የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ስብከት ሦስት

ወንድሞች በቅንነት በፍቅርና በሰላም ቀላል ይወት መኖር እንዳለባቸውና ከውስጣዊ ሳቦቻቸው ጋር መከራከርና መዋጋት እንዳለባቸው የተሰጠ ትምህርት
ወንድሞች በኅብረት ሲኖሩ በችሮታበመተዛዘን መኖር አለባቸው ። ሲጸልዩም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነቡ ደግሞም የትኛውንም ይነት ሥራ ሲሩ የጋራ መተዛዘንችሮታ ሊያሳዩ ይገባል ። በዚህ መልኩ እነዚህ የተለያዩ ዓይነት ዝንባሌዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኛሉ። የሚጸልዩትም ሆነ የሚያነቡት ደግሞም ሥራ የሚሩት በጋር በቅንነት ሆነው ቀላል ይወት መኖር ይችላሉ ። በመጽሐፉ ላይ ምን ተብሎ ነው የተጻፈው? “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” (ማቴ 6፥10)። በሰማይ ያሉት መላእክት በብረት ሆነው በስምምነትበሰላምና በቅንነት እንደሚኖሩ በእነሱ መካከልም ኩራትምቀኝነት እንደሌለ ወንድሞም በብረት እንዲሁ መኖር ይገባቸዋል ላሳ የሚሆኑ መነኮሳት በአንድ ላይ ይኖራሉ ሁሉም ቀንና ሌሊቱን መሉ አንድ ሥራ ላይ ብቻ መጠመድ አይችሉም። አንዳንዶቹ ለስድስት ሰዓታት ከጸለዩ በኋላ ማንበብ ይፈልጋሉ አንዳንዶቹ ለማገልገል ዝግጁፈጣን ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከባድ ራ ለመራት ዝግጁፈጣን ናቸው
ወንድሞች በምንም ዓይነት ራ ላይ ቢሆኑም እርስ በእርሳቸው በሰላምና በመተዛዘን ሊኖሩ ይገባችዋል ራው ሚጸልየውን እንዲህ ይበለው “ወንድሜ የሚያገኘው መንፈሳዊ ስጦታ የጋራችን ስለሆነ የእኔም ነው።” የሚጸልየውም አንባቢውን እንዲህ ይበለው፡- “አንብየሚያገኘው ትርፍ ለእኔም ይጠቅማል።” የራም እንዲህ ይበል፡-ራው ራ ለሁሉም የሚጠቅም ነው። “አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት” (1ቆሮ 12፥12) አካላቱም የየራሳቸውን ሥራ ይራሉ በተቃራኒው ደግሞ እርስ በእርስ ይተጋገዛሉ ። ዓይን ሁሉንም ወክሎ ያያል እጅም ሁሉንም ወክሎ ይራል። እግርም ሲራመድ ሁሉን ተሸክሞ ይጓዛል አንኛውም የሰውነት ክፍል ሲታመም ሁሉም ይታመማሉ ።ስለዚህ ወንድሞችም እርስ በእርስ እንዲህ ይሁኑ። የሚራው የሚጸልየውን እንደርሱ ስላልራ አይፍረድበት “እኔ ስለፋ ይጋደማል” አይበለው። የሚራው ማንም ላይ አይፍረድ ነገር ግን ሁሉም ማንኛውንም ዓይነት ራ ሲራውን ለእግዚአብሔር ክብር ያድርግ ። የሚያነበው የሚጸልየውን “የሚጸልየው ለእኔ ነው” ብሎ በማሰብ በሰላምና በደግነት ይቀበለው። የሚጸልየውም ስለሚራው የሚራው ለሁላችንም ጥቅም ነው” ብሎ ያስብ
በዚህ ሁኔታ ስምምነትና “በሰላም ማሰሪያ” የሆነ ብረት አንድ ላይ ሆነው ቅንቀላልለእግዚአብሔርም ያደላ ይወት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል ። በዚህ ሁሉ መል የማያቋርጥ ጸሎት ዋና ነገር ንደሆነ የታመነ ነው ። አንድ አስፈላጊ ነገር አለ ። ይህም ሰው ለነፍሱ ብት ማከማቸትና ጌታን ሁልጊዜ ማሰብ ያስፈልገዋል ። በየትኛውም ሁኔታ ሲራ ይሁን ሲጸልይ አልያም ሲያነብ የማይጠፋውን ብት ሊይዝ ግድ ይለዋል ። ይህም መንፈስ ቅዱስ ነው
እንዲህ የሚሉ ጥቂት ሰዎች ጌታ ከሰዎች የሚፈልገው የሚታየውን ፍሬ ብቻ ነውየማይታዩትን ነገሮች ማነለእግዚአብሔር የሚተው ነው። ይህ ግን እውነት አይደለም ። አንድ ሰው ከሌላ ሰጋር ያለውን ግንኙነት ሲጠብቅ በውስጥ ከሳቡ ጋር መዋጋትን ይቀጥላል ። ጌታ ምኞትህን እንቢ እንድትል ፣ ሳብህም ጋር እንድትዋጋ በውስጥህም ከሚነት ከንቱ ሳቦች ጋር እንዳትስማማና እንዳትደሰትባቸው ይጠብቅብሃል
ነገር ግን ኃጢአትንና ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ክፋትን ከሩ ነቅለን መጣል የምንችለው በመለኮታዊ እገዛ ነው። ሰው በራሱ ብቃት ኃጢአትን ነቅሎ መጣል አይቻለውም። ከኃጢአት ጋር መታገሉመዋጋቱቡጢ መቀበሉና መሰንዘሩ ያንተ ድርሻ ሲሆን ከሩ ነቅሎ መጣል ግን የእግዚአብሔር ድርሻ ነው ። ኃጢአትን ከር ነቅሎ መጣል ቢቻልህ ኑሮ ቀድሞውኑ የጌታ መምጣት ለምን አስፈለገ ? ዓይን ያለ ብርሃን ማየት እንደማይችለውያለ ምላስም መናገር እንደማይቻልያለ ጆሮም መስማት እንደማይቻልያለ እግርም መራመድ እንደማይቻልእጅም መራት እንደማይቻል ልክ እንደዚሁ ያለ ኢየሱስ መዳን ሆነ ወደ መንግተ ሰማያት መግባት አይቻልም ። “በውጫዊ ተግባር ዝሙት አልራሁም ወይም አላመነዘርኩም አንዳችም አልተመኘሁምና ጻድቅ ነኝ” ካልክ ተሳስተሃል ።ምክንያቱም ይህንን በማሰብህ ብቻ ሁሉንም ፈጽመሃቸዋል። ሰዎች ራሳቸውን መጠበቅ ያለባቸው ከሦስት የኃጢአት ዓይነቶች ብቻ አይደለም። ኃጢአት ብዙ ሺመልክ አለው ። ትዕቢትከልክ በላይ የሆነ በራስ መተማመንአለማመንቁጣቅናትማታለልግብዝነት ታድያ እነዚህ ከየት ናቸው? አንተ ከነዚህና እነዚህን ከመሳሰሉ ብዙ ኃጢአቶች ጋር በማይታየው ሊናህ ውስጥ መታገል የለብህምን ? ቤት ውስጥ ሌባ ካለ አንተም አንድ ጊዜ ከተጨነቅህ ድጋሚ ረፍት አታገኝምና አንተም ማጥቃት ትጀምራለህ ብጢዎችንም ትሰነዛዘራላችው ። ልክ እንደዚሁ ነፍስም መልሳ ማጥቃትመታገልና ኃይልን በኃይል መመከት አለባት።
ይህ ከሆነ በኋላ ምን ይከተላል ? ነፍስ በመታገልበመሰቃየትና በመጎዳት ውስጥ ስታልፍ ፈቃዳችን ትልቁን ድርሻ እየያዘ ይመጣል ። ይወድቃል ደግሞም ይነ ። ኃጢአት በሃያና በላሳ ግጭቶች መልሶ ይጥለዋል ። ኃጢአት ነፍስን ያሸንፋትና ይጥላታል ነፍስም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአንድ ፍልሚያ ኃጢአትን ያሸንፈዋል ። ነፍስም ይህንን ድል ማስጠበቅና አለ መዋዠቅ ከቻለች የድልንም ዋንጫ ከኃጢአት መንጠቅ ትችላለች ። ነገር ግን ሰው እዚህ ደረጃ ላይ ሆኖ ቢመረመር “ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ” (ኤፌ 4፥13) እስኪደርስ “የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው” (1ቆሮ 15፥26) ተብሎ እንደ ተጻፈው ሞትንም ሙሉ በሙሉ እስኪያሸንፍ ድረስ አሁንም ለእርሱ ኃጢአት ከባድ ነው ። ነገር ግን አስቀድመን እንዳየነው አንድ ሰው፡-  “ዝሙት አልፈጽምምገንዘብም አልወድምና ይህ በቂ ነው” ካለ ሁለት ኃጢአትችን ተቋቁሟል ነገር ግን ከዚህ ሌላ በሆኑ ኃጢአት ነፍስ ላይ በሚያመጣቸው ሃያ የኃጢአት ፈተናዎችን አልተቋቋመምና ይሸነፋል ። ሰውየው ሁሉንም ተቋቁሞ ሊታገል ስፈልገዋል ። ብዙ ጊዜ ደጋግሜ እንደ ተናገርኩት አእምሮአችን ከኃጢአት እኩል የሆነ ተፋላሚ ነው ከኃጢአት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ይልም ስላለው ኃጢአት የሚመጣውን ምክር ለመቋቋምና ለመመከት አቅም አለው
አንተ ተቃራኒው ኃይል በጣም ጠንካራ ነው ይህ ክት ሰው ላይ ሙሉ ልጣን አለውብለህ የምታስብ ከሆነ እግዚአብሔር ሰዎችን ለሰይጣን ፈቃድ በመገዛታቸው ሲፈርባቸው ሐሰተኛ ታደርገዋለህ ምክንያቱም ሰይጣን ኃይለኛና አስገድዶ የማነፍ ሥልጣን አለው ብለህ ተናገረሃል ። “ሰይጣንን ከነፍስ በላይ ታላቅና ኃይለኛ አደረከውና እኔን እንዲህ ብለህ ታዘኛለህ” “ለእርሱ አትሸነፍ” ። ይህ ማለት አንድ ሕጻን ልጅ ከወጣት ጋር እንዲታገል ከተደረገ በኋላ ሲሸነፍ በመሸነፉ ይፈረድበታል ማለት ነው ። ይህ ታላቅ ኢፍትዊ ነው ። እንግዲህ የሰው አእምሮ ከጠላት ጋር የተመጣጠነና የተስተካከለ ነው ። ይህን ዓይነት ነፍስ በምትሻበት ጊዜ ድጋፍ ስለምታገኝ ድነት ታገኛለች ። ውጊያውና ትግሉ በማይመጣጠኑ አካሎች መካከል አይደለም ። አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስን ለዘለዓለም እናመስግን አሜን።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ