችሁ !

በማይጠቁሙ ጣቶቹ ይሸፍናችሁ!

በማይሰስቱ እጆቹ ይባርካችሁ!

በሠራተኛ እጆቹ ቤትን ይሥራላችሁ!

በፍቅር ጣቶቹ ለክብር ይጻፋችሁ!
በማይደክሙ እጆቹ እንደገና ይምራችሁ!

በማይለቁ እጆቹ አጥብቆ ይያዛችሁ!

ሞትን በሚያግዱ እጆቹ የሞት አዋጅን ይሻርላችሁ!

ድል ነሺ በሆኑ እጆቹ ማኅተሙን ይፍታላችሁ!

ጥያቄ መላሽ በሆኑ ጣቶቹ መረቡን ይበጣጥስላችሁ!

እሳትን በሚያበርዱ እጆቹ ሰላምን ይስጣችሁ!

ማዕበልን በሚያግዱ እጆቹ የመጣባችሁን ይመልስላችሁ!

ተሸንፈው በማይገቡ እጆቹ ድልን ያብስራችሁ!

ሳይታገሉ በሚጥሉ እጆቹ ኩራት ይሁናችሁ!

በማያዳሉ እጆቹ ጓዳችሁን ይሙላላችሁ!

የተገፋን በሚደግፍ እጆቹ በቀኑ ላይ ያሰልጥናችሁ!

በሚያጽናኑ እጆቹ እንባችሁን ያብስላችሁ!

ብቸኝነትን በሚያርቁ እጆቹ በእቅፉ ይሰውራችሁ!

በተቸነከሩት እጆቹ ጭንቀታችሁን ያርቅላችሁ!

ጥቂቱን ብዙ በሚያደርጉ እጆቹ የደስታ እንጀራ ይስጣችሁ!

አፍረው በማይገቡ እጆቹ ዘመን ይጨምርላችሁ!

በሚያገናኙ እጆቹ የይቅርታ ልብ ይስጣችሁ!

በሚያጎርሱ እጆቹ የበቃኝ ኑሮ ይስጣችሁ!

በሚባርኩ እጆቹ ቀኑ ላይ ይሹማችሁ!

ለምጻምን ባዳኑ እጆቹ መልካችሁን ይለውጥላችሁ!

ለጴጥሮስ በተዘረጉ እጆቹ ከውድቀት ያንሣችሁ!

በባለጸጋ እጆቹ የምትሰጡ ያድርጋችሁ!

የችንካር ምልክት ባላቸው እጆቹ የክፉ  ቀን ወዳጅ ያድርጋችሁ!

ድሪቶን በሚያስጥሉ እጆቹ የጽድቅ ሸማ ያልብሳችሁ!

ሕግን በጻፉ ጣቶቹ አዝማደ ሥላሴ ያድርጋችሁ!

አሜን አሜን አሜን ! በስመ ሥላሴ የጸና ይሁን! አሜን ላለው ሁሉ ይደረግለት ፣ ይህችን ቀን የመሻገር ቀን ያድርግለት።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ