የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ኢየሱስ በዚያ ጊዜ ውኃውን ወይን እንዳደረገው ያን ጊዜም ዛሬም ድካማችንን ፣ የማይረጋውን ፈቃዳችንን መቀየርን አላቋረጠም ።

ዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለት ሲተረጉም የሰበከው ስብከት
የክርስቶስ የተአምራቱ/የምልክቱ ራዎች እንዲህ ያሉ ናቸው ። ተአምራቱ/ምልክቱ በተፈጥሮ ከሚሆኑት ነገሮች በበለጠ የተሟሉና የተሻሉ ናቸው ። ይህ ነገር በሌሎች አጋጣሚዎችም ታይቷል ። እርሱ የታመመን የሰውነት ክፍል ሲፈውስ ቀድሞ ከነበረው በላይ የተሻለ ያደርገዋል ። የተለወጠው ወይን ምርጥ ወይን ነበር ። ይህንንም አገልጋዮቹ ብቻ ሳይሆኑ ሙሽራውና አሳዳሪውም መስክረዋል ይህም በክርስቶስ የሆነ ነበር ።
ኢየሱስ በዚያ ጊዜ ውውን ወይን እንዳደረገው ያን ጊዜም ዛሬም ድካማችንን የማይረጋውን ፈቃዳችንን መቀየርን አላቋረጠም ። ከውየማይለዩ (ከውየተለየ ማንነት የሌላቸው) ቀዝቃዛ ፣ ደካማ የሆኑ ያልተረጋጉም ብዙዎች አሉ ። እንዲህ ያለ ባይ/ማንነት ያላቸውን ፈቃዳቸውን ወደ ወይን ይቀይረው ዘንድ ወደ ጌታ እናቅርባቸው ። እነሱም ከዚህ በኋላ ጥንካሬ የጎደላቸውልፍስፍስደካማሰነፍ እንዳይሆኑ ነገር ግን ጠንካራ ሆነው በመቆም ለራሳቸውና ለሌሎች የደስታ ምንጭ ይሆናሉ ። ነገር ግን እነዚህ ቀዝቃዛዎች ማን ሊሆኑ ይችላሉ ? እነሱ ልባቸውን ለዚህ ለሚያልፈው ዓለም አብለጭላጭ ነገር የሰጡ ፣ የዚህን ዓለም ብት ያልናቁ ፣ የክብርና የልጣን ወዳጆች የሆኑ ናቸው ። እነዚህ ነገሮች ሁሉ (አንድ ቦታ) የማይረጉ እንደሚወርድ ውወደ ገደል በይል የሚፋጠኑ ናቸው ። ዛሬ ብታም/ባለ ጸጋ የሆነው ነገ ድሃ ይሆናል ። አንድ ቀን መልካም ዜናን ፣ ሰረገላና ብዙ ተከታዮች የነበረው (ሰው) በቀጣዩ ቀን ጨለማ ቤት ይኖራል ። እንደገና ሆዳምና ብኩን የሆነው ሰውም ራሱን እስኪፈነዳ ድረስ ከሞላ በኋላ ለአንድም ቀን በጣፋጩ ምግብ ያገኘውን ጣም ማቆየት አይችልም ። ነገር ግን ይህ ካለቀ በኋላ ይህንን ለማደስ ተጨማሪ ምግብ ለመብላት ይገደዳል ። በዚህም ከጎርፍ/ከወራጅ ውኃ በአንዳችም ነገር አይለይም ። ጎርፍ/ወራጅ ውላይ የመጀመሪያው ከሄደ በኋላ በተራው ሌላው ይከተላል ።
ሆዳምነት ላይም እንዲሁ ነው ። አንዱ ገበታ ካለቀ በኋላ ሌላ እንድንፈልግ ግድ ይለናል ። የምድራዊ ነገሮች ጠባይና ድልም/ጣም እንዲሁ ነው ። ፈጽሞ አይረጋጋም ነገር ግን ሁልጊዜ ይፈሳል ይፋጠናል/ይቻኮላል ። ነገር ግን ብት ላይ መፍሰሱና መጣደፉ ብቻ ሳይሆን ሌላም ብዙ የሚያስቸግሩ የሚያደክሙ ነገሮች አሉ ። በሚፈጥረውም ሁከት የሰውነትን ጥንካሬ ይሸረሽራል ፣ ነፍስንም ከመልካምነቷ ይለያታል ። ብትና የማያቋርጥ ምኞትም የጤናችን ድንበር ጠራርገው እንደሚወስዱት የባሮች ኃይለሞገድ እንኳን ዳርቻዎቻቸውን በቀላሉ ሸርሽረው እንዲሰምጡ አያደርጉም ።
ወደ ሐኪም ቤት ሄዳችሁ ብትጠይቁት አብዛኛዎቹ በሽታዎች በዚህ ምክንያት እደሚመጡ ይነግችኋል ። በልክ የሆነ ይወትና የተመጠነ ማዕድ የጤናዎች ሁሉ እናት ነች ። ስለዚህ ሐኪሞች ፡- አለመጥገብን ጤንነት ብለውታል ። ምክንያቱም በምግብ አለመጥገብ ጤንነት ስለሆነ ነው። የተመጣጠነ ማዕድንም የጤንነት እናት ብለዋታል ። አሁን የተመጠነ ፍላጎት የጤናዎች እናት ከሆነች ጥጋብ ደግሞ የበሽታና የዝለት እናት እንደሆነች ግልጽ ነው ። ይህም ከሐኪሙ የመፈወስ በላይ የሆነ ጉዳትን ያመጣል ። እግር ላይ የሚከሰት ሪህ ፣ አንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ሮች ጉዳት ፣ የዓይን መጥፋት ፣ እጅ ላይ የሚሰማ መም ፣ የድምና የሰውነት መንቀጥቀጥ ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ መገታት (ሽባነት) ፣ ውስጣዊና የሚያነድ ትኩሳት ጊዜ ስለሌለን ልንዘረዝራቸውን የማንችላቸው ከዚህ በላይ ሌላ ብዙ በሽታዎች የጾምና የተመጣጠነ አመጋገብ ተፈጥሮአዊ ውጤቶች ሳይሆኑ የጥጋብና አብዝቶ የመመገብ ውጤቶች ናቸው ። ከእነዚህ የሚመጡትን የነፍስ መሞች ብትመረምሩ እነዚህን ታገኛላችሁ ምኞት ፣ ስንፍና ዘን ፣ ድንዛዜ ፣ ከንጽና መራቅ/በኃጢአት መቆሸሸ ፣ በሁሉም ነገር ውስጥ መሳሳትንና ከንቱ መሆንን ።
ነዚህ ነገሮች ምንጭ ጥጋብና ለክቶ አለመብላት እንደሆነ ታውቃላችሁ ። እንዲህ ካለ ግብዣ በኋላ እንዲህ ያለ ሰው ነፍስ በእነዚህ ምኞቶች ተቆራርጦ በዱር አራዊት ከተጫጨቀ አህያ እንኳን ያልተሻለ ይሆናል ። ብት ላይም ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች ምን ያመም እንደሚያጋጥማቸውም ምን ያል ከደስታ የራቁ እንደሆኑ ልናገር ? እነዚህን ቆጥሬ እንኳን አልጨርሳቸውም ። ነገር ግን በአንድ ነጥብ ሁሉንም ግልጽ ላድርግ ። አስቀድሜ እንደተናገርሁት ዓይነት ያለ ማዕድ ላይ ማለትም በጣም ድሎት የበዛበትና ዋጋውም ከፍ ያለ ማዕድ ላይ ሰዎች በስታ አይመገቡም ። ጥጋብ የሁሉም በሽታዎች ምንጭና ሥር እንደሆነ መቆጠብ/ጾም የደስታና የጤንነት እናት ነች ። ጥጋብ ካለ ፍላጎት ሊኖር አይችልም ፣ ፍላጎትም ከሌለ ደስታ እንዴት ሊኖር ይችላል? ስለዚህ ድዎች ከብታሞች የተሻለ መረዳት ያቸውና ጤናሞች እንደሆኑ ብቻ ሳይሆን ከብታሞችም የበለጠ ደስተኛዎች እንደሆኑ ልንረዳ ይገባል ።
ስለዚህ ነገር ስንወያይ ከስካርና ከብት እንሽሽ ። ነገር ግን በማዕድ ካለው (ስካርና ብት) ብቻ ሳይሆን በይወት ላይ ካለው (ስካርና ጥጋብም) ጭምር እንጂ ። በዚህ ፈንታ በመንፈሳዊ ነገር የሚገኘውን ደስታ እንያዝ ። ነዩም፡- “በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።” (መዝ 97፥4) እንዳለው መልካም የሆኑትን ነገሮች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶጸጋና ቸርነት እዚህና በሚመጣው ይወት እንድናገኝ ። በእርሱና ከእርሱ ጋር ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን ። ለዘላለሙ አሜን !
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ