የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ስብከት አምስት

የተባረከው ሐዋርያ ጳውሎስ የመንፈስ ጸጋ ስለሆነው ስለ ሰማያዊ ብትና ይህንን ለማግኘት ስለሚገጥመን ታላቅ መከራ ሲገልጥና ሁላችንም በዚህ ይወት ምን ለማግት መጣር እንዳለብን ሲናገር እንዲህ አለ “ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና” (2ቆሮ.5፥1) ። ስለዚህ ሁላችንም በሁሉም ዓይነት ጸጋዎች መጣርና መታገል ሰማያዊውንም ቤት እዚህ ማግኘት እንደምንችል ማመን ግድ ይለናል። የሰውነታችን ቤት ከጠፋ ነፍሳችን ምትመለበት ሌላ ቤት የለንም። “ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም” (2ቆሮ.53) ራቁት ማለት ከመንፈስ ቅዱስ ብረትና ስምረት መነጠል ማለት ነው። በዚህ ምክንያት እውነተኛ ክርስያኖች የሆኑ ክርስያኖች ከጋቸው ሲለዩ/ሲሞቱ በደስታ የሰማዩን መንገድ ይጀምራሉ። ምክንያቱም በእጅ ያልተራ ቤት ስላላቸው ነው ። ይህም ቤት በእነርሱ ሚያድረው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው ። ስለዚህ የሥጋ መኖሪያቸው ቢጠፋም ምንም የሚያስፈራቸው ነገር የለም ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ የሆነው ሰማያዊ ቤትና የማይጠፋው ክብር ስላላቸው ነውይህም ክር በትንጊዜ ሥጋ ለሆነው ሰውነታችን ይወትንና ክብርን የሚሰጥ ነው ። ሐዋርያው እንዲህ አለ፡- ”ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል(ሮሜ 8፥11) ዳግመኛምእንዲህ አለ፡- “የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ” (2ቆሮ 4፥11)“በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ” ( 2ቆሮ 5፥4)
                                                                                                                                                                                         
8. እንግዲህ በእምነትና በመልካም አኗኗራችን እዚሁ ምድር ላይ ሳለን ያንን ልብስ ለማግኘት እንጣር ። በኋለኛው ይወትም ከሥጋችን ስንለይ ርቃናችንን እንዳንሆን ሰውነታችንንም የሚያስጌጥ አንዳች ነገር እንዳናጣ እንትጋ ። ሁሉም ሰው በእምነትና ትጋት በእኩልነት የመንፈስ ቅዱስ ተካፋይ እንዲሆን ስለተፈቀደለት በዛ በፍርድ ቀን ሰውነቱም ይከብራል። አሁን ነፍስ በውስጧ ያከማቸችው በዚያንጊዜ በውጫዊው ሰውነታችን ይገለጣል ። ልክ በክረምት ወቅት ውያገኙ ዛፎች በማይታየው ፀይና ነፋስ ሲሞቁ ከውስጣቸው እንደሚያወጡትናሚያለብሳቸውም ቅጠል እንደሚያብብበዚህ ወቅትም አባዎች ከምድር እቅፍ እንደሚወጡ በዚህም ምድር እንደምትሸፈንና እንደምትለብስ ሁል ጊዜ ምናየው እውነት ነው። ይህም የምድር አበባ ጌታ እንዲህ ብሎ የገለፀው ነው፡-“ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም” (ማቴ 6፥29)ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ክርስያኖች በትንኤ ለሚያገኙት ክብር ምሳሌዎች ናቸው
                                                                                                                                                                                             
9. ስለዚህ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ነፍሳት ሁሉለእውነተኛ ክርስቲያኖች መስከረም የተባለ የመጀመሪያ  ወር ይመጣላቸዋል ይህ ቀን የትንኤ ቀን ነው በእውነተኛው ፀይ ኃይልም የመንፈስ ቅዱስ ክብር ከውስጥ ይወጣልበቅዱሳኑ አስቀድሞ የነበረው ነገር ግን በነፍሳቸው ተደብቆ የኖረውን  ክብር  በመግለጥ ሰውነት እያስጌጠና እየሸፈነ ይመጣል ። ሰው አሁን ያለው ነገር በዚያንቀን በውጭ ሰውነት ይገለጣል ። መጽሐፍም ስለዚህ ወር እንዲህ ይላል፡-“ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ” (ዘፀ 12፥2)ይህም ለሁሉም ፍጥረታት ደስታን ያመጣልምድርንም በመክፈት የተራቆቱትን ዛፎች ያለብሳል ለፍጥረትም ደስታንና ፍንደቃን ያመጣል ። ይህ ለክርስቲያኖች የመጀመሪያው ወርየትንኤ ጊዜ ሰውነታቸው አሁን በውስጣቸው ባለው ከቃላት በላይ በሆነው ብርሃን ማለትም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚከብርበትና የሚያጌጥበት ነው ። ይህም ክብር ለእነርሱ የሚበላየሚጠጣየደስታሴትየሰላምየዘላለም ይወት ካባና መጎናጸፊያ ይሆናቸዋል ። አሁን በቅምሻ ለመቀበል የታደሉትን ክብር በዚያን ጊዜ በምልአት ሁሉንም የብርሃን ውበቶችና ሰማያዊ ድምቀቶች ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይቀበላሉ
                                                                                                                                                                                          
10. እንዲህ ከሆነ እንዴት ሁላችንም በማመን መታገል በመልካም አኗኗር ስፋና በትት ሰማያዊውን ኃይል አሁን ለመቀበል የተገባን እንድንሆን ሥጋችን ሲሞት የምንለብሰውን የመንፈስ ቅዱስን ክብር በነፍሳችን ውስጥ  ለማግኘት አንፈልግም ? እንዲህ ከሆነ፡-“ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም” (2ቆሮ.5:3)“ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል” (ሮሜ8፥11) የሚለው ቃል ይፈጸምልናል ። ሙሴም ማንም ሰው አትኩሮ ሊያየው በማይችለው ፊቱ ላይ በነበረው የመንፈስ ቅዱስ ክብር ይህንን በምሳሌ አሳይቷል ። በጻድቃን ትንኤ ቀን የተገቡ ሁነው የተገኙት የእነዚያሰውነት እንዴት አይከብር ? ነገር ግን ይህ ክብር አሁን በቅዱሳንና በአማኞች በውስጣዊ ሰውነታቸው እንዲኖር የተሰጣቸው ነውዘመኑም ሲፈጸም በሙላት ይገለ ። መጽሐፉ፡-“እኛ ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት” ሲል በውስጣዊ ሰውነታችን ለማለት ነው ይህን ካለ በኋ   እንዲህ ይላል፡-“የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን” (2ኛ ቆሮ 3፥18) ። በተመሳሳይ መልኩ ሙሴ በመጽሐፍ እንደ ተጻፈው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንጀራ ሳይበላ ውም ሳይጠጣ በተራራው ላይ ነበር ። ሥጋ መንሳዊ ምግብ ካላገኘ በቀር የቅዱሳን ነፍስ በመንፈስ የሚመገየመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ካላገኘያለ ምግብ ረጅም ጊዜ መኖር አይችልም ።                                                                                                                                                                                 
11.የሙሴ ይወት በሁለት መንገድ ክርስያኖች የሚገኙትን ብርሃን ያሳያል ። ይህ ከመንፈስ ቅዱስ የሆነው የብርሃን ክብር እውነተኛ ክርስቲያኖች አሁን በዚህ ይወት ሳሉ የተሰጣቸውን በትንኤም ጊዜ በሙላት የሚኖራቸውን ቁሳዊ ያልሆነ መንፈሳዊ ደስታ በዚያንጊዜ በሰውነታቸው ሁሉ እንደሚገለጥ ያሳያል ። አስቀድመን እንዳልነው ቅዱሳን አሁን በነፍሳቸው ያላቸው ክብር እርቃነ ሰውነታቸውን ይሸፍናል ወደ መንግተ ሰማያትም ያስገባቸዋል ይህም ከሆነ በኋላ ሥጋና ነፍሳችን በመንግተ ሰማያት ከጌታ ጋር ያርፋሉ ። እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥረው እንደ ወፎች ያለ ክንፍ አላበጀለትም ነገር ግን በትንኤ የሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ክንፍ አዘጋጅቶለታል ። ይህም ክንፍ መንፈስ ቅዱስ እንደ ወደደ ከፍ እንዲያደርገውና እንዲይዘው ያደርጋል ። የቅዱሳን ነፍሶች ይህ ጋ እንዲኖራቸው የተገቡ ሲሆኑ በሰማያዊው የሳብ መቃን ውስጥ ገብተው እንዲከንፉ ያደርጋቸዋል ። ክርስቲያኖች የራሳቸው የሆነ ሌላ ዓለምሌላ የማዕድ ጠረጴዛሌላ ልብስሌላ የደስታ ዓይነትሌላ ብረትሌላ የአስተሳሰብ መንገድ አላቸው በዚህም ምክንያት ከዓለማያን ሰዎች ይበልጣሉ ። የነዚህንም ነገሮች ኃይል በመንፈስ ቅዱስ አሁን በነፍሳቸው አለ ስለዚህ በትንኤ ሰውነታችው ዘላለማዊ ከሆነው የመንፈስ ቅዱስ በረከት ይካፈላል ።በምድርም ሳሉ ነፍሳቸው በቅምሻ ካየችው ከዚህ በረከት ጋር ይዋዳሉ                                                                                                                                                                                            
12. ስለዚህ ሁላችንም መታገልመከራን መቀበልለተሰጡን ጸጋዎችም መጠንቀቅማመንጌታም መንፈሳዊ ሕይወታችንንአሁንና እዚህ ምድር ላይ የክብሩ ተካፋይ እንዲሆን ያደርገው ዘንድ ፣ ነሳችንም ከመንፈስ ቅዱስ ቅድስና ጋር ብረት እንዲኖራት እርሱን መማጸን አለብን ። በዚህም ከክፉ ርኩሰታችን እንድንነጻ ፣ በትንኤም ሰውነታችን ርቃኑን ሲነየምንሸፍንበት ብት እንዲኖረን በዘላለማዊው መንግት መልካምነትን በማጎናጸፍእንድናነቃቃውና እንድናድሰው ያስችለናል ። በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ እንደ ተጻፈው ክርስቶስ ከሰማይ ወርዶ ከመጀመሪያው ጀምሮ ያንቀላፉትን የአዳም ዘሮች ሁሉ ያስነና የተነትንም ለሁለት ይከፍላቸዋል ። የእርሱ ምልክት ማለትም የመንፈስ ቅዱስ ማተም ያላቸው የራሱ ስለሆኑ ወደ እርሱ ይጠራቸውና በቀኙ ያስምጣቸዋል ጌታ እንዲህ አለ ፡- ”በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል“ (ዮሐ 10፥14፤17) ። የነርሱም ሰውነት ከመልካም ራቸው የተነበመለኮታዊ ክብር ይደምቃል በመንፈስ ቅዱስም ክብር ይሞላል ጌታን በአየር ለመቀበል ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፡- ፍጻሜ በሌለው ዘላለም ከጌታ ጋር  ሁነን እየተደሰትን እንኖራለን አሜን
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ