የትምህርቱ ርዕስ | ቍጣ

ቍጣ ስሜታዊ እሳት ነው ። እሳት ሁሉ ጭስ አለው፣ የቍጣ እሳት ግን ጭስ የሌለው ቃጠሎ ነው። የሚቆጡ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን የሚል ስሜት የሚከተሉ ሲሆኑ አብረዋቸው የሚኖሩት ያላመኑበትን ነገር እሺ እያሉ ይኖራሉ። ቊጠኛው የደከመ ቀን በብዙ ወቀሳ፣ በመለየት ይቀጡታል። ቍጣ የዕድሜን ሠርክ ያበላሻል። ሰው ሁሉ ለሰላሙ ዋጋ ይከፍላል፣ ሰው ሁሉ ነጻነቱን ይወዳል። ቍጠኛ ሰው ሰላም የሚነሣ፣ ነጻነት የሚያሳጣ በመሆኑ ብቸኛ እየሆነ ይመጣል። እንዴት ተከዳሁ ብሎ የሸሹትን ስለሚከተል ቍጣው ተበቃይ ያደርገዋል። ብዙ ጊዜ ቍጠኛ ሰዎች ውስጣቸው ተንኮለኛ አይደለም። ከመጠን በላይ ከእኛ መጠበቃቸውና ፍጹም እነርሱን እንድንመስል በመፈለጋቸው ነው :: ቍጣቸው ራሳቸውንም የሚጎዳ በመሆኑ ሲበርድላቸው በጸጸት ይንገላታሉ። ሰዋዊ ኩራታቸው ይቅርታ እንዳይጠይቁ ያደርጋቸዋል :: ስለዚህ ከጸጸት ስሜታቸው በኋላ አኩራፊ ይሆናሉ።

ቍጣ ውሳጣዊና ውጫዊ ነው። ያለ መሸነፍ ስሜት ያላቸው ሰዎች አምቀው ራሳቸውን ይጎዳሉ ፣ ለበሽታ ይዳረጋሉ። ቍጣቸው የሚያመልጣቸው ብርቱ ጯኺ ፣ ተሳዳቢ ፣ ዱለኛ ይሆናሉ። ቍጣ ወደ ወንጀል የሚወስድ ነው። አጠገባችን ያሉት አልምጥ ሰዎች በራሳችን እሳት ስንነድ ማየት ያስደስታቸዋል :: እኛን በማስቆጣት ጻድቅ ለመምሰል ይሞክራሉ። በራሳችን ላይ ብንቆጣ ትርፍ የለውም፣ የተሰጠንን እየኖርን ነውና። ነጻ ፈቃዳችን ለጽድቅና ለኃጢአት እንጂ አኗኗርንና ምቾትን ለመምረጥ አይሆንም :: በሰዎች ላይ ብንቆጣም ሰዎች የተፈጠሩት የእኛን ፍላጎት ለማሟላት ሳይሆን ለፈጠራቸው እንዲኖሩ ነው። አንዳንዴ እኛ ያቃተንን እነርሱ ፈጽመውት ድካማችንን መበቀል እንፈልጋለን። ያ ሲያቅተን ተስፋ እንቆርጣለን። ቍጣ ለቀቢጸ ተስፋ ይደርጋል።

ቍጣ ዕለታዊ ስሜት ሊሆን ይችላል፣ ቍጣ ሕይወታችን ከሆነ የማይጠፋ እሳት ተሸክመን እንኖራለን:: ይልቁንም በዚህ ዘመን እንኳን ቍጣችን ፍቅራችን የሚከብደው ትውልድ መጥቷልና ሌሎችን ለመለወጥ ከመነሣታችን በፊት ራሳችንን መለወጥ አለብን :: ያ ጊዜ ትዕግሥተኛ እንሆናለን።

ይቀጥላል

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ