የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

እንኳን 2012 ዓ.ም. ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ !!!

ክፍል አንድ
 
ክርስቶስ በሥጋ ስለ መወለዱ የተዘመሩ መዝሙሮች
ቅዱስ ኤፍሬም
 
በዚህ ቀን ቃላቸው ተፈጽሟል የተናገሩትም ሁሉ ሆኗልና ይህ ቀን ነያትን ፣ ነገታትንና ካህናትን ደስ ያሰኛቸው ቀን ነው ። በዚህ ዕለት ድንግል አማኑኤልን በቤተ ልሔም ወልዳለች ። ኢሳይያስ በጥንት ጊዜ ተናገረው ቃል ዛሬ እውን ሆነ ። የአዛብን ጥር በጽፍ የሚናገረው እርሱ በዚያ ተወለደ ። በአንድ ወቅት ዳዊት የዘመረው መዝሙር ዛሬ ተፈጸመ ። በአንድ ወቅት ሚክያስ የተናገረው ቃል ዛሬ ሆነ ። ከኤፍራታ እረኛ መጥቷል በትሩም ነፍሳት ላይ ይገዛል ። ኦ ! ከያዕቆብ ኮከብ ወጣከእስራኤል ራስ ተነ። በለዓም የተናገረው ትንቢት ዛሬ ተተረጎመ ። የተሰወረው ብርሃን መጣ ከሰውነቱም ውበቱ ፈነጠቀ በዘካርያስ የተነገረው ብርሃን ዛሬ በቤተ ልሔም በራ
የንጉከተማ በሆነው በኤፍራታ የመንግቱ ብርሃን በራ ። ያዕቆብ የባረከው ራኬ ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ ። ልክ እንደዚሁ ያይወት ዛፍ ሟች ለሆኑ ሰዎች ተስፋ አመጣች ። ስውር የሆነው የሰሎሞን ምሳሌ ዛሬ ተገለጠ ። ዛሬ ፃን ተወለደ ስሙድንቅ ነው ! እግዚአብሔር ራሱን እንደ ፃን መግለጡ ድንቅ ነውና ። መወለዱ ያለ ጋብቻ ነበርና መንፈስ ቅዱስ ትኩስ በሆኑ ቃላት አስቀድሞ በምሳሌዎች (ስለ እርሱ) ተናገረ ። መንፈስ ቅዱስ (አስቀድሞ) ያመላከተው ምሳሌ ዛሬ ትርጉሙ ተገለጠ ። ከእርሱ አስቀድሞ በደረቅ መሬት ላይ እንዳለ ሥር መጣበስውር የተነገረው ዛሬ በግልጽ ተደረገ ። በይሁዳ ተሰውሮ የነበረውን ትማርም ከጭኑ መካከል የሰረቀው ስውር በሆነ ሁኔታ የወደደው ንጉ ዛሬ ማራኪ የሆነውን ውበቱን ተነ ሩት በእርሱ የተሰወረውን የይወት መድኃኒት አውቃለችና በቦዝ ጎን ተኛች ። ለሁሉም ይወትን የሚሰጠው ከእርሷ ዘር ተነቷልና ዛሬ መላዋ ተፈጸመ ። እናታችን ሔዋን የተወለደ ካልሆነው/እናትና አባት ከሌሉት ከወንድ ወለደች። (እንዲህ ከሆነ) የሔዋን ልጅ እንዴት ያለ ወንድ ወልዳለች ቢባል አትታመንም ! ድንግሊቱ መሬት የምድር ንጉየነበረውን አዳምን ወለደች ! ዛሬ ደግሞ ድንግል በሰማያት ላይ ንጉየሆነውን አዳምወለደች ። የአሮን በትር አበበች ደረቋም እንጨት ፍሬ አፈራች ። ከድንግል ማፀን (ወንድ) ልጅ ተወልዷልና ምጢሩ ዛሬ ግልጽ ሆነ
አዳኛችን እስካልመጣ ድስ ትንቢታቸው እውነተኛነቱ አልተረጋገጠምና ነቢያትን እንደ እውነተኞች የሚመለከት ያፍራል። የእውነት አባት ከሆነው (ከአብ) የመጣውና የእውነተኛ ነቢያት ትንቢት የፈጸው እርሱ ይባረክ። ጌታ ሆይ ከብትህ ግምጃ ቤት ከቅዱሳት መጻፍትህ መዝገብ የአንተን መምጣት ለመመልከት የናፈቁትን (አስብ) ኖኅን የሸፈኑት ሁለቱ ወንድማማቾች በኩራት የሰከረውን የአዳምን ርቃን ሊሸፍን የሚመጣውን የእግዚአብሔርን አንድያ ልጅ ተመለከቱ። ሴምና ያፌት ደግና መልካም ነው ሊመጣ ያለውን ፣ ፣ ነዓንንም ከኃጢአት ባርነት ነየሚያደረገውን  ደጉን (የእግዚአብሔር) ልጅ ፈለጉት
መልከ ጸዴቅ ሊቀ ካህን እንደ መሆኑ የክህነት ጌታ የሆነውን ሂሶጱም ዓለምየሚያነጻውን ይመለከት ዘንድ ጠበቀው። ሎጥ ተፈጥሮአዊ/እንደተለመደው ያልሆነውን ቅድስና የሚሰጠውን ጌታ ተመልክቷልና ሰዶማውያን ተፈጥሮን እንዴት እንዳጎደፏት አስተዋለ ። አሮን በትሩ እባቦችን የሚውጥ ከሆነ የክርስቶስ መስቀል ደግሞ አዳምና ሔዋንን የበላችውን እባብ እንደሚውጥ ተመለከተ። ሙሴ የእባቡን መርዝ የፈወሰውን የተሰቀለውን (የነሱን) እባብ ተመልክቷልና የጥንቱን እባብ ቊስል የሚፈውሰውን እርሱን አስተዋለ። ሙሴ እርሱ ብቻ ከእግዚአብሔር ብርሃን እንደተካፈለ ተመልክቶ በትምህርቱ (የጸጋ) አምላክነትን የሚሰጠውን እርሱን ፈለገ
ሰላዩ ካሌብ የወይን ዘለላ በመሎጊያ ዞ መጣ ወይኑ ዓለም የሚያጽናናውን (እውነተኛውን) ዘለላ ያይ ዘንድ ናፈቀ። የመጠሪያ ስሙን ኃይል ያውቅ ዘንድ እርሱን የነዌ ልጅ ኢያሱ ናፈቀው ። (ኢያሱ ማለት መድኃኒት ማለት ነው) በኢየሱስ ስም በኃይል ድል ካደረገ ክርስቶስ በልደቱ ምን ያህል ድል ያደርግ ይሆን ? ይህ ፍሬ ሰብስቦና ተሸክሞ ይዞ የመጣው ኢያሱ ፍሬው ለሁሉም ይወትን የሚሰጠውን የይወትን ዛፍ ይናፍቅ ነበር ። እርሱን ረዓብም ትፈልገው ነበር ። ቀዩ ፈትል በምሳሌ ከቊጣ ባዳናት ጊዜ በምሳሌው ከእውነት ቀመሰች። እርሱን ኤልያስም ናፈቀው። እርሱንም በምድር ላይ ባላገኘው ጊዜ ይመለከተው ዘንድ እጅግ ንጽበሆነ እምነት ወደ ሰማይ ረገ ። ሙሴ ተመለከተው ኤልያስም እንዲሁ ። ትቱ ሰው /ኤልያስ/ ከጥልቅ ወደ ላይ ወጣ ቀናውም ጌታ ከላይ ወደ ታች ወረደ በመካከልም (የእግዚአብሔርን) ልጅ ተመለከተው ። (ሙሴና ኤልያስ) የመምጣቱን ምጢር ተመለከቱ ። ሙሴ የሙታን ምሳሌ ኤልያስ የያዋን ሲሆኑ በምጽአቱ ይገናኙት ዘንድ ሄዱ ። ሞቱን የቀመሱ ሙታን ፊተኛ እንዲሆኑ የቀሩት ያልተቀበሩትም እርሱን ይገናኙት ዘንድ ኋለኛ ሆነው ይነጠቃሉ
ደካማ ፍጥረቶች በሆነው በእኛ አንደበት ይቊጠር ዘንድ የማይቻለውን (የእግዚአብሔርን) ልጅ የፈለጉትን የጻድቃንን ቊጥር ሊቆጥር የሚችለው ማን ነው ? እንግዲህ ተወዳጆች በሚቻለኝ መጠን በሌላ ጊዜና በሌላ ትረካ አስቀድሞ ያዩትን እተርክ ዘንድ ጸልዩልኝ ። ወደ እኛ የመጣውን የእውነትን ልጅ ያመሰግን ዘንድ ብቁ የሆነ ማን ነው ? በትውልዳቸው ያዩት ዘንድ ጻድቃን የናፈቁት እርሱን ነው። እርሱ የኪሩቤል ጌታ ነውና አዳም እርሱን ፈለገው። አቤል በእርሱ ዘመን ይመጣ ዘንድ እርሱ ካቀረበው በግ ይልቅ የእግዚአብሔርን በግ ይመለከት ዘንድ እርሱን ናፈቀ ። እርሱን ሔዋንም ፈለገ ። የሴቶች ርቃን መራራ ነበር እርሱም በቅጠል ያይደለ ባጡት ክብር ይከድናቸው ዘንድ የሚችል ነውና። ምጢራዊ በሆነ መንገድ አንዱን እየተመለከቱ ብዙኑ የገነቡት ግንብ ወደ ምድር መጥቶ ወደ ሰማይ የሚያወጣውን ግንብ ገነባ።  እርሱ ነፍሶች መጠለያ የሚያገኙባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይገነባልና የያዋኑ መርከብ በምሳሌ ጌታን ተመለከተ ። በጥፋት ውቀን ምድር ተከፋፍላ ነበር ። እርሱ በእሳት ልሳኖች ምድርን ለዋርያት አከፋፈላት ። እርሱ ወደ ምድር መጣና ጥምቀትን (ባርኮ) ጀሰዎች በእርሱ ወደ ሰማይ ሄዱ ። ሴትና ሄኖክ ከነዓንም የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ተጠርተው ነበር ። በጸጋ ወንድሞቹ ይሆኑ ዘንድ የእግዚአብሔርን ልጅ ፈለጉ። ማቱሳላ ከሺህ ዓመት ጥቂት የጎደለውን ዕድሜ ኖረ እርሱም የማያልቀውን ይወት ወራሾች የሚያደርገውን (የእግዚአብሔ) ልጅ ናፈቀ ። ጸጋም ራሱ ስውር በሆነ ምጢር ጌታቸው በእነርሱ ዘመን ይመጣና ጉድለታቸውን ይሞላ ዘንድ ይለምን ነበር። መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ስለ እነርሱ በተመስጦ ይለምናል። (መንፈስ ቅዱስ) አነቃቃቸው በእርሱም የሚናፍቁትን ያንን አዳኝ ተመለከቱ
ይቀጥላል
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ