የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ቅድስት ዓርብ/ቀዳም ሥዑር

ፌኒሎን ተመስጦውን እንደ ጻፈው

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ ሚያዝያ 10 ቀን 2012 ዓ.ም.
www.ashenafimekonen.blogspot.com
ቀዳም ሥዑር ከክርስቶስ ሞት እስከ ትንኤው ድረስ ያለውን ፤ ይህም ሥጋው በጨለማ መቃብር ውስጥ የነበረበት ጊዜ የሚወክል ነው ። በዚህ (የተመስጦ ጽፍ ውስጥ) ፌኒሎን የተባለ ፀሐፊ እግዚአብሔር የራሱን ይወት ነጥቆ ከኢየሱስ ሞቱ ጋር ኅብረት ያደርግ ዘንድ እንደሚሻ ይናገራል ። እግዚአብሔር ይህንን ራ በእኛ ይራ ዘንድ ስንፈቅድ እንዲህ (ይሆንልናል) ብሎ ይጽፋል፡- “የማይወሰን ፍቅር በእኛ ውስጥ ያፈቅራል፣ ፍቅራችንም የእግዚአብሔር የራሱን ጠባይና መልክ ይይዛል” . . . መልካም ንባብ!
*****
ዛሬ ወደ ሊናዬ የሚመጣው ኢየሱስ መከራ የተቀበለበት ሞትና እንደገና የሚቀጥለው ይወት ። ትንኤው ከሞቱ ያነሰ እውነት አይደለም ። ሞቱም ከቃይና ከመከራ ይወት ወደ ደስታና ሐሤት የሚደረግ ጉዞ ነው ። አዳኝ ሆይ ! አመልክሃለ፣ በመቃብር ውስጥ እወድሃለው ፣ በመቃብር ውስጥም ራሴን በአንተ አለብሳለው እሸፍንማለ። ከዚህ በኋላ ዓለም ትመለከተኝ ዘንድ አልሻም ። ከዚህ በኋላ ራሴንም እመለከት ዘንድ አልሻም ። ወደ ጨለማና ወደ ትቢያነት ወረድኩ ። ከያዋን ጋር ዳግም አልቆጠርም ። ሙታን ይርሱኝ ከእግራቸው በታችም ይረማመዱብኝ ! እኔ ሞቻለሁ ለእኔ የተዘጋጀልኝ ሕይወትም በእግዚአብሔር ዘንድ ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአለና።[1] 
እነዚህ ድንቅ እውነታዎች ናቸው። ። ስለዚህ “ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?” (ሮሜ 6፥3) የሚሉት የሐዋርያው ቃላት ትርጉም ምንድን ነው? በእኛ ይራ ዘንድ የሚገባው ይህ የክርስያንነታችን ምልክት የሆነው ይህ ሞት ወዴት ነው ? ይህ የመቃብር ቦታስ ወዴት ነው ?

እኔ እታወቅ ፣ እመሰገን ፣ ልዩና ዝነኛ እሆን ዘንድ መፈለጌ እንዴት ያለ ጨካኝነት ነው ? ለጎረቤቶቼ የሚያስቡበት አንዳች ነገር እጥ ዘንድ እፈልጋለሁ ፣ የጎረቤቶቼን ልብ እቆጣጠርና እሞላ ዘንድ ፣ ራሴን በስመ ጥርነትና በወዳጅነት ውስጥ ጣኦት አደርግ ዘንድ እፈልጋለ። በመዊያው ላይ የሚጤሰውን ትንሽ ዕጣን ከእግዚአብሔር መስረቅ የእግዚአብሔር የሆነውን መውሰድ ከሚሻና ራሱን ሌሎች ፍጡራን ላይ ጣኦት ማድረ በመሻት ነፍስን ከሚሰርቅ የረከሰ ተግባር ጋር ሲነጻጸር ምንም ነው
ውዱ እግዚአብሔር ሆይ ፣ ሰዎች እንዲወዱኝና በክብር እንደሚመለከቱኝ ራሴን ማፍቀርና መውደድ መቼ ነው የምተወው ? ፍቅር ላንተ ብቻ የተገባ ነው ። በአንተ ፣ ለአንተና ላንተ ካለኝ ንጹ ፍቅር ውጪ አንዳች ነገር ላለማፍቀር ቆርጫለሁ ። እንደ እንግዳና መጻተኛነቴ ንጹ ከሆነ ክርስቲያናዊ በጎነት ካልሆነ በስተቀ ራሴን አፈቅር ዘንድ አይገባኝም ። ሌሎች እንዲወዱኝና እንዲያፈቅሩኝ ስፈልግና ስሻ ማፈር አይገባኝምን ?
ከንቱ የሆነው ስሜታዊነቴ በክርስትና በጎነት ከሚገኘው ፍቅር አይረሰርስም። ጨለምተኛና አስከፊ የሆነው ኩራትና ትቢቴ “ይህ ፍትሐዊ አይደለም! በእርሱ ላይ አም!” ይላል ። እግዚአብሔር ሆይ ኩራትና ትቢቴን ቅጣው ። እኔ ካንተ ጋርና ላንተ ነኝና ከራሴ በተቃራኒ እሆናለ። ከከንቱነቴ በተቃራኒ ላለው ላንተ ክብርና ፍትህ እወግናለ። ራስህን የምታመልክ ከንቱ ፍጥረት ! ስለዚህ ከእግዚአብሔር ውጪ ምን አለህ ? ክርስቲያናዊ በጎነት ላይ ያልተመረተው የዚያ ደማቅ ብረትና የፍቅር ግንኙነት መጨረሻ ምንድን ነው ? እንዲህ ያለ ኢፍትዊነት ሲሰማንና እግዚአብሔር ለራሳችን እንዳናደርግ የከለከለንን ነገር ሌሎች ለእኛ ያደርጉልን ዘንድ ስንሻ እንዴት ክርስቲያናዊ በጎነትን እንሻለን
እግዚአብሔር በፍጡራኑ ላይ ፍቅርን አትሟል ። ፍቅርን እንዲህ እናደርገው ዘንድ ነው የእርሱ ፍላጎት ? እርሱ ማፍቀር እንችል ዘንድ አላደረገንምን ? ይህንን ያደረገልንስ እያንዳንዳችን ይህ ንጹ ፍቅር ካለው ብቸኛ ዓላማና ምክንያት ዘወር እንል ዘንድ ነውን ? እግዚአብሔር ሆይ እንዲህስ አይደለም! ሰዎች ያፈቅሩኝ ዘንድ አልሻም ። ሰዎች ላንተ ካላቸው ፍቅር የተነ በትንሹ ያብሩኝ ዘንድ ነው የሚገባው ። ጎረቤቶቼ ለእኔ ስላላቸው ፍቅር ካወቅሁና ከተሰማኝ ለፍቅራቸው አብዝቼ ያልተገባሁ እሆናለው ከእኔ ይወሰድ ዘንድም አብዝቼ እፈልጋለሁ
ጌታ ሆይ ይህ ስለ ዝና ሆነ ስለ ወዳጅነትም እውነት ነው ። እንደ ፈቃድህ ስጥ ውሰድም። ለአንተ ክብርን የሚሰጥህ ከሆነ ከራሱ ከይወት በላይ ለእኔ ውድ የሆነው ዝና ለእኔ እንደ መርገም ጨርቅ ይሁንብኝ [2]በመቃብር እንዳሉ ሙታን ሰዎች ደጋግመው ተላልፈውኝ ከሄዱ ፣ ሰዎች እንደ ምንም ከቆጠሩኝ ፣ ሰዎች ከጠሉኝ ፣ ሰዎች ከአንዳች ነገር ካላተረፉኝ ይህ ጥሩና መልክም ነው ። አሁንም በውስጤ ከነገሮች ጋር ያለ በፈቃድ የሆነ ቁርኝት፣ ዝናና ክብርን የማግኘት ስር የሆነ ፍላጎት በውስጤ ካለ ከክርስቶስ ጋር አልሞትሁም የትንኤው ይወት እየተካፈልኩ አይደለም [3]
ወደ አዲሱ ሰው ይወት የምንሻገረው ከክፋት ፍጹም መወገድና ከአሮጌው ሰው ብልሹ ይወት ሙሉ መጥፋት በኋላ ነው [4] ሁሉም ነገር መሞት አለበት ። ምቾት ፣ መጽናናት ፣ የአእምሮ ሰላም ፣ ጠንካራ ወዳጅነት ፣ ክብር ፣ ዝናና ስም እነዚህ ሁሉ መሞት አለባቸው ። ሁሉም ነገር መቶ እጥፍ ሆኖ ይሰጠናል ነገር ግን (አስቀድሞ) ሁሉም ነገር ይሞት ዘንድ ይገባዋል [5]ሁሉም ነገር ይዋ ዘንድ ይገባል ። በእኛ ዘንድ ሁሉንም ነገር ስናጣ ሁሉንም ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ እናገኘዋለን ። በእኛ ዘንድ የነበረን ንጽና የሌለው አሮጌ ሰዋችን በአዲሱ ሰውነት ንጽና ተመልሶ ይሰጠናል ። እሳት ውስጥ የሚገባ ብረት እውነተኛና ንጽ ርይውን እንደማያጣ በተቃራኒው ዝገቱና ቆሻሻቸው እንደሚነጥሩና እንደሚነጹ (በእኛም ዘንድ እንዲህ ነው) [6]
ውዱ እግዚአብሔር ! በዚህ ምክንያት በእኛ ውስጥ የሚቃትተውና የሚጸልው ያ መንፈስ ቅዱስ ራሱ በእኛ ውስጥ አብዝቶ ፍጹም በሆነ አፈቃቀር ያፈቅራል [7]ልባችን እንዴት አብዝቶ ታላቅ ይሆናል ፣ እንዴትስ አብዝቶ ቀናተኛ ፣ ቸርና ደግ ይሆናል ! በጠባብ ድንበር ተወስነን እንደ ደካማ ፍጡራን ነንና አናፈቅርም የማይወሰን ፍቅር በእኛ ውስጥ ያፈቅራል ፣ ፍቅራችንም የእግዚአብሔር የራሱን ጠባይና መልክ ይይዛል
ቃዩና ጣረ ሞቱ ወቅት፣ በሞቱና በመቃብሩ ውስጥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ራሳችንን አንድ ማድረግንና መተባበርን ብቸኛ ሳባችንና ዓላማችን አድርገን እንያዝ ። በንጹ ነት ራሳችንን በጨለማ ሌሊቶች እንቅበር ። ራሳችንን ለሞት ፍርሃትና ድንጋጤ አሳልፈን እንስጥ ። እኔ ራሴን እንደዚህ ዓለም ፍጥረት በፍጹም መመልከት አልሻም ። እኔ እየረሳሁት እንዳለ፣ ራሴንም መርሳት እንደምፈልገው ዓለሙ ይርሳኝ ! ጌታ ኢየሱስ የሞትው እኔ እሞት ዘንድ ብቻ ነው ይወቴን በኃይል ውሰድ ። ከዚህ በኋላ እተነፍስ ዘንድ አታድርገኝ ። አንዳች ነገር መልሼ እንድይዝ አታድርገኝ ። ልቤን እስከ መጨረሻው ድረስ ግፋት ። መቴ ላይ ገደብና ድንበር አላበጅም ። 


[1] በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና  . . . “ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና።” ቆሎ 3፥3
[2]የመርገም ጨርቅ . . . . “ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። ኢሳ 64፥6
[3] ከክርስቶስ ጋር አልሞትሁም . . . ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን። ሮሜ 6፥7-8
[4]አዲሱ ሰውና አርጌው ሰው . . . “ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22-24
[5]ሁሉም ነገር መቶ እጥፍ ሆኖ ይሰጠናል . . . ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥ አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም። ማር 10፥2930
[6]ከዝገትና ቆሻሻቸው እንደሚነጥሩና እንደሚነጹ . . . “ሦስተኛውንምክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ እኔም። ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።” ዛካ 13፥9
[7] በእኛ ውስጥ የሚቃትተውና የሚጸልያው . . . እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል” ሮሜ 8፥26።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ