የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የተሰጠ ስብከት/ክፍል 2/

“እነሆ ድንግል በድንግልና ትወልዳለች” (ኢሳ 7፥14)
ይህ ትንቢት የተፈጸመው በተነገረበት በአይሁድ መል ነው። ሆኖም ግን ትንቢት ሳይነገርልን ያመነው እኛ ነን። “እነሆ ድንግል በድንግልና ትወልዳለች” (ኢሳ 7፥14) የሚሉት ቃላት የምኩራብ ናቸው ነገር ግን ባለቤትነቱ የቤተ ክርስቲያን ነው ። ቤተ አይሁድ የድንጋይ ጽላት አገኙ ቤተ ክርስቲያን ግን ውድ የሆነውን ዕንቁ አገኘች ። ቤተ አይሁድ ጨርቁን አቀለሙት ቤተ ክርስቲያን ምራዊውን መጎናጸፊያ ለበሰች ። ይሁዳ ወለደችው ዓለም ተቀበለው ። ምኩራብ አጠባችው አሳደገችው ቤተ ክርስቲያን ተቀበለችው የአዝመራውንም ፍሬ ሐሤት አደረገችበት ። የወይን ረጉ ቅርንጫፍ ከቤተ አይሁጋር ነው የወይኑ ዘለላ እውነት ግን ከእኔ ጋር ነው ። ቤተ አይሁድ የወይኑን ዘለላ ሰበሰቡት አዛብ ደግሞ የምጢራዊውን መጠጥ ጠጡት ። ቤተ አይሁድ የዘር ቅንጣት በይሁዳ ዘሩ አዛብም በእምነት ማጭድ የምርቱን አዝመራ ሰበሰቡ ። አዛብ በጽድቅና በይማኖት ጽሬዳውን ቆረጡ ያለ ማመን እሾህ ግን አይሁድ ጋር ቀረ ። ጎጆው በሮ ሄደ ወላጆቹ ከጎጆው ጎን አንቀላፉ ። አይሁድ የፊደሉን ቅጠል ተረጎሙት ዛብ የመንፈስን ፍሬ ሰበሰቡት ። 
“እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች” (ኢሳ. 7፥14)አንተ አይሁድ ንገረኝ? በመጨረሻ ማንን እንደ ወለደች ንገረኝ? ሮድንስን እንዳመናችሁት እኔንም እመኑኝ ። ነገር ግን እኔን በሴራችሁና በድብቅ እቅዳችሁ ምክንያት እንደማታምኑኝ አውቃለሁ ። እናንተ እንዲገድለው ፈልጋችሁ ለእርሱ ነገራችሁት እኔ ግን እንዳመልከው አልነገራችሁኝም ። ድንግል ማንን ነው የወለደችው ? ማንን ነው ? የፍጥረትን ጌታ ። እናንተ ዝም ብትሉም ተፈጥሮ በኃይል ጮኾ ይናገራል ። እርሷ በፈቃዱ መወለየፈለገውን አስገኘችው ። ይህ ተአምር በተፈጥሮግ አይቻልም ።  ነገር ግን እሱ ምንም እንኳን ሰው ቢሆንም የተፈጥሮ ጌታ ስለሆነ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ይወለደ ዘንድ አዲስና እንግዳ የሆነ ልደት አስታወቀን ። ተፈጥሮንና ጋብቻን ድል ያደረገው እሱ ዛሬ ከድንግል ተወለደ ። የቅድስና ባለቤት ለሆነው ለእርሱ ንጹና ቅዱስ ከሆነ ምንጭ መገኘት ይስማማዋል ። አዳምን ከብዙ ጊዜ በፊት ከድንግል መሬት የፈጠረው እርሱ ነበር ሔዋንን ደግሞ ያለ ሚስት ከአዳም ራት ። አዳም ከጎኑ ሴት ለብቻው እንዳስገኘው ልክ እንደዚሁ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድ ልጅ ወለደች
ሱ ሰው ሆኗልና ማን ያውቀዋል ? ማንስ ይለየዋል ? ሴቶች ለሰው ዘር ሁሉ ዳ ስለነበረባቸው አዳም ያለ ሚስት ሴት እንዳስገኘ በዚህ ምክንያት ዛሬ ድንግል ያለ ወንድ ወለደችበሔዋን ቦታ ሁናም ለወንዶች የነበረውን ዳ ከፈለች ። አዳም ያለ ሚስት ሴት በማስገኘቱ ትዕቢተኛ እንዳይሆን ድንግልም ያለ ወንድ ወለደች በዚህም ተመሳሳይ በሆነው ተአምር የሁለቱን ተፈጥሮ እኩልነት ሳየ ። ከአዳም የጎን አጥንት ሲወስድ አዳምን በምንም ዓይነት መልኩ እንዳላሳነሰው በዚህ መልኩ ማኅተመ ድንግናዋን ሳይፈታ ለራሱ ድንግል ማፀን ውስጥ ያው የሆነ ማደሪያ ጎን ጥንቱ ከተወሰደ በኋም አዳም ሙሉ እንደ ሆነ ነው የቀጠለው ። ልክ እንደዚሁ ድንግልም ልጅ ከወለደች በኋላ ማኅተመ ድንግልናዋ አልተፈታም ። በዚህ ምክንያት ለራሱ የሚሆን ማደሪያ ከሌላ ቦታ አላመጣም ሌላ አካል ፈጥሮም አልተዋደም የአዳምን አፈርነት የሚዘልፍ እንዳይመስል የአዳምን ሥጋ ተዋሐደ
ሰው በሰይጣን ከተታለለ በኋየሰይጣን መሳሪያ ሆኖ ነበር በዚህ ምክንያት ከፈጣሪው ጋር ባለው ግንኙነረት ከሰይጣን ቁራኝነት ይለየው ዘንድ ተጥሎ የነበረውን ሕያው ማደሪያ መለሰው ሆኖም ግን ሰው ቢሆንም የተወለደው እንደ እግዚአብሔር ነው ። እሱ እንደ እኔ በተለመደ ጋብቻ ተወልዶ ቢሆን በብዙኑ ዘንድ እንደ ውሸት ይታሰብ ነበር ። ነገር ግን አሁን እንደሆነው በዚህ ምክንያት ነበር ከድንግል የተወለደው ። ይህ ተአራዊ የሆነ ልደት ለእኔ የታላቅ እምነት ምንጭ ይሆንልኝ ዘንድ ማፀኗን አልለወጠውም ኅተመ ድንግልናዋም እንዳይፈታ ጠበቀው ። ስለዚህ ግሪካዊ ወይም አይሁዳዊ በባርይው አምላክ የሆነው ክርስቶስ ከተፈጥሮ ግ በተቃራኒ ሰው ሆነ ወይ ? ብሎ ቢጠይቀኝ ያልተፈታውን ማተመ ድንግልናዋን ለክርክሬ ምስክርነት በመጥራት “አዎ” ብዬ እመልሳለሁ ። በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ከተፈጥሮ ግ በላይ መሆኑን አሳይቷል ። በዚህ መንገድ የማፀን ፈጣሪ የድንግልናም ምንጭ ነው ። ምክንያቱም ልደቱንየመወለዱን መንገድ ንጹአድርጎታል ራሱ በወደደው መንገድም ሊገለጥ በማይችል መልኩም ለራሱ ደሪያ አዘጋጀ
 ስለዚህ አይሁዳዊ ሆይ ንገረኝ ድንግል ወለደች ወይስ አልወለደችም ? ከወለደች ልዩ የሆነውን ልደት መስክር ። ካልወለደች ግን ለምን ሄሮድስን አታለልከው ? ሄሮድስ ክርስቶስ የት እንደሚወለድ ሲጠይቅ በይሁዳ ቤተ ልሔም እንደ ነበረ ነገረዋል ። እኔ መንደሩን ወይም ቦታውን አውቃለሁ? እኔ የተወለደውን የእሱን ጥቅም/ዋጋ አውቃለሁ ? ኢሳያስ እንደ እግዚአብሔር አልጠቀሰውም? እሱ እንዲህ ይላልና፡- “ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” (ኢሳ  7፥14) ። እናንተ የማትረቡ ጠላቶች እውነትን አታገናዝቡምን ? እናንተ ጉን አጥብቃችሁ የምትከተሉ ፀሐፍትና ፈሪሳያን ስለ እርሱ የሚነገሩትን ሁሉንም ነገሮች አትነግሩንም? እኛ ዕብራይስኛ እናውቃለን? መጻፍትን አትተረጉሙም? ድንግል ከወለደች በኋላ እና ከመውለዷ በፊት ስለ እግዚአብሔር የተነገረውን ሄሮድስ ሲጠይቃችሁ የተናገራችሁት ቃል እንዲያምናችሁ ነዩ ሚክያስን እንደ ምስክር አላመጣችሁምን ? እሱ እንዲህ ይላልና፡- “አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል” (ሚክ 5፥2) ። ነዩ ከእናንተ በተሻለ በደንብ አድርጎ ይናገራል ።
ሱ ከእናንተ መል ወደ ዓለም መጣ ጥንት የነበረው አካላዊ ቃል ሲመጣ ከዚህ ቀደም ያልነበረው ሥጋ ተፈጠረ ህልውም ሆነ ነገር ግን ዛሬ በአንድ በኩል ሰው እንደ መሆኑ ዝቡን እረኛ ሆኖ እየጠበቀ እንደ አምላክነቱ ደግሞ ዓለምን ለማዳን ዛሬ ተወለደ ። ኦ መልካም ጠላቶች! ኦ በጎ አድራጊ ከሳሾች! ሳታውቁ እግዚአብሔር በቤተ ልሔም እንደሚወለድ ያሳወቃችሁ በረት ውስጥ የተሰወረውን ጌታ የጠቆማችሁ፤ ዋሻ ውስጥ የተኛውን ሳትፈቅዱ የገለጣችሁት፤ ሳታውቁ የደገፋችሁን፤ እሱን ለመደበቅ እየፈልጋችሁ የገለጣችሁት (እናንተ መልካም ጠላቶች! በጎ አድራጊ ከሳሾች!)። አላዋቂ የሆኑ አስተማሪዎቻችሁን አያችኋቸው? የሚያስተምሩትን አይረዱትም የተራቡ ሲሆኑ ምግብ ይሰጣሉ የተጠሙ ሲሆኑ ው ያጠጣሉ ። ድሃ ሆነው ሳለ ሌሎችን ባለ ጸጋ ያደርጋሉ ።
የመወለዱ ነገር ድንቅ ነውና ፡ የበሉ ምጢር እንግዳ ነው ስለዚህ ኑ በል እናድርግ ኑ እናክብር ። ዛሬ ጊዜያዊው ባርነት ቀንበር ተሰብሯል ይጣን አፍሯልአጋንንት ሸሽተዋልሞት ተሸንፏልገነት ተከፍቷል ፣ እርግማን ጠፍቷል ፣ ኃጢአከመንገዳችን ተወግዷልስህተት ከእኛ ርቋልእውነት ተመልሷልየሃይማኖት ቃል ሁሉም ቦታ ተስፋፍቷል
ይቀጥላል
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ